>

መንግስት ኦነግና ግንቦት 7ን ከአሸባሪነት እንደፋቀው ህዋሃትንም ከአሽባሪነት ያነሳዋል? ወይስ...???  (ጎዳና ያእቆብ)

መንግስት ኦነግና ግንቦት 7ን ከአሸባሪነት እንደፋቀው ህዋሃትንም ከአሽባሪነት ያነሳዋል? ወይስ…??? 

ጎዳና ያእቆብ

እኔ የምለው የፌዴራል መንግስቱ ጎረቤት ኤርትራን ከፍዬ አስገብቼ ትግራይን አውድሜአለሁ: ሴቶች ደፍሬአለሁ: ወጣቶች ካለፍርድ ገድያለሁ (እነዚህ ወንጀሎች ሁሉ በፌዴራል አቃቤ ህግና በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የታመኑ ወንጀሎች ስለሆኑና አብይ አህመድም በወንጀል ምርመራ ላይ ያሉ የሰራዊቱ አባላት አሉ ብሎ ስለማነ መረጃ ማስረጃ እንዳትሉኝ ብዬ በትህትና እጠይቃለሁ) እና መቀሌን በሻሻ አድርገናት ተልኮአችንን ጨርሰናልና እኛም የእረፍት ክፍለ ጊዜ እንውሰድ የአማራን ገበሬ ከእርሻው ላይ አንስተን አደራጅተነውና ሳናስታጥቅ እስክናሰማራ የትግራይ ገበሬ ይረስ ብለን በተናጥል የተኩስ አቁም አውጀናል ሲሉ ህዋሃት ለምን አዋጄን ተቀብሎ እስክደራጅ እጁንና እግሩን አጣጥፎ የእረፍት ክፍለ ጊዜአችንን አክብሮ ለምን አልተቀመጠም ብሎ መውቀስ ከወታደራዊ አሰራር አንፃር ሊገባኝ አልቻለም::
እኔ ጦርነት አፍቃሪ አይደልሁም:: ጦርነቱን ከጅምሩ ጀምሮ አጥብቄ ተቃውሜዋልሁ:: ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሚከስርበት እንጂ የሚያተርፍበት እንዳልሆነ ላንቃዬ እስኪላቀቅ ተናግሬአለሁ:: አማራ እንደ አማራ ይዞታው በእግ ካልተዛወረለት በስተቀር ከሞራል ድል ባለፈ በፌደራል መንግስቱ የሚካድበት ሌላ ቁማር ይሆናል ብለናል::
አሁንም ቢሆን ከመዋጋትና ከመገዳደል ይልቅ መወያየት ላይቀር ቀድሞ መነጋገር ይበጃል:: መደራደር ያስፈልጋል::
የድርድር ሁሉ መጀመሪያ መሆን ያለበት ደግሞ አለም አቀፍ የተኩስ አቁም ህግጋት መከተል ያስፈልጋል::  የንጉስ አዋጅና ውሳኔ ሳይሆን ስምምነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም መሆን አለበት:: የትውኩስ አቁሙ እስከመቼ? እንዴት ነው የሚተገበረው? ከእርሻ ባለፈ አላማው ምንድነው? ወደ ዘላቂ ሰላም ይወስዳል? ወይስ የጥሞና ጊዜው ሲያልፍ ወደጦርነት ይገባል? የጥሞና ጊዜ የሚለው ወታደራዊና ፓለቲካዊ ትርጉሙ ምንድነው? ምንን ያካትታል? ምንን አያካትትም? በጥሞና ጊዜውስ ትግራይን ማን ያስተዳድራል? ጊዜአዊ መንግስቱ ይመለሳል? ወይስ መንግስት አሸባሪ ያለው ሀይል በጥሞና ጊዜው ያስተዳድራል? ወይስ ኦነግና ግንቦት 7ን ከአሸባሪነት እንደፋቀው ህዋሃትንም ከአሽባሪነት ያነሳዋል?
