>
5:21 pm - Wednesday July 21, 9238

መንግስት ያቀረበውን የተኩስ አቁም ስምምነት ህወሓት "አልቀበልም!" አለ...!!!  (ማለዳ ቲቪ)

መንግስት ያቀረበውን የተኩስ አቁም ስምምነት ህወሓት “አልቀበልም!” አለ…!!!

 ማለዳ ቲቪ

*… *….  “ጠላት” ያልና ቸውን ኃይሎች ለመውጋት እስከ ኤርትራ እና አማራ ክልል  እንዘምታለን”  
የሕወሃት ቃል አቀባይ  ጌታቸው ረዳ
*…. “በእኛ እና በመላ የአማራ ህዝብ መቃብር ላይ ካልሆነ ዳግም “ተከዜን” የሚሻገር አንዳች የትህነግ አሻባሪ ቡድን አይኖርም!
ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ 
 according to the source from CNN the rebel group of TPLF refused to accept the cease fire
ከህወሀት ጋር ጨዋታ ስታለቅስ ለመኖር ስትፈልግ ብቻ ነው ።
የአገሪቱ መንግስት አሸባሪ ካለው ጋር ነው የተኩስ አቁም ስምምነት ፈጠርኩ ያለው ሆኖም ህወሓት የክልሉን አንዳንድ ከተሞች ከተቆጣጠረ ወዲህ የምን ተኩስ አቁም ስምምነት ነው አብይ አህመድ ተገዶ ነው እንዲህ አይነት ቀልድ አልቀበልም ሲል አስታውቋል.
ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው ኤርትራን እና አማራን እንደሚወጉ ዝተዋል ከዛ ባለፈ አዲስ አበባን በቅርብ እንደሚጠቀልሉ ለትግል አጋሮቻቸውም ገልፀዋል።
ህወሓት በምንም አይነት መንገድ ከአብይ አህመድ የሚቀርብለትን ምንም አይነት ጥያቄ እንደማይቀበል ከስፍራው መረጃወች ወተዋል  ከወደ ኤርትራ በኩልም አዲስ መረጃ ወቱዋል በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት የተኩስ ማቆም ስምምነት ብሎ ሙሉ ለሙሉ ለህወሀት ለቆ መውጣቱ በኤርትራ አክቲቪስቶች ዘንድ ቁጣን ፈጥሮዋል ኤርትራም ጦሩዋን ወደ ድንበር ማስጠጋቱዋ እየተሰማ ነው ።
ህወሓት የተኩስ አቁም ስምምነት አልቀበልም ማለቱን የዘገበው CNN ነው እነሆ
“ጠላት” ያልና ቸውን ኃይሎች ለመውጋት እስከ ኤርትራ እና አማራ ክልል  እንዘምታለን”  
የሕወሃት ቃል አቀባይ  ጌታቸው ረዳ  
የአማጺው ሕወሃት ተዋጊዎች “ጠላት” ያሏቸውን ኃይሎች ለመውጋት እስከ ኤርትራ እና አማራ ክልል ድረስ ሊዘምቱ እንደሚችሉ የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡ ሕወሃት የመንግሥትን የተናጥል ተኩስ አቁሙን ውድቅ በማድረግ፣ በቀጣዮቹ ቀናት ተዋጊዎቹ ወደ ደቡባዊና ምሥራቃዊ ትግራይ ይዞታቸውን እንደሚያሰፉ አስታውቋል፡፡ መቀሌ ከተማ ሙሉ በሙሉ በአማጺው ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መሆኗን ጌታቸው አረጋግጠዋል፡፡ከዚኽ መግለጫ በኋላ የዐማራ ብልጽግና መልስ የሰጠ ሲሆን በአማራ ክልል የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ  ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ በተጨማሪ ከዚኽ በታች ያለውን መግለጫ አውጥተዋል።
