አሜርካን ያስጨነቁ ሁለት ጉዳዮች – በቀላል ቋንቋ….!!!
ብርሀኑ ሌንጂሶ
አሜርካ ከኢትዮጵያ ጋር የረጅም ዓመት ድፕሎማሳዊ ግንኙነት ያላት ሀገር ነች:: መቶ ዓመታትን የተሻገረዉ የኢትዮ-አሜርካ ግንኙነት በርካታ ክደቶችንም አሰተናግዶዋ::
ለምሳሌ በ1935 እኤአ ጣልያን ኢትዮጵያን ሲትወር አሜርካ አዲስ አበባ የሚገኘዉን ፅ/ቤቷዋን ዘግታ ከመዉጣም አልፋ ሁለቱም ሀገራት ላይ የመሳሪያ ግዥ ዕቀባ ጥላለች:: በወቅቱ የተሻለ መሳሪያ የማግኘት ዕድል የነበራት ጣልያንም ኢትዮጵያን ወራ መያዝ ቻለች:: እነእንግልዝ ግን ከኢትዮጵያ ጋር እስከምጨረሻዉ ቆሙ::
በ1977/8 ሶማልያ ኢትዮጵያን ሲትወር አሜርካ ኢትዮጵያ የገዛችዉን የጦር መሳሪያ ከመከልከልም አልፋ ለሶማልያ የመሳሪያና የገንዘብ ዕርዳት በማድረግ ኢትዮጵያን አስወጋች::
ቀጥሎም ከደርግ ጋር በነበራት አለመስማማት ለ16 ዓመታት ከግብፅ ጋር በመሆን ወያኔን ጫካ ዉስጥ በመርዳት ወያኔ በትግራይ ህዝብ ላይ ይሰራ የነበረዉን ድራማ ሁሉ በመደገፍ ወደስልጣን እንድመጡ ከፍተኛ ሚና ተጫዉታለች:: በስልጣን ዘመናቸዉም ጠንካራ ደጋፊ በመሆን ቆይቶዋል:: ወያኔ ከስልጣን በመዉረዱ አሜርካ ደስተኛ እንዳልሆነች ግልፅ ነዉ::
አሜርካኖች ውያኔን የሚፈልጉበትም ሆነ አሁን ስልጣን ላይ ያለዉን መንግስት የሚያስጨንቁበት ጉዳይ አንድ ነዉ:: እነሱ የሚፈልጉት በአፍርካ ቀንድ በታማኝነት የነሱን ጥቅም የሚያስከብር መንግስት ነዉ:: ከምንም በላይ ደግሞ የአከባቢዉን ሰላምና ፀጥታ ማስከበር የሚችል ሀይል ነዉ::
የአፍርካ ቀንድ ሀገራት የሚባሉቱ ሀገሮች ኤርትሪያ, ኢትዮጵያ, ጅቡትና ሶማልያ ናቸዉ:: የአፍርካ ቀንድ የነዳጅ መንገድን (oil routes) ከማዋሰኑም በላይ የነዳጅ ሀብት ባለፀጋ ከሆነችዉ ሳዉድና ከነድጅ ማምረቻ ቦታ ያለዉ ቅርበት የአፍርካ የአዉሮፖና የኤሽያ አህጉራት መገናኛ እስፖት መሆኑ እና የባህር ሀይል ሃያላን ሀገሮች መገናኛ መሆኑ ለአሜርካም ሆነ ለሌሎች የዓለማችን ሃያል ሀገራት ቁልፍ ቦታ ያደርጎዋል:: ከሂንድ ዉቅያኖስ እስከ ቀይ ባህር እስከ ገልፍ ኦፍ ኤደን እስከ ሜደተራኒያን ዉቅያኖስ ይዘልቃል::
የዚህን አከባቢ ሰላምና ፀጥታ ማስከበር የአሜርካን ጥቅም ማስከበር ሰለሆነ በየደረጃዉ ለተለያዩ ሀገሮች ሚና ተቀምጦዋል:: ኢትዮጵያ የአፍርካ ቀንድን በበላይነት እንድትቆጣጠር ሲትመደብ ግብፅ ደግሞ የአረብ ሀገራትን ጉዳይ እንድትቆጣጠር ተቀምጣለች::
ላለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ የአፍርካን ቀንድ ለመቆጣጠር ትጠቀምበት የነበረችዉ ዘዴ ሶማያንና ኤርትሪያን እንደጠላት በመፈረጅ (check and balance) ማድረግ ነበር:: ወያኔ የአከባቢውን ሀገራት በማተራመስና በመሃከላቸዉ ስምምነት እንዳይኖር በማድረግ ለአሜርካ ጥሩ ተላላክ መሆን ችሎ ነበር:: አሜርካም በዝያ ደስተኛ ስለነበረች ሀገርቷ ዉስጥ ለነበሩ የሰበሃዊ ችግሮች እንድም ቀን ትኩረት ሳትሰጥ ሰላሳ ዓመታት አለፉ::