በአማራ ክልል በኩል ያለው የህልውና አደጋና የጥሞና ጊዜ እንዴት ይታረቃል? የክተት አዋጅ በክልሎች በኩል የመታወጁ ነገር ባህላዊ አሰራሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ህጋዊና ህገ መንግስታዊ መሰረት አለው ወይ? የመንግስትን  የክተት አዋጅ ጥሪ ሰምቶ የወጣ ሀይል ደምወዝ ይኖረዋል? ቢሞት ወይም ቢቆስል ቤተሰቡን ማን ይንከባከብለታል? ጡረታ አለው? ህክምና ያገኛል? ትጥቅና ስንቅስ ማን ነው የሚያቀርበው? እርሻውንስ ማን ያርስለታል?
መከላከያው በተራዘመው የእረፍት ክፍለ ጊዜው ይቀጥላል? ወይስ በጦር ግንባር ይሰለፋል? ይሄ ሁሉ የጦር ዝግጅትስ ከተኩስ አቁምና ከሰላም ጥሪ ጋር እንዴት ይታረቃል? የአማራ ልዩሀይል በብርንሻንጉል ገብቶ በማንነታቸው የሚታረዱ አማራዎችን ላድን ሲል ካለ ፌደራል መንግስት ፍቃድ ወደ ቤንሻንጉል መግባት የቤንሻንጉልን ልእዋላዊነት መዳፈር ነው ብለው እንዳይገባ ታግዶ ሳለ ልዩ ሀይሎች ካለ ፌደራል መንግስት የአደባባይ ይሁንታ በአማራ ክልል ግብዣ ብቻ መግባት ና በጦርነት መሳተፍ ከህግ አንፃር አንድምታው ምንድነው? የፌደራል መንግስትስ ይሁንታውን ከሰጠ ከተኩስ አቁም ጥሪውና የጥሞና ጊዜው ጋር እንዴት ይታረቃል? እንዴት ይቃረናል?
እነዚህና ሌሎች በርካታ መልስ ያላገኙ ጥያዎች ባለበት ሁኔታ የተኩስ አቁም አዋጁ  ሲስሮ እንዳለው this is war  disguised as peace (በሰላም የተሸፈነ/የተለበጠ  ጦርነት) ነውና ግልፅ በሆነ የጋራ ስምምነት ላይ ያልተደረሰበትና በድርድር  ላይ ያልተመረኮዘን ስለሆነ በአብይ አህመድ የታወጀውን አዋጅ ፍይዳ እንዳለው የተኩስ አቁም ላየው ይቸግረኛል:: ያ ማለት ደግሞ ጦርነቱ እንደቀጠለ ነውና መከላከያው ወደ ስራው ተመልሶ ጦርነት አይደልም ህግ የማስከበር ዘመቻ እንጂ ብሏልና የአማራ ክልል ደግሞ የፌደራል መንግስትን ህግ የማስከበር ህጋዊ አመክንዬ ስለሌለ ግብር የሚሰበስበው ይህን ለመስራት ስለሆነ የፌደራል መንግስቱ መከላከያውን ልኮ ስራውን ይስራል::
ዜጎች ሲገደሉ የሰፈራችሁ ሚሊሻ አይደልውሁም:: ጦርነት ሲነሳ አማራ ብቻውን በቂ ነው የሚል ቀልደኛ ንጉስ የተናጥል የተኩስ አቁም አዋጅ አውጄአለሁ አሜን በሉልኝ ሲል ሌላ ቁማር አልበላም ስለዚህ የተኩስ አቁምን ውል ትፅፉታላችሁ! ብሎ እንቢ ማለት ህዋሀትና ጤንነትን በአንድ አረፍተ ነገር ላይ መጠቀም ቢቸግረኝም ከአራት ኪሎው እብደት ግን የሚሻል ነው እላልሁ:: ስለዚህ አማራውን ከመማገዳችሁ በፊት ውሉን ፃፉት:: የተናጥል የሚለውን ቀልድ ትታችሁ የጋራ (አማራንም የጨመረ) የተኩስ አቁም ውሉን ፃፉት::
Filed in: Amharic