ኦነጋውያን ኦሮሞማ የሚሉት ዘረፋን፣ ወረራንና ቅርምት የትግል ዓላማው ያደረገውን የወንጀል ተግባራቸውን ነው….!!!
አቻምየለህ ታምሩ
ለሁሉ ነገር እርሾ ያስፈልገዋል። አገር ለምራት ደግሞ ከሁሉ በላይ እርሾ ያስፈልጋል። ለልጅ መፈጠር የእናት ማሕጸንና የእንቁላል አስኳል እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለማንኛውም አካል ለመፈጠርና ለማደግ የተመቻቸ መነሻ ያስፈልገዋል። እነዚህ እርሾዎች ሳይመቻቹ አዲስ፣ ተተኪ ወይም የተሻለ ፍጥረት ሊመጣ አይችልም። አገሮች የሚፈጠሩበት፣ ቀድመው ከነበሩበት ሁኔታ ለማሻሻል ወይም በተሻለ ለመተካትም ቢሆን የሚሳካው ያንን የሚያመቻች አስኳል ነገር አልያም እርሾ ሲኖር ብቻ ነው።
አንድ የጦር መሪ አገሮችን ወግቶ በቁጥጥሩ ውስጥ ስላደረገ ብቻ አገር አይመሰረትም፣ መምራትም አይቻለውም። ይህ ባገራችም፣ በውጪም አገሮችም የታየ ታሪክ ነው። የግሪኮችን፣ የሮማን፣ የእንግሊዝን፣ የአሜሪካንን፣ የሩሲያን፣ የጃፓንን ታሪክ ብንመለከት አገሮቹ የተፈጠሩት አስኳል የሚሆን ምቹ ሁኔታ ስለነበራቸው፤ ካልነበራቸው ደግሞ ከሌላ አገር እንደ እርሾ በመዋስ ነው። ድሮ የንጉሣዊ ቤተሰብ ያልነበራቸው አገሮች አገር ለመመስረት ሰማያዊ ደም ያለውን ከሌላ አገር አንዳንዴም ከባላንጣ አገር ይዋሱ ነበር። የዛሬው የኖርዌይ ንጉሣዊ ቤተሰቦች የመጡት ከድሮ ገዢዎቻቸው ከዴንማርክና እንግሊዝ ነው። ካናዳ እንደ አገር የቆመችው ከእንግሊዝ አገር ዘውድ ተውሰው የአገራቸው ምልክት በማድረግ ነው።
ሕገ መንግሥቶችንና የሕግ ስርዓቶችን የወሰድን እንደሆነም ታሪኩ ተወራራሽ ናቸው። ሌሎች ባሕሎች የራሳቸውን ተጽዕኖ ወይም አስተዋጽዖ ቢያደርጉም የመጀመሪያው እርሾ ለምን ኖረ የሚል ጥያቄ ግን አያስነሳም። ያለፉት ሶስት ሺሕ ዓመታትና እስከ ዛሬም ያለውን የኢትዮጵያን ታሪክ መለስ ብለን ካየነው የሚነግረን ይህንኑ ነው።
ዮዲት ያካሄደችው አብዮት ወገኔ ያለቻቸውን የአንድ ጎሳ ጦረኞች ወደ ስልጣን ቢያወጣም ወደ ስልጣን የመጡት ግን አገር በመምራት ኢትዮጵያን ማስተዳደር አልቻሉም፤ ስለዚህ ራሳቸውን ስልጣኑን ለሚመራ ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን በመጨረሻ ያለጦርነት ዘውዱን አሳልፈው ሰጥተው ሄዱ። ግራኝ አሕመድ ጦሩን ይዞ ኢትዮጵያን መቆጣጠር ቢችልም፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማስተዳድር የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ዝግጅት ስላልነበረው ከሱ እሳቤ ውጭ ያለውን ማጥፋት እንደ አማራጭ ወስዶ መጨረሻ ሳይሳካለት ቀርቷል።
ከግራኝ በኋላ በመላው ኢትዮጵያ እንደዋርካ የተስፋፉት አባገዳዎችም ከሶስት መቶ አመታት በላይ እየተስፋፉ የአገሪቱን ለም መሬት በቁጥጥራቸው ስር ሲያደርጉ የሌላውን አክብሮ አብሮ የመኖር ምንም ፍላጎት አልነበራቸው። ስለዚህ የነበረውን ዘር ሁሉ ማጥፋት እንደአማራጭ ወሰዱት እንጂ ሁሉንም እንዳባቱ የሚኖርበት አገር አልገነቡም። ባለፉት ሀያ ሰባት አመታት ስልጣን ላይ የነበሩት ወያኔዎችም በዘር ተደራጅተው በመንግሥትነት ቢሰየሙም በሀያ ሰባት አመታት ውስጥ ያደረጉት ነገር ቢኖር የዐፄ ይኩኖ አምላክ መንግሥት ወደ ስልጣን ተመልሶ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 1966 ዓ.ም. ድረስ ለ 750 አመት ያልተካሄደ መዝረፍና ማፈናቀል በ27 ዓመት ውስጥ መዝረፍና ማፈናቀል ነው። እነዚህ ዘራፊዎች ሀብታችንን ጨርሰው ኩላሊታችን ወደ መዝረፍ ገቡ እንጂ አገር ለመገንባትና ማስተዳደር ችሎታምም ፍላጎት ፍላጎት እንዲሁም የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ አልነበራቸውም።
