>

አሜሪካ ግብጽና አባይ ....!!!! (ፍትህ)

አ ሜሪካ ግብጽና አባይ ….!!!!

ፍትህ

አሜሪካ በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያን ለምን ማዋከብ ፈለገች?
ሁለተኛው የአለም ጦርነት መገባደጃ አከባቢ 1945 እኤአ አገረ እስራኤል ትመሰረታለች። በዚህ የእስራኤል መመስረት አለም በድጋፍና በተቃውሞ ለሁለት ጎራ ተከፈለ።
 በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ወቅት ጃንሆይ ዘሬ ከእስራኤል ነው ቢሉም ድጋፋቸውን ግን ለፍልስጤም ሰጡ።
ይህም ቢሆን የእስራኤል ጠላት ሆና ብቅ ያለችው ግብጽ እንጂ ኢትዮጵያ ያን ያህል አደጋ አልነበረችም።
 ስለዚህ አሜሪካ በማግስቱ ኢትዮጵያ መጣች።
ዋና አላማዋም ጃንሆይ የአባይን ግድብ እንዲሠሩ ማግባባት ነበር።
በ1952ዓ.ም አሜሪካ በራሷ ድርጅት (United States Reclamation services ) በኩል በ10ሚሊዮን ዶላር ግድቡ የጥናት ስራው ተጠናቀቀ።
ከጥናቱ በኋላ የግንባታውን ማስጀመሪያ IMF እንደሚችል ተስማሙ።
ነገር ግን በአመቱ 1953 ላይ በኢትዮጵያ የግብጹ ሳዳት እጅ አለበት  የሚባለውን የታህሳሱን ግርግር አስተናገደች።
 የግድቡ ጉዳይም ከግርማሜ ነዋይና ከመንግስቱ ነዋይ ጋር አብሮ መቃብር የገባ ያህል ተረሳ።
በ1967 መባቻ ስልጣን የያዘው ደርግ ምንም እንኳ ኮሚኒስት ቢሆንም እስከ የዚያድ ባሬ ጦርነት ድረስ የእስራኤልና አሜሪካ  እንክብካቤ አልተለየውም ነበር።
ጭራሽ በ1971 እስራኤል ውድና ዘመናዊ ማሽኖቿን ጭና ጎጃም በመግባት ለኢትዮጵያ ትልልቅ ግድቦችን ለመገንባት ቅደመ ዝግጅት ስራዎችን ጀመረች።
ይሄንን ጉዳይ የአሜሪካ ዜና አውታሮች እስከ 7ኛው ሰማይ አጮኹት።
 በዚህ ብርክ የያዛት ግብጽ በማግስቱ ልዑኳን ይዛ ዋሽንግተን ገባች።
አሜሪካንን “እባክሽን እስራኤልን ከኢትዮጵያ ውጭ በይልን” ብለው እግሯ ስር ወደቁ።
አሜሪካም ትጠብቀው የነበረው ጉዳይ ስለሆነ እጇን ስማ ተቀበለችና ቅድመ ሁኔታ አስቀመጠች።
 አሜሪካም “እስራኤል ጋር አደራድራችኋለሁ; ግን አገር የሚደራደረው ከአገር ጋር ነውና የእስራኤልን አገርነት ቅድሚያ ተቀበይ” አለች።
በአረቡ አለምና በአባይ ውሃ መሀል የምትዋልለው ግብጽም ለ12ቀናት በካምፕ ዴቪድ ለ12ቀናት ወሸባ ገባች።
 ከ12ቀናት በኋላ ጀሚ ካርተር በመሀል፣ የግብጹ ፕሬዚዳንት አኗር ሳዳት በግራ የእስራኤሉ ጠ/ሚ መንቼም ቤጊን በቀኝ በኩል ሆነው ከሚስጥራዊው አዳራሽ ወጥተው ለአለም ታዩ።
 ይህ ሚስጥራዊ ስምምነትም Camp David Accordsን ወለደ።
በዚህ ስምምነት መሠረት
1. ግብጽ እስራኤልን እንደ አገር ተቀበለች።
በአረቡ አለም ለመጀመሪያ ጊዜ የእስራኤል ካርታ በግብጽ ታተመ።
 በምትኩ ፍልስጤም የምትባል አገር በግብጽ ምድር በሚገኙ የአለም ካርታዎች ላይ ተሰረዘች።
2. ግብጽ እስራኤልን እንደ አገር መቀበል ብቻ ሳይሆን የእስራኤልን interest የመጠበቅ በተለይም በጋዛ በኩል ያለውን መግቢያ የመጠበቅ ግዴታን ፈረመች።
3. በሌላ በኩል አሜሪካ ኢትዮጵያ አባይ ላይ ግድብ እንዳትገድብ እንደምታደርግ ፊርማዋን አስቀመጠች።
በወቅቱ የእስራኤል ታላላቅ ማሽኖች ከጎጃም ምደር ለቀው እስራኤል የገቡት ገና መሪዎቹ ስምምነቱን ጨርሰው ሻይ ቡና በሚልበት ወቅት ነበር።
ይሄ እንግዲህ 24ሰዓት ኢትዮጵያ ላይ የምታላዝነው አሜሪካ የመጀመሪያውና ዋናው ምክንያቷ እንጂ እውነት ለትግራይ ህዝብ አስባ አይደለም።
Filed in: Amharic