የፕሬዝዳንቱ ንግግርና የአማርኛ አንድምታው !
ሱሌማን አብደላ
በመጀመሪያ ደረጃ ሲሲ በምስራቅ አፍሪካ አሉ ከሚባሉ የፖለቲካ ቃል መርጦ ተናጋሪ መሪዎች ውስጥ ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል!
ሰውየው ትናንት ከ700ሺ ሰው በላይ በታደሙበት ያደረገው ንግግር የሰላም ቃል ያላቸው ነገር ግን ንግግሮቹ እርስበርስ የሚጣረሱ የፖለቲካ «.ማሰሪያ ቋንቋን መሰረት ያደረጉ ናቸው.»!
.
1) የሰላም ቃል መሳይ
ለኢትዮጵያና ሱዳን ወንድሞቻችን «ኑ »
ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት እንፈራረምና በሰላም አብረን ተከባብረን እንበልፅግ አለ። እዚህ ላይ ሰውየው መናገር የፈለገው አስገዳጅ የሆነ ህጋዊ ስምምነት እናድርግ የምትለዋ ግብፆች ኢትዮጵያ ከአባይ ግድብ ውጭ ሌላ ግድብ ልማት እንዳታለማ ትፈርምልን የሚሉት አሁን ከኢትዮጵያ ጋር የሚጨቃጨቁበት ሰነዳቸው ነው። ስለዚህ የሰውየው ንግግር አሁንም በቅኝ ግዛት ሰነድ ላሉየተመረኮዘ ኢትዮጵያ ወደፊት የአባይን ወንዝ ለፈገለችው አላማ እንዳትጠቀም የሚያስር ስምምነት ከመፈለግ የመነጨ ነው ማለት ነው።
2) ለማስፈራራት ሲፈልግ
የግብፅን ብሔራዊ ደህንነት ጥሸ እንደፈለኩ እጋልባለሁ ማለት « ቀይ መስመር መሻገር ነው .! ምን ማለቱ ነው
ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት ላይ ካልደረስን
የግብፅን ብሔራዊ ደህንነት መጣስ ስለሆነ እርምጃ እንወስዳለን ማለቱ ነው!
3 ድንፋታ
በቀጠናው ላለው ነገር ጠንካራ የፖለቲካ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ፍላጎቶቻችንን የሚያሳካና አቅማችንን የሚጠብቅ ሀይል አለን! ምን ማለቱ ነው የውሀ ደህንነታችንን ለመጠበቅ፣ የፖለቲካ ኢኮኖሚያዊ ፍላጎታችንን ለማስፈጸም፣ በቀጠናው ጠንካራ የሆነ ወታደራዊ ሀይል አለን
4 ( ለህዝቡ ቃል ሲገባ
ወድ የግብፅ ህዝቦች ይሄ ሁሉ የምላችሁ ነገር ካልተሳካ፣ ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ነገር ቢሆኖር በግብፅ ላይ ምንም አይነት ብሔራዊ ስጋት የሚከሰት ከሆነ፣ እኔና የግብፅ ሠራዊት መጀመሪያ መሰዋት ሆነን ነው ይሄ ነገር የሚፈፀመው !
5) ህዝቡን ሲያረጋጋ
ግብፅ ታላቅ ሀገር ነች እናም እኛ እንደ ግብፅ መጨነቅ መፍራት ባህላችን አይደለም! ጥሬ ቃሉ ጦርነትን ፈርተን ጥቅማችንን አሳልፈን የምንሰጥ ህዝቦች አይደለንም ማለቱ ነው
.
6)ሰላም ፈላጊ መሆኑን ለማሳወቅ ሲፈልግ
በዘመናችን የማንንም አገር አስፈራርተንና እላፊ ቃላቶችን ተቅመን አናውቅም። ከላይ እንደፃፉኩት ማስፈራሪያ ማስጠንቀቂያ የሚመስሉ ቃላቶችን እንደፈለገ ሲናገር ነበር ! ( አቋም የለሽ )
7) ስለ አባይ ውሀ ደህነነት
አንድ ጠብታ ውሃ እንዳይባክን ቢሊዮን ጂኔ (ጂኔ ማለት የግብፅ የገንዘብ ስም ነው)
በጅተን ወደ ስራ ገብተናል ! ኢትዮጵያ በየ አመቱ የአባይ ውሀ የዝናብ እጥረትንና የጎርፍ ደለልን ለመከላከል ሚሊዮን ዶላር ወጭ እንደምታደርግ ስለሚያውቅ እነሱም ተመሳሳይ ስራ እንደሚሰሩ ለመግለፅ ፈልጎ ነው። በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ለዚህ የጉልበት ብዝበዛዋ ከግብፅና ሱዳን 40 ቢሊዮን ዶላር ካሳ መጠየቅ አለባት የሚል በኢትዮጵያ ሙህራኖች ሀሳብ ከተሰነዘረ ቡሀላ ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን መርሳት የለብንም !
8) ስለ ህዳሴው ግድብ ድርድር
ጉዳዩን ወደ ፀጥታው ም / ቤት የወሰድነው የህዳሴ ግድብን ቀውስ ባለማቀፉ ማህበረሰብ ልብ ውስጥ አጀንዳ ለማድረግ ነበር። እዚህ ላይ በድርድር ምንም ውጤት አላስገኘንማ ማለቱ ነው !
9) ልማት ፈላጊ መሆኑን ለማሳወቅ
ለህዝቦች ልማት እና ብልጽግና በሚረዳን መንገድ በኤሌክትሪክ ሃይልም ይሁን በሌሎች ልማቶች ከኢትዮጵያ ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆናችንን ባገኘነው መድረክ ለኢትዮጵያ ስናስረዳ ኖረናል!
አሁንም በዚሁ አቋማችን ፀንተን እንገኛለን !
«..ምን ማለት ፈልጎ ነው.»? በናይል ወንዝ ላይ የህዳሴ ግድቡን ብቻ ገንቡ፣ ሌላ ግን መገንባት አትችሉም። ይሄው ይበቃችኋል ይሄንኑ እንድትጠቀሙበት እንፈቅድላችኋለን
በዚህ አቋማችሁ ፀንታችሁ ፀንተን አብረን መልማት እንችላለን ማለቱ ነው.»