>

በአጤ ዮሐንስም ሆነ በአቶ መለስ ላይ ካንተ በላይ ክህዴት የፈጸመ የታሪክ ሌባ አለ እንዴ? (አሳዬ ደርቤ)

በአጤ ዮሐንስም ሆነ በአቶ መለስ ላይ ካንተ በላይ ክህዴት የፈጸመ የታሪክ ሌባ አለ እንዴ?

አሳዬ ደርቤ

*…..  እኛ ‹‹ኢትዮጵያ እናትህ፣ ሚስትህ፣ ልጅህ ናት…›› የሚለውን የአጼ ዮሐንስ አስተምህሮ ወርሰን ኢትዮጵያን ‹‹እናቴ›› ስንላት አንተ ግን ‹‹ጠላቴ›› ብለህ ፍርሰቷን ትመኛለህ፡፡ 
– ንጉሡ የተዋጋላትን እና ሕይወቱን የሰጣትን አገር ክደህ የንጉሡን አንገት ከቆረጠችው አገር ጋር አንገት ለአንገት ተቃቅፈህ ትወጋታለህ፡፡ 
– አጼ ዮሐንስ በስናይዳር እየቆላ ድባቅ ሲመታት በኖረችው አገር አገርህን ለማስጠቃት ከምሥር ጋር ታሤራለህ፡፡
–  አገር ሲቀልስ በኖረው በራስ አሉላ ሥም የአገር ማፍረስ ዘመቻህን ትሰይማለህ….
 
