>

"ለሀገራችን ያልሰጠናት የማንሰጣትም ነገር የለም!"  ( አንዱዓለም አራጌ)

“ለሀገራችን ያልሰጠናት የማንሰጣትም ነገር የለም!” 
 
አንዱዓለም አራጌ


 ዛሬ የ2013 ዓ.ም. የምርጫ ተሳትፏቸውን እና ውጤቱን በተመለከተ ፓርቲው አዘጋጅቶት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የማጠቃለያ ንግግራቸው ላይ ቃል በቃል የተወሰደ…..
የሚቆጫችሁ ነገር አለ ወይ ? ለተባለው፡- ለኢትዮዽያ ያልሰጠናት ምንም ነገር አለ ብለን አናምንም፡፡ በጣም ፈታኝ በሆኑ፣ በጣም ስሜትን በሚፈትኑ ሁኔታዎች ወስጥ ስሜታችንን ገዝተን  ሀገር አስቀድመን ነው የተጓዝነው፡፡
ያንን ሁሉ  ያደረግነው ለሀገራችን ብለን ነው፡፡  የተልቅነት መገለጫ ነው፡፡ የትልቅነት መገለጫም የሰዎችን  ሁኔታ መናገር ሳይሆን በራስ ውስጥ ያለን ስሜት መግዛት ነው፡፡  እንደ ግለሰብ ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡ እንደ ድርጅት ግን የተለያዩ አባላቶቻንን ስሜት አርመን  ከፊታን የምናየውን ተስፋ ፣ በትዕግስት  ፣ በፅናት መሥራት ያለብንን ሁሉ  እንድንሰራ የመጣነው መንገድ  በእጅጉ ከባድ ነው፡፡
በኢትዮዽያ ፖለቲካ ውስጥ ሠላማዊ ትግል እንደ ባህል ያልተለመደ ነው፡፡ ያንን ያልተለመደ ያልተሄደበት መንገድ ስንሄድ  የገጠመን ፈተና ከባድ ቢሆንም ለሀገራችን ስንል ያላደረግነው፣ ያልወጣነው ያልወረድነው ነገር የለም፡፡
እያንዳንዱን ነገር እያንዳንዱን የኢዜማ ተወዳዳሪ ፣ እያንዳንዱን አባል ብታዩ ፡ ህይወቱን ሰቶ ነው የተወዳደረው፡፡  ለሀገሩ የከፈለው መስዋዕትነት በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡እያንዳንዱን ዜጋ ለመድረስ፣ እያንዳንዱን ሕዝባችንን ለማንቃት፣ ህይወታችንን አደጋ ላይ ጥለን  ለህይወታችን እንኳን አልሳሳንም፡፡
እውነት ለመናገር እዚህ ባልተረጋጋ ሀገር ውስጥ በየአካባቢው ራሳችንን ፊት ለፊት አጋፍጠን በሠራዊት ታጅበን አይደለም ራሳችን ከሁሉም ሰው መሀከል ላይ አድርገን ሞትን በየደቂቃው ተጋፍጠናል፡፡ ለሀገራችን ያላደረግነው ነገር የለም፡፡
በፖሊሲ ዝግጅት ፣ አዲስ ባህል በማስተዋወቅ፣ በወረዳ ደረጃ ዲሞክራሲን በማለማመድ፣ፓርቲያችን ውስጥ ጭምር ራሳችን በመለማመድና አንደበታችንን በማቀብ ብዙ ነገር ብዙ ናዳ ችለን ነው የተወዳደርነው፡፡  የኢዜማ አባል ብዙ ዱላ ችሎ ፣ ኢዜማም ኢትዮዽያን እያሰበ ወደ ፊት እየተራመደ ያለ ድርጅት ነው፡፡
ስለዚህ እውነት ለመናገር ይሄን ጥያቄ እንኳን አነሳኸው፡፡ ነገር ግን ራሳችሁን ራስህን መጠየቅ የምትችለው ጥያቄ ይመስለኛል፡፡ ኢዜማ የመጣበት አስቸጋሪ መንገድ  ያልተገራ የፖለቲካ ስርዓት፣በልተገራ ባህል ውስጥ ኢዜማ ተገርቶ ለመሄድ ያንን ባህልም ለማለማመድ የሄደበት መንገድ ጠመዝማዛ ነበር፡፡
ግን በድል ተጉዘነዋል፡፡ ስለዚህ ለሀገራችን ያልሰጠናት የማንሰጣትም ነገር የለም ወደፊትም፡፡ እና  ምንም የሚቆጨን ነገር የለም፡፡
ግልፅ ነው እንግዲህ እኔ ነገሮችን በድፍረት መናገር እውዳለሁ እና  ብዙ ጊዜ ሲባል የነበረው ነገር ለምሳሌ ኤሮሚያ ላይ 178 ወንበር ወደ ቁጥር  ወደ 547 ወንበር ብትቀይሩት  በፐርሰንት 36  ወየም 35 ፐርሰንት አካባቢ ይሆናል፡፡  አንድ የመቶ ሜትር ሯጭ  36ኛው ሜትር ላይ ቆሞ እንወዳደር እና ካሸነፍከኝ እጨብጥሀለሁ ፣ እያለህ አዲስ ባህል ነው እና  አሁን እንለማመድ የሚል ተረት  ተረት ቀልድ ነው፡፡
