>

ክህደቱ ፈጠነ እንጂ የማይጠበቅ አልነበረም...!!!  (መቅደስ አበጀ)

ክህደቱ ፈጠነ እንጂ የማይጠበቅ አልነበረም…!!! 

.መቅደስ አበጀ

ብረት-ነከሱ- ኦሮ ማራ ወደፖለቲካ ድል የማይመነዘር በምንም ማሰሪያ ውል ያልታሰረ ያልተቀደሰ ጋብቻ ነበር። በአማራ ልዩ ሀይል፣ በአማራ ሚሊሻና አብይ በሚያዘው መከላከያ ሠራዊት መካከል ያለው የብረት-ነከስ የውሽሜ ጥምረት (tactical alliance) የቅዱስ ጋብቻ ጥምረት (strategic alliance) አድርገህ ራስህን ያሞኘህ አንተ የተኛህ አማራ ንቃ!!!
.
በስታሊን የሶቭየት ጦርና በአሜሪካ መካከል የነበረው የብረት-ነከስ ጥምረት ናዚን ከማስወገድ በዘለለ መዳረሻ አላማቸው የሰማይና የምድር ያህል የተራራቀ ነው። ሌላው ቢቀር ተስማምተንበታል ባሉት ብረት-ነከሳዊ የናዚ መወገድ ላይ ሳይቀር ከጀርባ ብዙ ደባ ይፈፀም ነበር። ለምሳሌ ከሂትለርም ይሁን ከናዚ ጦር ጋር የተናጠል ስምምነት አልያም ድርድር ላለማድረግ የተስማሙ ቢሆንም በጦርነቱ መገባደጃ አካባቢ የአሜሪካ መንግስት የካዛብላንካውን የጋራ ስምምነት በመጣስ ስዊዘርላንድ በሚገኘው የ Office of Strategic Service ተወካዩ ኤለን ደለስ (ከ1953-1961 የሲ.አይ.ኤ ዳይሬክተር) አማካኝነት በሰሜን ጣልያን ይገኝ ከነበረው የናዚ ጀርመን ጦር አዛዥ ከጄነራል ካርል ቮልፍ ጋር “operation sunrise” የተባለ “ድብቅ” የተናጠል ስምምነት በማድረግ ሰሜን ጣልያንን ያለውጊያ ለአሜሪካ ጦር እንዲያስረክብ በምላሹ ጄነራል ካርል ቮልፍ በጦርነቱ ማግስት በናዚ ወታደራዊና ሲቪል ባለስልጣናት ላይ ከሚመሰረተው ማንኛውም ክስ ነፃ እንዲደረግ ደባ ተፈፅሟል።
.
ይህንን ያወቁት ሶቭየቶች ብረት-ነከሱ የጋራ ዘመቻ ሳይጠናቀቅ ቀዝቃዛው ጦርነትን ጀመሩ። ብረት-ነከስ ጊዜያዊ ጥምረት በተቃራኒ የቆመን ብረት-ነከስ የጋራ ጠላትን ለመምታት እንጂ ከዚያ በኋላ ላለው ነገር ቀድመህ ካልተዘጋጀህ ከውድቀትህ አወዳደቅህ የከፋ ይሆናል።
ብረት-ነከሱ- ኦሮ ማራ ወደፖለቲካ ድል የማይመነዘር በምንም ማሰሪያ ውል ያልታሰረ ያልተቀደሰ ጋብቻ ነበር።
ሲጀመር አብይ ጦርነቱን ያወጀው ዙፋኑ መነቃነቅ ስለጀመረ ነው። አላማውም ዙፋን ነቅናቂውን ቡድን ማስገበር እንጂ እኛ እንደምንመኘው ህወሃትን ማጥፋት አይደለም። የዚህ ማረጋገጫው ደግሞ በሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ላይ ፍፁም ኢሰብአዊ የሆነ ጭፍጨፋን የፈፀመው ሀይል ዛሬ በመቀሌ እንዲፈነጭ መፈቀዱ ነው። እሬሳው ከጉድጓድ አፈር ልሶ መውጣቱ ነው። የአማራ እርስቶች ዳግም ስጋት ላይ መውደቃ ነው።
.
የአማራ ህዝብ በእነዚህ ግዛቶቹ ላይ ያለው ጥያቄ የዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥያቄ አይደለም፤ የአማራ ህዝብ ጥያቄ የርስት ባለቤትነት ጥያቄ ነው!!! የአብይ መንግስት ግን “መሬቱ የመላው ኢትዮጵያ፣ አስተዳደሩ በትግሬ ክልል ቢሆንም ባሉበት ቦታ የአማራዎች መብት ተከብሮላቸው በቋንቋቸው እየተማሩና እየተዳኙ ይኖራሉ” ወደሚል፣ የፈሰሰው የአማራ ደምን ደመ-ከልብ የሚያደርግ ክህደት እየገፉት ይገኛል።
.
ሳይረፍድ እደግመዋለሁ፥ በደምህ ያስከበርከውን ወሰን፥ እስከመጨረሻው ለማፅናት፥ አጀንዳውን ከምናምን አስመላሽ ኮሚቴና ከፓርቲ ትከሻ አውርደህ የመላው አማራ ህዝብ አጀንዳ አድርገህ ህዝባዊ መነቃነቅ ፍጠር።
ርስቶቻችን የመላው አማራ ናቸው፥ ባለቤት የሆነውን መላውን የአማራ ህዝብ ካስነሳህና ህዝባዊ አጀንዳ ካደረግኸው፥ አብይ አህመድና ሰራዊቱ በፊትህ ድንክ ናቸው።
Filed in: Amharic