>

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጡት ማብራሪያ ...!!

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች …!!
• ባለፉት ስምንት ወራት መንግስት ተገዶ በገባበት የህግ ማስከበር እንቅስቃሴ በዜጎች ህይወት ንብረትና የሀገር ገፅታ ላይ የደረሰው ጉዳት ግዙፍ እንደሆነ ይታወቃል፤
–  መንግስት ተጨማሪ ኪሳራንና የህዝብ ጉዳትና እልቂትን ለማስቀረት ሲባል መሰረቱን ሰብአዊነት ላይ ያደረገ ነገር ግን ሌሎችንም ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የሀገር ሉአላዊነት ላይ የተደቀኑ አደጋዎዎችን ግምት ውስጥ ያስገቡና ተያይዥነት ያላቸውን ምክንያቶች ታሳቢ ያደረገ የተናጥል የተኩስ አቁም አውጇል፤
– ይህንንም ተከትሎ ሰራዊቱን ከግጭቱ አከባቢ አስወጥቷል፤
– በዚህም ምክንያት አታጅቡን አትከተሉን እኛው በተመቸን መንገድ ተንቀሳቅሰን ለብቻችን ሆነን እርዳታ ማድረስ አለብን የሚል ውትወታ ሲያካሄዱ ለነበሩ አካላት እድል ሰጥቷል፤
 – የፍተሻ ኬላዎች ይነሱልን በፍተሸ የሚስተጓጎል ሰዓት አይኑር ምን እንደያዝንም ማንን እንደጫንም ለማወቅ አትሞክሩ ነፃ አድርጋችሁ ልቀቁን በሚል በርካታ ግፊቶችን ሲያካሄዱ ለነበሩ መልስ ሆኗል፤
– ግጭቱን ጋብ በማድረግ የተኩስ አቁም ወስኑና ዕርዳታ በቀላሉ ማድረስ የሚቻልበት ሁኔታ ይፈጠር አርሶ አደሩም ይረስ ሲሉ ለነበሩም ምልሽ ሆኗል፤
– አዝመራውና የእርሻው ጊዜ ካለፈ ረሀብን እንደመሳሪያ ተጠቅማችሁዋል ብለን እንከሳችኋለንና አዝመራው ሳያልፍ የእርሻው ጊዜ ሳይስተጓጎል ተኩስ አቁማችሁ አርሶ አደሩ ማረስ የሚችልበት ዕድል መፈጠር አለበት የሚል ውትወታ ሲያካሄዱ ለነበሩም ውሳኔው ይጠቅማል፤
– ዋናው ምክንያታቸው ዋናው መሻታቸው ዋናው ፍላጎታቸው ምንም ይሁን ምን እነዚህን ጉዳዮቻቸውን በተለያዩ የዓለም አደባባዮች በተናጠልም በጋራም ሲያስተጋቡ ለነበሩ አካላት ምላሽ የሚሆን ነበር ተብሎ ይታሰባል፤
– በእርግጥም ለህዝቡና ለኢትዮጵያ ደህንነት መረጋጋት ተጨንቀው ለነበሩት ደግሞ እፎይታ የሚሰጥ ፣ የሚያስፈግግ አዎንታዊ ውሳኔ ነበር ተብሎ ይታመናል፤
– ነገር ግን መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም ቢያደርግም ህወሓት አሁንም ግጭቱን በአፋርም በአማራ በኩልም ለማስፋት የሚያደርገው እንቅሰቃሴዎችን ምዕራባዊያን ሚዲያዎች ለማገጋለጥ የሚያደርጉት ጥረት አነስተኛ ነው፤
– መንግስት ተኩስ አቁሞ ከአካባቢው የወጣው ለህዝቡም እረፍት ለሰላምም እድል ለመስጠት እንጂ የግጭት አካባቢ ለመቀየር አልነበረም፤
– ይህ ሁኔታ በግላጭ እየታየ ባለበት ሁኔታ ሁላችንም ስንወተውት የነበረውን የተኩስ ማቆም  ለህዝብ እፎይታ የመስጠት ርዳታ ለማድረስ የሚያስችል መደላድልን ይጎዳልና መቆም አለበት የሚል አከካል ብዙም አለመሆኑ በርግጥም ግጭቱ እንዲቆም ይፈለጋል ወይ የሚል ጥያቄ መንግስት እንዲያነሳ አስገድዶታል፤
– የሰብአዊ ድጋፍ እናቀርባለን እናስተባብራለን የሚሉ አካላት የሚያቀርቧቸው የነበሩ ጥያቄዎች በሙሉ  ተመልሰውላቸው አሁንም መንግስት በአካባቢው በነበረበት ወቅት ያነሷቸው የነበሩ ስሞታዎችን እያቀረቡ መሆኑን ስንመለከት መጀመሪያም ቢሆን ችግሩ መንግስት ነበረ ወይ የሚለውን ጥያቄ እንድናነሳ አስገድዶናል፤
– መንግስት በረራ ፈቅዶ በረራ ታግዷል ይላሉ፤ ርዳታ የሚገባበት መስመር ተመቻችቶ ርዳታ አልገባም ይላሉ፤
– አንድ አንድ የአውሮፓ አገራትና ግለሰብ ባለስልጣናት ጉዳዩ የግላቸው እስከሚስል ድረስ በጣም የግል ጉዳይ አድርገው በኢትዮጵያ ላይ ጫና ማሳደሩን ቀጥለውበታል፤
– አንድ አንድ ድርጅቶች አገር ውስጥ ሆነው ርዳታ እንዲያስተባብሩ ከመደቧቸው ግለሰቦች ውጭ በርቀት ሆነው ከርዳታ ይልቅ ፕሮፖጋንዳ የማስተባበር ኢትዮጵያን የማዋከብና የማጠልሸት ስራ እየሰሩ ነው፤
– ይህንን አስጠንቅቀናል፤ የማይታረም ከሆነ የራሳችንን ርምጃ እንወስዳለን፤ አንድ አንዶችንም ከአገር ለማስወጣት እንገደዳለን፤
– ከኢትዮጵያ ጎን ሆነው እወነታውን ተረድተው ለዓለም እያስረዱ ላሉ አንድ አንድ አገራት በተቃራኒው የሚሄዱበት መንገድ አይጠቅምም ብለው የሚሟገቱ ወዳጅ አገራትን መንግስት ያመሰግናል፤
Filed in: Amharic