የአማራ ሕዝብ እንደ አገር የተሠራን ገድል ‹‹የእኛ›› ብሎ ከመቀበል ባለፈ የእኔ እና የአንተ እያለ የሚደለድል ሕዝብ አይደለም፡፡ ለብቻው ከተሰጠው ታሪክ በተጨማሪ እንደ አገር የሚጋራው ገድል ያለው ሕዝብ ደግሞ የታሪክ እጥረት ስለማያጋጥመው የታሪክ ስርቆት ውስጥ አይገባም፡፡
በመሆኑም ‹‹አክሱም የኔ ነው›› ስትለው ‹‹የእኛ ነው›› ብሎህ ታቦቱን ሊሳለም ይመጣል፡፡ ሐውልቱን ይኮራበታል ፡፡ ደብረ ሊባኖስን ይመንንበታል፡፡ ቁልቢን ይሳልበታል፡፡ አልነጃሽን ይሰግድበታል፡፡
አንተ አጼ ምኒልክ ያልቆረጠውን ጡት ፍለጋ የታሪክ ድርሳናትን ስታገላብጥ፣ እሱ ከአጼ ዮሐንስ ታሪክ ላይ ስለ ሽንፈቱ እና ስለ አንገቱ የሚያወራውን አንቀጽ መሰረዝ ያምረዋል፡፡ ሽንፈትህን እንደ ሽንፈቱ፣ ድልህን እንደ ድሉ ቆጥሮ ተሸነፍን ወይም ደግሞ አሸነፍን ይልኻል፡፡
.
ሌላውን ተወውና ስለ አጼ ዮሐንስ እና ስለ መለስ ብናወራ እንኳን…  ‹‹የብቻዬ ናቸው›› እያልክ ከምታናፋው ከአንተ ይልቅ በእኛ ልብ ውስጥ በጎ ታሪካቸውም ሆነ አስተምህሯቸው ነፍስ ዘርቶ ታገኘዋለህ፡፡
በመሆኑም…
እኛ ‹‹ኢትዮጵያ እናትህ፣ ሚስትህ፣ ልጂህ ናት…›› የሚለውን የአጼ ዮሐንስ አስተምህሮ ወርሰን ኢትዮጵያን ‹‹እናቴ›› ስንላት አንተ ግን ‹‹ጠላቴ›› ብለህ ፍርሰቷን ትመኛለህ፡፡ ንጉሡ የተዋጋላትን እና ሕይወቱን የሰጣትን አገር ክዴህ የንጉሡን አንገት ከቆረጠችው አገር ጋር አንገት ለአንገት ተቃቅፈህ ትወጋታለህ፡፡ አጼ ዮሐንስ በስናይዳር እየቆላ ድባቅ ሲመታት በኖረችው አገር አገርህን ለማስጠቃት ከምሥር ጋር ታሤራለህ፡፡ አገር ሲቀልስ በኖረው በራስ አሉላ ሥም የአገር ማፍረስ ዘመቻህን ትሰይማለህ፡፡
.
ስለ መለስ ዜናዊም በግሌ ሳስብ ኢትዮጵያን በዘር መከፋፈሉን እና አማራ ጠል መሆኑን ጠንቅቄ ባውቅም ያደረጋቸውን መልካም ነገሮች ግን ልክዳቸው አልችልም፡፡ ስለሆነም በውጩ ማሕበረሰብ ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት ያላት አገር በመፍጠሩና የዓባይን ግድብ በማስጀመሩ አደንቀዋለሁ፡፡ በአጼ ምኒልክ ዘመን የተፈረመውን የቅኝ ግዛት ውልም ድባቅ የመታበትን ሎጂክ ልረሳው አልችልም፡፡
የአማራ ሕዝብም በመለስ ዘመን ከተደረገበት ይልቅ የተደረገለትን በማሰብ ሲሞት ከማልቀሱም በላይ ያስጀመረውን ግድብም ‹‹እንደጀመርን እንጨርሰዋለን›› በሚል አስተሳሰብ ለአሥር ዓመታት ያህል ግብጽን በንቃት እየተጠባበቀ ቦንድ ሲገዛ ኑሯል፡፡
-ያንተው ሜቴክ ግን መለስ ሲሞት ፕሮጀክቱን ትቶ በጀቱን ጨርሶት አረፈ፡፡
-ያንተው ህውሓት ግን የመለስን ሕልም በማሳካት ፈንታ ግድቡን በማጓተት የሥልጣን ቆይታዋን ታረዝምበት ያዘች፡፡
እኛ አማራዎች ስንገደልበት በከረምነው ክልል ውስጥ የተሠራው ግድብ ውሃ መያዙን ሰምተን ደስታችንን ስንገልጽ፣ ሲገድለን የከረመው ያንተው ኦነግ ግን ከግብጽ ጋር ተባብሮ ግድቡን ለማስተጓጎልና የኦሮሞ ተወላጅ የሆነውን ጠ/ሚር ለመፈንቀል እየተፍገመገመ ነው፡፡
እኛ አማራዎች የትግራይ ተወላጅ በሆነው ጠ/ሚኒስትር ተጀምሮ በዶክተር ዐቢይ ዘመን በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን ግድብ በኢትዮጵያ እሳቤ ተጋርተን ግድቡንም ሆነ መሪዎቹን የእኛ በማለት ደስታችንን ስንገልጽ ያንተው ትሕነግ ግን የመለስን ግድብ የሚደበድብ የአልሲሲን ቦምብ አንጋጦ እየተመለከተ ነው፡፡
የእኛ ዲያስፖራዎች የጸጥታው ምክር ቤት ለግብጽ ወግኖ አገራቸው ላይ ማዕቀብ እንዳይጥል ሲሟገቱ ያንተዎቹ ግን ስለ መለስ ግድብም ሆነ የእርዳታ ስንዴ ስለሚጠብቀው ሕዝብ ማሰብ ተስኗቸው በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል እየወተወቱ ነው፡፡
እናስ አቶ መለስንም ሆነ አጼ ዮሐንስን፣ አገራቸውንም ሆነ ታሪካቸውን የካድክ አንተ ወይስ እኛ?
በሥማቸው እና በብሔራቸው ከመኩራት ባለፈ የትኛውን በጎ ሕልማቸውን ወይም ደግሞ ታሪካቸውን ወርሰህ ነው ታሪክህን የምንሰርቅህ?
Filed in: Amharic