በእኛ እና በመላ የአማራ ህዝብ መቃብር ላይ ካልሆነ ዳግም “ተከዜን” የሚሻገር አንዳች የትህነግ አሻባሪ ቡድን አይኖርም!
ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ 
~~~~
በኢትዮጵያ ህዝብ ወኪሎች ፊት ቀርቦ አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀ ቡድን ጋር መንግስታዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረግ ከአሸባሪዎች አገር የማፍረስ ዓላማ እና ፍላጎት አይተናነስም። ከአሁን በሗላ በአማራ ህዝብ የህልውና ላይ ሒሳብ ለማወራረድ የሚሞክር መንግሥታዊም ይሁን አሸባር ቡድን ካለ ራሱ ይዋረዳል።
በመንግስት በኩል በቅርቡ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የትህነግ ቡድን በአገር ላይ በፈጸመው ግፍና ክደት ምክንያት የአገር መከላከያ ሰራዊት እና የአማራ ልዩ ሐይል በወሰዱት ኦፕሬሽን ከአማራ ታሪካዊ ግዛት ከሆኑት ወልቃይት ጠገዴ ፣ ጠለምትና ራያ ማጽዳት ተችሏል።  በተወደሰደው እርምጃም በርካታ ጉምቱ አባላቱ ድፋቅ ተመተዋል። ላይመለሱ አሸልበዋል።
በተለይም አሸባሪው የትህነግ ቡድን በሀገር ላይ ከፈጸመው ግፍ በተለየ ሁኔታ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ አማራ ህዝብ ላይ ለዘመናት ሲፈጽም የኖረው ግፍና በደል በዚህ መለስ የሚባል አይደለም። ታሪክ ይቅር የማይለው ሰባዊና ቁሳዊ በደል ፈጽሟል። ጋራ ሸንተረሮች ሁሉ ሰባዊ አጽም እንዲከማችባቸው አድርጓል።
የአማራ ህዝብ ለዘመናት ተጭኖበት ከነበረው መከራና ግፍ ለመላቀቅ ተመን የለሽ መስዕዋትነት ከፍሏል። ለነጻነቱ ሲልም በከፈልነው ዋጋ ላይ ሒሳብ ለማወራረድ የሚሞክር አካል ካለ ጠባችን ከአሸባሪ የትህነግ ቡድን ጋር ብቻ ሳይሆን ስምምነት ከፈጸመው አካል ጋር ጭምር ነው።
ምክኒያቱም በኢትዮጵያ ህዝብ ወኪሎች ፊት ቀርቦ አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀ ቡድን ጋር መንግስታዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረግ ከአሸባሪዎች አገር የማፍረስ ዓላማ እና ፍላጎት አይተናነስም!
የአማራ ህዝብ መረዳት ያለበት ነባራዊ ሀቅና እውነታ ከራሱ ታሪካዊ ግዛት ከሆኑት ወልቃይት ጠገዴ ፣ ጠለምትና ራያ ተከዜን ተሻግሮ የሚመጣ ቡድን በእኛ በመላው የአማራ ህዝብ መቃብር ላይ መሆኑን ነው።
ለአማራ ህዝብ ነጻነት ሲባል ሚሊዮን አማራዎች ተገለዋል ፣ ሚሊዮኖች ደግሞ ተፈናቅለዋል። በሚሊዮን ወገኖቹ መስዋትነት ነፃነቱን ያረጋገጠው የወልቃይት ጠገዴ ፣ ጠለምትና ራያ አማራ ህዝብ ህልውና በጋራ ትግላችን ነጻነቱን አውጀዋል። በማንም የግልና የቡድን ፍላጎት ሳይሆን ለዘመናት ተነጥቆ ታፍኖና ተጨቁኖ ከኖረበት ግፍና በደል ተላቆ አማራነቱን በአደባባይ አውጇል። የማንንም ይሁንታ አይጠይቅም ፤ አያስፈቅድም።
በእኛ እና በመላ የአማራ ህዝብ መቃብር ላይ ካልሆነ ዳግም ከእንደዚህ ቀደሙ ሁሉ “ተከዜን” የሚሻገር አንዳች የትህነግ አሻባሪ ቡድን አይኖርም። ሊኖርም አይችልም።
Filed in: Amharic