ብሔርተኛነት እንደ እሳቤ የያዙ ሁሉ አላማው የሌላውን ነጥቆና ተቀራምቶ የራስ ብቻ የማድረግ የቅሚያ፣ የወረራና የመውረስ እንቅስቃሴ እንጂ ከእኩልነትና መብት ትግል ጋር የሚያገናኘው አንዳች ግብ የለውም። ኦሮሙማን ታጥቀው በመንግሥትነት የተሰየሙት እነ ዐቢይም አላማቸው እንደዚያው ነው። ለዚህም ነው የእነ ዐቢይ የአፓርታይድ አገዛዝ ፋሽስት ወያኔ 27 ዓመታት የፈጀበትን የቅድሚያ፣ ወረራና የመውረስ ክብረ ወሰን በአስር ወራት ውስጥ የሰበረው።
የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አግዛዝ መንግሥታዊ ያደረገው እሳቤ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውና እርሾ ያለው የኢትዮጵያ የሥነ መንግሥት ሳይሆን ኦነጋውያን ኦሮሞማ የሚሉት ዘረፋን፣ ወረራንና ቅርምት የትግል ዓላማው ያደረገውን የወንጀል ተግባር ነው። የኦሮሙማው ፈጣሪዎች የሆኑት ኦነጋውያን ፖለቲከኞች ሳይሆኑ ዘረፋን፣ ወረራንና ቅርምትን የትግላቸው ዓላማ ያደረጉ፣ ሕጻናትና ሴቶችን ሲሰልቡና ሲዘርፉ የኖሩ፣ አቅመ ደካሞችን ሲያፈናቅሉ የኖሩ ተራ ማጅራት መቺዎች ናቸው። ኦነጋውያን ሁሉ የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ የሌላቸው ወሮበሎች ስለሆኑ ከነሱ አስተሳሰብ ውጭ ያለን ሲያምር ያዩትን ነገር ሁሉ ካላጠፉ እንቅልፍ አይሰውዳቸውም።
የኦነጋውያንን ፖለቲካ የሚገልጸው ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም «ፋቡላ የአውሬዎች ተረት ተውኔት» በተሰኘው ድርሰታቸው ውስጥ የጻፉት ዘመን ተሻጋሪ ግጥም ነው። ተከለ ሐዋርያት በጻፉት የፋቡላ ተረቶች ውስጥ ገጸ ባህርያት ከሆኑት መካከል እንስሳት በተለይም አውሬዎች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። ገጸ ባሕርያቱ እንስሳት በመሆናቸው ይመስለኛል ተክለ ሐዋርያት የመጽሐፉን ርእስ «ፋቡላ የአውሬዎች ተረት ተውኔት» ሲሉ የሰየሙት።
በነገራችን ላይ የፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም «ፋቡላ የአውሬዎች ተረት ተውኔት» የጆርጅ ኦርዌል «የእንስሳት እርሻ» ወይንም Animal Farm የሚለው አጭር ልበ ወለድ ድርሰት ከመጻፉ ዘመናት በፊት በቲያትር መልክ ጽፈውና አዘጋጅተው አዲስ አበባ ላይ በዘመናቸው መድረክ ላይ ያቀረቡት ግሩምና ድንቅ ጽሑፍ ነው። የፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም ተረት የአውሬ ዞምቢዎች ተውኔት ነው። በሞተ ልብ፣ በበሰበሰ ኅሊና፣ በቆሸሸ ስብዕና የሚገለጡት አውሬ ዞምቢዎች መልካም ነገር ካዩ እንቅልፍ የላቸውም፤ በጎ ነገር አይታያቸውም። መልካም ስራ ፍሬ ሲይዝ ካዩት ልክ እንደ ፋሽስት ወያኔ ከስሩ ይነቅሉታል።
ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም በ«ፋቡላ የአውሬዎች ተረት ተውኔት» ድርሳናቸው የኛዎቹን ዞምቢዎች የናዚ ኦነጋውያንን አውሬነትና ጠባይ ፋቡላዋ አውረ በሰው ሰውኛ የተናገረችው አድርገው አራት ስንኝ ባለው ጉልበታም ግጥም እንዲህ ይገልጹታል፤
አንድ ነገር ሲያምር ያየሁት እንደሆን፣
ያንን ታላጠፋሁ ከቶ ምንም ቢሆን፣
ዕረፍት አላገኝም እንቅልፍ አይወስደኝም፣
ቅን ነገር አይቼ እኔ አያስችለኝም።
በሰው አምሳያ የተፈጥሩት ፋቡላዎቹ ኦነጋውያንም ሲያምር ያዩትን ሁሉ ካላጠፉት፣ ዞምቢ ካላደረጉት፣ ካልወረሱትና የነሱ አድርገው ከላከሸፉት እንቅልፍ የላቸውም። በፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም የተገለጠው «ፋቡላ የአውሬዎች ተረት ተውኔት» መስተጋብር በዐቢይ አሕመድ የአፓርታይግ አገዛዝ ዘመን የየእለቱ የሕይወታችን አካል ሆኗል።
ዐቢይ አሕመድና የዘረጋው የአፓርታይድ አገዛዝ ባላደራዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ጥንታዊቱን በራራን፤ ዘመናዊቱን አዲስ አበባን አፍርሰው በኦነጋውያን የደነዘዘ አእምሮ ውስጥ በተፈጠረችው ፊንፊኔ ለመተካት ያላፈረሱት የቆየ አሻራና የከተማይቱን ጥንታዊነት የሚመሰክር ምልክት የለም። የከተማ አስተዳደሩን የፖሊስ ሠራዊት ኦሮሚያ ከሚባለው ክልል በመለመሏቸው ለከተማው ከባሕር የወጣ አሳ በሆኑ የፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ ቀሮዎች ተክተውታል። ደብረ ዘይት በሚገኘው ሆራ ሐይቅ ከመስቀል በኋላ ይከበር የነበረውን እሬቻን “ሸገርን ለማስዋብ” በሚል ዐቢይ አሕመድ ግለሰቦችን [አብዛኛዎቹ አማሮች ናቸው] አምስት አምስት ሚሊዮን ብር እንዲያወጡ አድርጎ ባስቋረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ውስጥ አዲስ አበባ እንዲከበር አድርገዋል። በመሰረቱ እሬቻ የኦሮሞ ገዢ መደብ በየስምንት አመቱ ሲያደርግ የኖረውን ወረራ ገና ሳያካሂድ፤ የእርሻ ስራና ሰብል ማምረት ሳይጀምርና ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ምድር ሳይስፋፋ መስከረም በገባ መስቀል በተከበረ በሳምንቱ ሲከበር የኖረው ደብረ ዘይት የአቡዬ የጸበል ሥፍራ በነበረው በሆራ ሐይቅ ነው።
እዚህ ላይ አንባቢ ግር እንዳይሰኝ አንድ ነገር ላክል። እሬቻ የሚለው ቃል የአማርኛ ቃል እንጂ የኦሮምኛ ቃል አይደለም። እሬቻ ኦሮምኛ ነው የሚል ቢኖር የቃሉን የኦሮምኛ ግንድና ቃሉ በኦሮምኛ እንዴት አንደሚረባ ማስረዳት ይጠበቅበታል። የግዕዙ ሊቅ አለቃ ደስታ ተክለ ወልድ “ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት” በሚል ባሰናዱት መዝገበ ቃላት ውስጥ እንደጻፉት እሬቻ ዋናው ሰብል ደርቆ ከመታጨዱና በአውድማ ተወቅቶ ወደ ጎተራ ከመግባቱ በፊት ቀድሞ የደረሰው ተቆርጦ በበትር በመወቃት ወይም በእጅ ታሽቶ የሚቀመሰው እህል ይሉታል። ለላው ሊቅ ከሣቴ ብርሃን ተሰማም በ1951 ዓ.ም ባሳተሙት “የአማርኛ መዝገበ ቃላት” መጽሐፋቸው የአማርኛ ቃል ስለሆነው እሬቻ የሚነግሩን ትርጉም ተመሳሳይ ነው። በመሆኑም የእሬቻ በዓልንም የሚያከበረው አራሹ ገበሬ ክረምቱን በሰላም እንዲያልፍ፤ ያዘመረው እህል ለፍሬ እንዲበቃና እሸት እንዲቀምስ ያስቻለውን ፈጣሪውን ለማክበር ነው። ባጭሩ የእሬቻ በዓል እህል የሚያበቅል አራሽ ገበሬ የሚያከብረው አመታዊ ዝክር ነው።
