>

ከአምስት ቀን በፊት በሌሊት ከቤታቸው ታፍነው የተወሰዱት  ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ ያሉበት አልታወቀም፤ ፍርድ ቤትም አላቀረቧቸውም...!!! (ጌጥዬ ያለው)

ከአምስት ቀን በፊት በሌሊት ከቤታቸው ታፍነው የተወሰዱት  ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ ያሉበት አልታወቀም፤ ፍርድ ቤትም አላቀረቧቸውም…!!!

ጌጥዬ ያለው 

ከአንባገነናዊነት ወደ ለየለት ውንብድና የተሸጋገረው የአብይ አሕመድ መንግሥት ጋሽ ታዴዎስ ታንቱን ከአምስት ቀን በፊት አፍኖ እንደወሰዳቸው የደረሱበት አልታወቀም። ሰኔ 25 ለ26 አጥቢያ በሌሊት ከእንቅልፋቸው ተቀስቅሰው በፖሊስ ተወሰዱ። ባለቤታቸውና ሕፃናት ልጆቻቸው በየፖሊስ ጣቢያው ቢንከራተቱም አላገኟቸውም። በየፍርድ ቤቱ ተቀምጠው ሲጠብቁ ይውላሉ፤ ነገር ግን አዛወንቱ ጋዜጠኛ አልቀረቡም። አላገኟቸውም። ተጨንቀዋል።

Filed in: Amharic