>

መከላከያ ሠራዊት መቀሌ ከተማን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሉ ሲቪሎች  ከለላ ሊደረግላቸው ይገባል..!! (አምነስቲ ኢንተርናሽናል )

መከላከያ ሠራዊት መቀሌ ከተማን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሉ ሲቪሎች  ከለላ ሊደረግላቸው ይገባል..!!

አምነስቲ ኢንተርናሽናል

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪቃ፣ የአፍሪቃ ቀንድ እና የታላላቅ ኃይቆች አካባቢ ምክትል ዳይሬክተር ሣራ ጃክሰን ባወጡት መግለጫ፤ ድርጅታቸው ትግራይ ውስጥ የሲቪሎች ደህንነት በብርቱ እንዳሳሰበው አመልክተዋል። ሲቪሉ ኅብረተሰብ ለወራት ጦርነቱን እና የመብት ጥሰቶችን እንዲሁም የጦር ወንጀልን ተቋቁሞ መቆየቱን በመጥቀስም የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች አካባቢውን ለቅቀው ሲወጡ እና የክልሉ ኃይል በስፍራው ሲተካ ለሲቪሎች ተገቢውን ከለላ ማረጋገጥ መሠረታዊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በመሆኑም «ቀጣይ ግድያ እና የጦር ወንጀል ከመፈጸም ሁሉም ወገኖች እንዲታቀቡ፤ በተለይም የበቀል ጥቃቶች በወታደሮቻቸውም ሆኑከእነሱ በወገኑሚሊሺያዎቻቸው እንዳይፈጸም ጥሪ እናቀርባለን።» ብለዋል።

በተጨማሪም ሁሉም ወገኖች ለሲቪሎች ያለምንም መሰናክል ሰብዓዊ ርዳታ እንዲቀርብ እንዲሁም የመገናኛ ስልቶች ባለመኖራቸው ዳግም የኢንተርኔት፣ የሕትመትም  ሆነ የራዲዮ እና ቴሌቪዥን አገልግሎት እንዲሠራ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።
የትግራይ መከላከያ ሃይሎችም ሆኑ የዚህ አካል የሆነው ህወሓት ወደ ከተሞች ተመልሰው ሲገቡ: ከብልፅግና ጊዜያዊ አስተዳድርም ሆነ ከኢትዮጵያ መከላከያ ጋር የወገኑ ተጋሩዎችን በጠላትነት ከማየትና ሰብአዊ መብታቸውን ከመንካት እንዲቆጠቡ ማስታወስ እወዳለሁ:: ትግራይ የህወሓት ብቻ ሳትሆን የኢትዮጵያ መንግስትንም የሚደግፉ ተጋሩዎች መኖርያ መሆኗን መቀበል ያስፈልጋል:: ወደቀድሞ የወያኔ አፋኝ አሠራሮችና የመብት ረገጣዎች ላለመመለስ አዲሱ የትግራይ መከላከያ ሃይሎች አዲስ አመራር በዴሞክራሲያዊ መንፈስ የታነፀ እንዲሆን ይጠበቅበታል:: ማንም ትግራዋይ በፖለቲካ አስተሳሰቡ የማይሰጋበት: በጠላትነት የማይታይበት: ከህወሓት የተለየ የፖለቲካ አተሳሰብ ማራመድ የሚችልበት አዲስ ህይወት ለትግራይ እመኛለሁ::
Filed in: Amharic