የኦሮሞ ብሔርተኞቹ እነ ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን፣ ዶክተር ነገሶ ጊዳዳ፤ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፤ አቶ ይልማ ደረሳ፤ ፕሮፈሰር ተሰማ ታዓ፤ ወዘተ እንደነገሩን ደግሞ ኦሮሞ ከብት በማርባት የሚተዳደር የነበረ ሲሆን የእርሻ ስራ የጀመረው ዛሬ በሰፈረበት አካባቢ ከረጋ በኋላ ከ17ኛውና ከ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ ነው። ይህ ማለት የተሰማራበት የስራ መስክ ከብት ማርባት፤ እምነቱ ደግሞ ዋቄ ፈና ነው የተባለው ኦሮሞ የማያበቅለው እህል የሚሽትበትን ወቅት ጠብቆ ሃይማኖቱ አይደለም የተባለውን መስቀልን አሳልፎ መስቀል በሆነ በሳምንቱ እህል እንዲያበቅል፤ እሸት እንዲቀምስ ለሚያስችል ፈጣሪ ምስጋና ሊያቀርብ ይችላል ካልተባለ በስቀር ከብት አርቢ የነበረው ኦሮሞ እሬቻን ማክበር የጀመረው ሸዋን ሲወር ያገኛቸው አራሽና እህል አብቃይ የአማራ ገበሬዎች ያመረቱት ሰብል ለፍሬ እንዲበቃና እሬቻ [እሼት] እንዲቀምሱ ላስቻላቸው ፈጣሪያቸው ያቀርቡት የነበረውን የምስጋና ባሕል በመውረስ ነው። ስለዚህ እሬቻ ከብት አርቢ የነበረው ኦሮሞ ከነ ቃሉ ከሰብል አምራች የአማራ አርሶ አደሮች የወረሰው የምስጋና በዓል ሲሆን ኦሮሞ አካባቢውን ከመውረሩ በፊት ጀምሮ ይከበር የነበረው ደብረ ዘይት በሚገኘው ሆራ ሐይቅ እንጂ አዲስ አበባ ውስጥ አልነበረም።
ይህ እውነት ቢሆንም ቅሉ የኦነጋውያን ኦሮሙማ ማዕከሉ ዘረፋ፣ ወረራና ቅሚያ ስለሆነ አዲስ አበባን ዳግማዊ ምኒልክ ከመምስረታቸው በፊት የነበሩት ኦሮሞዎች፤ እሬቻም ከነ ቃሉ የኦሮሞ አይደለም፤ አዲስ አበባ ውስጥም ተከብሮ አያውቅም የሚለው የታሪክ እውነት ደንታ አይሰጣቸውም። በዚያ ላይ በአዲስ አበባ ዙሪያና በመላው አገሪቱ የሚገኘው ኦሮምኛ ተናጋሪ ሁሉ ኦሮሞ አለመሆኑን የራሳቸው ሰዎች እንኳ ያጠኑትን ታሪክ ለመቀበል ዝግጁ ያልሆኑ ሕመምተኞች ናቸው። በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ኦሮሞዎቹ ወራሪዎቹ አባገዳዎቹና የነሱ ዘመዶች ብቻ ናቸው። ነባሩ ሕዝብ ኦሮምኛ እንዲናገር የተደረገው ተገዶ ኦሮምኛ ስለተናገረ ኦሮሞ ነው ማለት አይደለም።
ኦሮምኛ የሚናገረው ሁሉ ኦሮምኛ እንዳልሆነ እውነተኞቹ ኦሮሞዎቹ ራሳቸው ምስክር ናቸው። በእውነተኞቹ ኦሮሞዎች ትውፊት ውስጥ «Salgan Borana, sagaltamman gabra» የሚል አባባል አለ። ይህ ወደ አማርኛ ሲተረጎም «ዘጠኙ ኦሮሞ ነው፤ ዘጠናው ገርበ ነው» ማለት ነው። ገርበ ኦሮሞ ሲስፋፋ ያስገበራቸውንና ባርያ ያደረጋቸውን ነገዶች የሚጠራበት ስያሜ ነው። በኦሮሞ በራሱ ትውፊት መሰረት ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ ከሚኖረው ኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝበ መካከል ትክክለኛው ኦሮሞ ከአስሩ አንዱ ብቻ ነው ማለት ነው። ከአስሩ ዘጠኙ ገርበ ወይም በአባገዳዎች በወረራ የተያዘና በኃይል ኦሮሞ የተደረገ ሕዝብ ነው።