ስለዚህም ከመጀመሪያ ማናችሁም ይህንን መጠበቅ ትችላላችሁ፡፡ ህይወት ስናጣ ፣ህይወት ስንገብር ኦሮሚያ ላይ መሳሪያ ሲቀባበል አበበ አለ በህይወት መሳሪያ በት በነበረበት ሁኔታ መቀስቀስ አትችሉም ሲባል፣ መድረስ አትችሉም ሲባል መንገዱ ሁሉ ሲዘጋ ውጤቱ ወደ ማን ሊያጋድል እንደሚችል የታወቀ ነው፡፡
ፖለቲካሊ ኮሬክት ለመሆን  ጊዜ እንውሰድ ካላላችሁ በስትቀር መጀመሪያ ምን ዓይነት አቅጣጫ ? እንደተወሰደ በደንብ ያስታውቃል፡፡ ግን የኛ ዓላማ እኛ እንደ ፓርቲ ከማሸነፍ በላይ  ደጋግመን ያልነው ቃላቱን እነርሱ እየተቀበሉ እየደጋገሙት ነው፡፡
 እኛ ሁልጊዜ የምናመጣው ኢትዮዽያ እንድታሸንፍ ነው፡፡ እኛ ጠዋትና ማታ የምንብሰለሰለው ኢትዮዽያ እንዴት ታሸንፋለች  እንጂ እህል ውሃ ፍለጋም ሥራ ፍለጋም እንዳልሆነ  ብዙዎቻችሁ የምታውቁ ይመስለኛል፡፡ኢዜማ ውስጥ እሱ አይደለም፡፡
ኢዜማ የሚቃትትለት ዓላማ ኢትዮዽያ እንደ ሀገር አሸንፋ ህዝቧ አንገቱን ቀና አድርጎ የሚኖርበትን ስርዓት ዘመን እንዲመጣ ማድረግ ነወ፡፡
ስለዚህ ውጤቱ ቀድሞ አቅጣጫ ስቶ ነበር ማለት በእውነት ፣ በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡
አብራችሁ ትሰራላችሁ ወይ ? ለሚለው ብዙ የምንመክርበት ነገር ነው፡፡ እንደ ፖሊሲ እንደ መርህ ኢትዮዽያ ውስጥ ኢትዮዽያዊነታቸውን ተቀብለው፤ለኢትዮዽያ ይጠቅማል የሚሉት ሃሳብ ያላቸውን የተለየ መንገድ ያላቸው፣ የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ሁሉ እልህ አስጨራሽ ውይይት በማድረግ ፣ ደርድር በማድረግ ስለሀገራችን አብረን እንሰራለን፡፡ ስለሀገራችን እንመክራለን፡፡
በአፈሙዝ ጨክነን እንደ ምንገዳደለው ሳይሆን እሰከመጨረሻው በአንደበት መከራከር የባህላችን አንኳር ምሰሶ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ኢዜማ በዚህ በኩል ፋና ወጊ ሆኖ ነው የሚቀጥለው፡፡
ፓሊሲዎቹን ለማስፈፀም ሃሳቦቹን ወደ ፊት ለመግፋት ከየትኛውም አካል ጋር ተቀራርቦ ለመስራ ቅድም አቶ የሺዋስ ብሎታል የኢትዮዽያን አንድነት ፣ የኢትዮዽያን ሰላም የኢትዮዽያን ሀገራዊ ተስፋ የማያጨልም መንገድ ለኢትዮዽያ የሚጠቅመውን መንገድ የማያጨልም መስመር ላይ ሁልጊዜ ኢዜማ ይኖራል የሚለውን ነገር እንድትወስዱልን እንፈልጋለን፡፡
አንድ ጥቅል ነገር መጨረሻ ላይ ልናገር እና ላብቃ፡፡
ኢዜማ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን  ይሄ ምርጫ በነገራችን ላይ በገንዘብ ደረጃ እንኳን ከምን ዓይነት ፓርቲ ጋር እንደምንወዳደር ታውቃላችሁ፡፡የሚያስፈልገንን ገንዘብ ለማምጣት ከእያንዳንዱ አባል ኪስ ጀምሮ በውጪ ሀገር ካሉ ዜጎች ጭምር ቀን ከሌት የተከፈሉት ዋጋ በጣም የሚያስደምም ነው፡፡ ለኢትዮዽያ ለሀገራቸው ሲሉ፡፡
ስለዚህ አሁንም ኢዜማዊያን እንፀናለን፡፡  ገዝፈን እንቀጥላለን፡፡  ኢዜማ ከዚህ በኃላም ይገዝፋል፡፡ እስከ አሁን መሠረት እየጣለ ነው የመጣው፡፡
ከዚህ በኃላ የኢትዮዽያን መልካ ምድር ሞልቶ ፣ በኢትዮዽያ ፖለቲካ ተንሰራፍቶ  ገዝፎ ኢዜማ ውስጥ ያለን ሰዎች የምንታወቀው በታጋይነት ነው፡፡ ትናንት ታጋዮች ነበርን፡፡ ዛሬም ታጋዮች ነን፡፡ ነገም ታጋዮች ነን፡፡  ይሄ ጽናታችን መለያችን ነው፡፡
ስለዚህ ገዝፈን እንቀጥላለን !!
ያነገብነውን ራዕይ ለህዝባችን እናስረዳለን!!
ሃሳባችንን በያንዳንዱ ልብ ውስጥ እንዲሰርፅ አንዲጋባ እናደርጋለን!!
ኢዜማ ይፀናል  ይገዝፋል!!
 ለኢትዮዽያ ይታገላል!!
በምንም ዓይንት መንገድ ወደ ኋላ አንመለስም፡፡
 ኢዜማ ውስጥ ያለን ሰዎች…..
Filed in: Amharic