>
5:26 pm - Wednesday September 15, 1762

"ከእንግዲህ ህወሃት ለአብይ አህመድ ስልጣን ሳይሆን፣ ለአማራ ህዝብ ብቻ ነው ስጋት ሆኖ የሚቀጥለው...!!!" (ጋዜጠኛ - ማዕዛ መሐመድ)

“ከእንግዲህ ህወሃት ለአብይ አህመድ ስልጣን ሳይሆን፣ ለአማራ ህዝብ ብቻ ነው ስጋት ሆኖ የሚቀጥለው…!!!”
ጋዜጠኛ ማዕዛ መሐመድ

ልደቱ አያሌው የተመረጠ መንግስት ሳይኖርና ከምርጫ በፊት የሽግግር መንግስት ይመስረት በማለቱ ታስሮበታል። እስክንድር ነጋ የምርጫ ዘመኑን በሁለት አመት ያሳለፈው የአዲስ አበባ አስተዳደር የባላደራ መንግስት ይቋቋም በማለቱ ትናንት ጦር እንማዘዛለን ተባለ፣ ዛሬም ታስሮበታል። ኦፌኮ እና ኦነግ ግን ያውም ከምርጫ ውጤት በሗላ በኦሮሚያ ክልል የሽግግር መንግስት አቋቁሚያለሁ ብሏል። የነካው አካል ግን የለም። ሁለት አይነት ህግ ነው በዚህ አገር ያለው።
ፌደራል መንግስት በዚህ ጦርነት ለስልጣኑ የሚያሰጋውን የህወሃት ቡድን አዳክሟል። አሁን ህወሃት ለአብይ አህመድ ስልጣን ሳይሆን ለአማራ ህዝብ ብቻ ነው ስጋት ሆኖ የሚቀጥለው። ህወሃትም ቢያንስ ወልቃይትንና ራያን  የትግራይ ክልል ሆነው እንዲቀጥሉ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳመን ላይ ይገኛሉ።
ብአዴን ግን እንደ ልማዱ ተመዝኖ አንሶ ተገኝቷል። ስምንት ወር ሙሉ የጦርነቱን ድል ወደ ፖለቲካ ድል መቀየር ተስኖት ተኝቶ ከርሟል። አሁን በድንገት መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ክልል ለቆ ይውጣ ሲባል የሚይዙት፣ የሚጨብጡት ጠፍቶባቸዋል።
Filed in: Amharic