>
5:16 pm - Wednesday May 24, 4958

"ህዝብ_እውነቱን ሲያውቅ እርቃንህን ትቀራለህ ብዬህ_ነበር...!!!" (የቀድሞው የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ ጥላሁን አበጀ)

ህዝብ እውነቱን ሲያውቅ እርቃንህን ትቀራለህ ብዬህ_ነበር…!!!”

የቀድሞው የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ ጥላሁን አበጀ

*… አንተ ፍርድ አዋቂ ህዝብ ስላንተ የምከፍለው መስዋዕትነት ያንስሀል! ድንቅ ህዝብ!!!!
ስለ ብርሀኑ ነጋ ምንም ብዬ አላውቅም ዛሬ ግን የሆነ ነገር ተሰማኝ ከምር በቃ ምን እንደሆነ አላውቅም ብቻ የተለየ ስሜት ተሰማኝ ።ብርሃኑን በግል ስሙን አንስቼ በግል ጉዳይ ምንም ማለት አልፈልግም ነበር። በትግል ላይ እያለን የነበሩ ሂደቶችን ሁሉንም በጊዜው ወደናንተ አደርሰዋለሁ።
ለዛሬው ግን ብርሀኑን ስሙን አንስቼ እንድፅፍ የገፋፋኝ አንድ ወቅት እኔ ከእስር ቤት ወጥቼ እሱ መንግስት ባደረገለት ጥሪ ሀገሩ ኢትዮጲያ እንደገባ ነበር አዲስ አበባ ማሪዮት ሆቴል
የተገናኘነው። በተገናኘንበት ሰሞን እኔና ጓደኞቼ መርጌታ ብርሀኑ ተ/ያሬድ ፣ኤፍሬም ሰለሞን እና እየሩሳሌም ተስፋው ባዘጋጀነው የአርበኞች ግ7 አቀባበል አዲስ አበባ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አደባባዮች በባንዲራ ያሸበረቁበት ወቅት ነው።
በነገራችን ላይ ያን አቀባበል ስናዘጋጅ ብርሀኑ ነጋን ለማወደስ ሳይሆን ከ17ዓመት በላይ በኤርትራ በረሃ ሲሰቃዩ የነበሩ በርካታ የትግል ጓዶቼ ለሀገራቸው የበቁበት እና ላመኑበት አላማም ህይወታቸውን ሁሉ ትተው ስለ ሀገራቸው ሲሉ በምንም የማይተካ መስዋዕትነታቸው ክብር ስንል ነበር።
ታድያ አቀባበሉ እንዳለቀ ለአርበኞች ግ7 አመራሮች ማንሳት የምፈልገው ጥያቄ ስለነበረኝ ሁሉንም ከዶ/ር ታደሰ ብሩ ውጭ ያሉ አመራሮችን በየ ተራ አግኝቼ ጥያቄየን ብጠይቅም ለጥያቄየ ብቸኛ መላሽ በትግል ስሙ #ካሳ/ብርሀኑ መሆኑን ነግረውኝ ከሱ ጋር ተገናኘን ።
በወቅቱ ከነበሩኝ በርካታ ጥያቄዎች መካከል:- ከኤርትራ ወደ ኢትዮጲያ ለግዳጅ ስንላክ የነበሩ ችግሮች በአመራሩ ችግር እንደሆነና ይሄንንም ሁሉም አባላት ባለበት እያንዳንዱ ሰው ሂሱን ይዋጥ ፣በትግሉ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው አባላት ህክምና እና መቋቋሚያ ይሰጣቸው፣በንቅናዌው ስም የተሰበሰበ ገንዘብ የኦዲት ሪፖርት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ይነገርና ንቅናቄው ለመጨረሻ ጊዜ ይፍረስ ፓርቲ እመሰርታለሁ የሚል ካለ ከዛ በኋላ መሆን አለበት የሚሉ ጥላያቄዎች ነበሩ።
እንዴት ተጠየኩ በሚል ብስጭት ውስጥ እንዳለ ያስታውቅ ነበር ።ጥያቄዎቼን ተራ በተራ አንስቼ እስክጨርስ እያየሁት የለኮሰው ሲጋራ ሁለቱ ጣቶቹ ላይ እያለ ወደ አመድነት ተቀየረ።”ስማ” ይሄ አንተ ያነሳኸው ጥያቄ እኔን አይመለከትም ጠቅላላ ጉባኤ ሲጠራ ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርበው አሁን እንዲህ አይነት ተራ ጥያቄዎችን የምቀበልበት ጊዜ አይደለም ሲጀመር አንተ ማነህና ነው ይሄን የምትጠይቀኝ? የት አውቅሀለሁ ብሎ አምባረቀብኝና ሌላ ሲጋራ ፍለጋ ኪሶቹን መፈተሽ ጀመረ።
ያኔ እኔም አንዳች የሆነ ነገር ውስጤን ሲያቃጥለኝ ይሰማኛል።አላውቅህም? እንግዲያውስ እወቀኝ አንተ አስመራ ተቀምጠህ በስሜ ስትለምንብኝ የነበርኩት ከሀሬና እስከ አደምድሚት፣ከአደምድሚት አስክ አሸጋላ አሉማ እና የአህያ አብሽ እየበላሁ ፣አፈር ላይ ስንከባለል ከርሜ ባንተ ትዕዛዝ ለወያኔ ተወርውሬ የተሰጠሁት ጥላሁን ነኝ ብየ ንግግሬን በቁጣ አቋረጠው ውጣልኝ •••ውጣልኝ እስኪ ምን ታመጣለህ ማንም አይሰማህም ብሎ ጮኸብኝ።
እኔም ተቀመጥኩበት ወንበር ተነስቼ ከቢሮው ለመውጣት እየሞከርኩ የመጨረሻ መልዕክቴን ነገርኩት አንተ አዲስ አበባ ለመግባት ብዙ የምወዳቸው ጓዶቼ ፊቴ ላይ ወድቀዋል። የካድካቸው እኔን ብቻ ሳይሆን እነዛ በየበረሀው የወደቁ ጓዶቻችንን ነው ። ይሄን ደግሞ አንድ ቀን ታየዋለህ ትቀጣበታለህ ።ሰሞኑን ባንዲራ አልብሶ የተቀበለህ ህዝብ እውነቱን ያወቀ እለት ይፀየፍሀል ።ያ•••••ኔ ታስታውሰኛለህ ብዬው ነበር ከቢሮው የወጣሁት።
ይሄው ያ ጊዜ ደርሶ ዛሬ በአደባባይ ያ እኔም እሱም የምናውቀው ህዝብ ፍርዱን ሰቷል።
አንተ ፍርድ አዋቂ ህዝብ ስላንተ የምከፍለው መስዋዕትነት ያንስሀል።ድንቅ ህዝብ!!!!
Filed in: Amharic