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደስልጣን ስመጣ ከቀየራቸውና አሜርካን ምቾት ከነሱ ነገሮች አንዱ በአፍርካ ቀንድ ሀገራት መሃከል ያለዉ ግንኙነት ነዉ:: ኢትዮጵያ እየተጣላቻቸዉ እየተዋጋቻቸዉ የአሜርካን ጥቅም እንድታስከብር ከተቀመጡ ሀገሮች ጋር ዕርቅ መፈፀሙ ነዉ:: ከሶማልያና ከኤርትሪያ ጋር ጥብቅ ወዳጅነት መፍጠሩ ነዉ:: ይሄን ደግሞ አዲሱ የአፍርካ ቀንድ ልዩ መልክተኛ ጀፊር ፍልትማን በማያሻማ ቋንቋ አስቀምጦዋል:: የሶስቱ ሀገራት መወዳጀት ጥሩ እንዳልሆነ ተናግረዋል::
ሁለተኛዉ ደግሞ ከሌላኛዋ የአሜርካ ተላላክ ሀገር ከግብፅ ጋር የተፈጠረዉ አለመግባባት ነዉ:: አሜርካ በዋናነት ያሳሰባት ግን የግብፅ የዉሃ ችግር አይደለም:: የኢትዮጵያ ራስን ችሎ ጠንካራ ሀገር ሆኖ መወጣት እንጅ:: ምናልባት ኢትዩጵያ በአፍርካ ቀንድ ላይ የነበራትን የማተራመስ ሚና ቢትቀጥል ኖሮ የአሜርካ ምላሽ በተቃራንዉ ሊሆን እንደምችል ግምት አለኝ::
ባጠቃላይ የአሜርካ ትኩረት የትግራይ ግጭትም የሰበሃዊ ቀውስም አይደለም:: አሜርካን ያሰጨነቃት ሁለት ነገር ነዉ:: ሁለቱም ጅኦፖለቲክስ (geopolitics) ናቸዉ:: ድርብ ፍራቻን ይዞላቸዉ የመጣ የጅኦፖለቲክስ ፍጥጫ::
አንደኛዉ ኢትዮጵያ በተለመደ መልኩ የአሜርካን ጥቅም ለማስከብር ከጎረበት ሀገራት ጋር ግጭትና ሹኩቻ ዉስጥ መግባት ማቆሞዋ ነዉ:: ከኤርትሪያና ከሰማሊያ ጋር መወደጀቷ ነዉ::
ሁለተኛዉ ደግም የአሜርካ ታማኝ ተላላክ የሆነችዉን ግብፅን ማስጨነቋ ነዉ:: ኢትዮጵያ በሂደትም ግብፅ በአፍርካና በአረቡ ዓለም ላይ ያላትን ሃያልነት ለመንጠቅ የሚያስችላትን እንቅስቃሰ በአባይ ወንዝ ላይ መጀመሯ ነዉ::
Now America is a in a deep shit. Her two best allies Ethiopia and Egypt are in a serious disagreements over the Ethiopian dam. America took side in mediating this disagreement and already lost her trust with Ethiopia. Ethiopia changed her policy towards her neighboring countries in the Horn of Africa from conflict as a tool of relations to cooperation between countries. This already put America in a paranoia and a source of all the pressures that American is putting on Ethiopia using the Tigray crises as a pretext.