>

"የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ፈሷል...!!!" (ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ይፋዊ መግለጫ)

“የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ፈሷል…!!!”

የዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ይፋዊ መግለጫ!!

 

<<ዛሬ ሀምሌ 12ቀን 2013 ዓ.ም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ፈሷል:: ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም እንኳን ደስ አላችሁ።
 ይህ ውጤት ማለት  2 ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን የውሃ መጠንና ይዘናል ማለት ነው:: በዘንድሮው አመት እየዘነበ ያለው ውሃ መጠን እጅግ ከፍተኛ ነው። ይህም ከፈጣሪ የተሰጠን ፀጋ ምን ያህል ትልቅ እንደህነና እንዴት እያገዘን እንደህነ መረዳት እንችላለን:: ለዚሁም ምስጋና ይግባው!
እዚህ ደረጃ ለመድረስ በዘንድሮው አመት መጠነ ሰፊ ስራ ሰርተናል:: በቀጣይ ሁለቱ ተርባይኖች እንዲያመነጩ ብርቱ ስራዎች እየተሰሩ ነው እናም ያንን በቅርብ ወራት በማጠናቀቅ ልፋታችንን ውጤት ላይ እናደርሳለን:: >>
(ከ7 ቢሊዮን ኪሜ ውሃ በላይ) ግድቡ ይዟል
#Ethiopia | በዚህ አመት ለመያዝ የታቀደው 18.4 ቢሊዬን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ቢሆንም አሁን ግድቡ ባለው ከፍታ መያዝ የሚችለው የውሃ መጠን 10 ቢሊዮን ሜኪ ይሆናል።
አሁን የግድቡ ሁለቱን ተርባይኖች ስራ ለማስጀመር የሚጠይቀ ከፍታ በላይ (የመካከለኛው ክፍል 573m በላይ) ደርሷል።
 በነሀሴ 2013 መጨረሻ ላይም ሁለቱን ተርባይኖች የሙከራ ሀይል የማመንጨት ስራ ለማስጀመር የሚያስችል የውሀ መጠን (ከ7 ቢሊዮን ኪሜ ውሃ በላይ) ግድቡ ይዟል።
Filed in: Amharic