>

"ብልጽግና ከወያኔ የወረሰዉን ዘረኝነት - የጎሳ ፖለቲካ ተሸካሚነት እራሱን ያጠፋዋል...!!!" (ሸንቁጥ አየለ)

“ብልጽግና ከወያኔ የወረሰዉን ዘረኝነት – የጎሳ ፖለቲካ ተሸካሚነት እራሱን ያጠፋዋል…!!!”
ሸንቁጥ አየለ

*…. አባይ ዘዉዱን በአስቸኳይ ፍቱት።የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀያቸዉ መልሳችሁ አቋቁሙ !!!
ለምን የተፈናቀሉ አማሮችን ቃለ መጠይቅ አደረግህ ተብሎ የታሰረዉ አባይ ዘዉዱ ጉዳይ የብልጽግና መንግስት ፈጽሞ የመዳን ተስፋ የሌለዉ ሀይል መሆኑን ያሳያል።
 የማይማረዉ የብልጽግና መንግስት ሲበዛ አሳፋሪ ወንጀሎችን አሁንም መቀጠሉ ምን ለማትረፍ አስቦ ይሆን?
 ከኦሮሚያ ተፈናቅለዉ በተለያዩ አካባቢዎች የተበተኑ አማሮች እጅግ ብዙ ናቸዉ። የተወሰኑት አሁን ድረስ በአዉቶቢስ ተራ ተበትነዉ ይገኛሉ።
 የአማራ ሚዲያ ማእከል ጋዜጠኛ አባይ ዘዉዱ እነዚህን በአዉቶቡስ ተራ ተፈናቅለዉ የሚገኙ ዜጎችን ለምን ኢንተርቪዉ አደረግህ ተብሎ ታስሯል። የት እንደታሰረም አይታወቅም።
ጸረ ዲሞክራሲያዊነት፡ ዘረኝነት፡ የብሄር ፖለቲካ አደረጃጀት ፈጽሞ ከኢትዮጵያ ሳይነቀል ማንም እረፍት የለዉም።
 ብልጽግና ከወያኔ የወረሰዉን ዘረኝነት ፡ ጸረ ዲሞክራሲያዊነት፡ የጎሳ ፖለቲካን ካንሰር ተሸካሚነት እራሱን አንቆ ይገለዋል።
አባይ ዘዉዱን የመሳሰሉ እዉነት ላይ የቆሙ እዉነተኛ የህዝብ ልጆች ግን እንደ ጨረቃ ገና በህዝብ ዘንድ ይፈካሉ እንጂ ዘረኞች እንደሚያስቡት የህዝብን ድምጽ ማፈን አይችሉም።
 አባይ ዘዉዱን በአስቸኳይ ፍቱት።የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀያቸዉ መልሳችሁ አቋቁሙ።
ፍትህ አንድነት ነጻነት እኩልነት እና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያዉያን ሁሉ ይሁን።
 ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይጠብቃት!
Filed in: Amharic