ይህንን እውነት ከኦሮሞዎች ትውፊት በተጨማሪ ዛሬ በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። የሰላሌና አምቦ ሕዝብ የDNA ውጤት እንደሚያሳየው ዝምድናው ከምንጃርና ወይም ጅሩ ሕዝብ ጋር እንጂ ከቦረና (እወነተኛው ኦሮሞዎች) ጋር አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ ፖል ሶሊሌት የተባለው የፈረንሳይ ጎብኝ እ.ኤ.አ. በ1884 ዓ.ም. ሸዋን ጎብኝቶ በጻፈው የጉዞ ማስታወሻው በሰላሌና ጃርሶ ውስጥ ኦሮሞ ገርበ ያደረጋቸው የአካባቢው ቀደምት ባለይዞታዎች አማሮች እንደሆኑ ጽፏል።
የአርሲ ሕዝብ ዝምድናው ከሐዲያ ጋር እንጂ ከቦረና ጋር አይደለም። ጀርመናዊው የታሪክ ምሁር በርካምበር እንዳጠናው ከአርሲ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛው ሐድያ ነው። የጅማ ሕዝብ ከየምና ከከፋ ሕዝብ እንጂ ከኦሮሞ ጋር ምንም ዝምድና የለውም። አባጅፋር ራሱ አረብ እንጂ ኦሮሞ አይደለም። ወለጋ እውነተኛ ኦሮሞዎች ከመቶ አስርም አይሞሉም። እውነተኛ ኦሮሞዎቹ ለባሪያ ፍንገላና ውሀና ሳር ፍለጋ መጥተው ሌላውን ገርበ አድርገው የቀሩት አባገዳዎችና ልጆቻቸው ብቻ ናቸው።
የትኛውም ብሔርተኛ ቢሆን አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር አይቻለውም። በየትኛውም አለም ብሔርተኛ ሆኖ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር ሲያፈርስን እንጂ አገር ሲያረጋጋና ሲያስተዳድር ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም። በኢትዮጵያም ሆነ በአለም ታሪክ በብሔርተኛነት እሳቤ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር የማስተዳደር እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ ያለው አገዛዝ የለም። የኦሮሞ ብሔረተኞም ዓላማቸው ወንድምን በወንድም ላይ እኅትን በእኅት ላይ በማስነሳት የኦርሞ ኤምፓየር ቅዠታቸውን ማሳካት እንጂ ኢትዮጵያ የምትባልን አገር የማስተዳደር ፍላጎት፣ እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ የላቸውም።
ከነገዳቸው ውጭ ያለውን የተቀረውን ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ይዞ ለመቆየት የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ እሴት እንዲሁም የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ የሌላውን ዘረፋን፣ ወረራንና መውረስን ፖለቲካቸው ያደረጉ ያበዱ ብሔርተኞች መንግሥት ይሆኑናል ብሎ ማሰብ ውሻ ነከሰኝ ብሎ ለጅብ አቤት እንደማለት አይነት የዋህነት ነው። ብሔርተኛ ሁሉ አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር እንደማይችል ያለፉት አርባ አራት አመታት የኢትዮጵያ የቁልቁለት መንገድ ምስክር ነው። ልክ በቅሎ እንደማትወልድ ሁሉ የነገዱ ሳይሆን የኢትዮጵያ ስነ መንግሥት እሳቤ የሌለው፣ ከነገዱ ውጭ ያለውን የተቀረውን ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ይዞ ለመቆየት የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ እሴት ያልያዘ ማናቸውም አይነት የሁሉም መንግሥት የመሆን ችሎታ የለውም። ያለው ችሎታ ቢኖር እንደ ወያኔና ኦነግ የሌላውን መዝረፍ፣ መቀማት፣ መቀራመት፣ መውረስና የተሰራ አገር ማፍረስ ብቻ ነው። ይኼው ነው።