>

የምርጫ መታዘብ ቀዳሚ ዘገባ  (ኢሰመጉ)

የምርጫ መታዘብ ቀዳሚ ዘገባ 

ኢሰመጉ

 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በበጎ አድራጎትና ማኅበራት አዋጅ ቁጥር
1113/2011 መሠረት አገር በቀል ድርጅት ሆኖ በምዝገባ ቁጥር 1146 ከ02/11/11 ዓ.ም ጀምሮ በሲቪል
ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዳግም ተመዝግቦ በሕጋዊነት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ
የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ነው፡፡ ኢሰመጉ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ነጻና ገለልተኛ የሆነ የሰብዓዊ  መብቶች ተከላካይ ተቋም ሲሆን፤ ዓላማውም በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት፣ ለሕግ የበላይነት  መስፈንና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የበኩሉን አስተዋጽዖ ለማድረግ ነው፡፡
ኢሰመጉ በ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደረግ መቆየቱ ይታወሳል።  በገጽ ለገጽ ስልጠና፣ በአጭር ጽሁፍ መልዕክቶች፣ በበራሪ ወረቀቶች፣ በራዲዮ መልዕክቶች እና በማኅበራዊ የትስስር ገጾች የመራጮች ትምህርት መስጠት፣ የምርጫ ክርክር መድረኮችን ማዘጋጀት፣  በምርጫ ዑደት ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታን መከታተልና ማጣራት፣ እንዲሁም የምርጫ  መታዘብ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ኢሰመጉ በእነዚህ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች በስምንቱን ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ በኩል ዘጠኝ ክልሎችን እና ሁለቱን የከተማ አስተዳደሮች ለመሸፈን ችሏል፡፡ በዚህም 12
ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎችን በተለያዩ አጋጣሚዎች ተደራሽ እና ተሳታፊ ለማድረግ ችሏል፡፡ ኢሰመጉ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባገኘው ሕጋዊ የምርጫ ታዛቢነት ፈቃድ  መሠረት ከ640 በላይ ታዛቢዎችን ለማሠማራት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህ መሠረት  በቅድመ ምርጫ፣ በድምጽ መስጫ ዕለትና ድህረ-ምርጫ ወቅቶች ያለውን አጠቃላይ የምርጫ ሒደት  እንዲታዘቡ እና የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታን ክትትል እንዲያደርጉ 515 ያህል ቋሚ እና ተዘዋዋሪ
ታዛቢዎቹ በስምንት ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ተሠማርተዋል፡፡ በዚህም ታዛቢዎቻችን  በምርጫው ዕለት ከ 4000 በላይ ምርጫ ጣቢያዎችን ለመታዘብ ችለዋል፡፡ ምንም እንኳ ኢሰመጉ  ለማሠማራት አቅዶ የነበረው ታዛቢዎች ቁጥር ከ640 በላይ ቢሆንም በዋናነት የታዛቢዎች መለያ ባጅ  ህትመት ከምርጫ ቦርድ በኩል በጊዜ ያልደረሰ በመሆኑ፤ በታቀደው ልክ ታዛቢዎችን ለማሠማራት እክል የፈጠረበት መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል…
Filed in: Amharic