ሰለሞን አለምነህ
*…. ፈጣሪያቸውን መፍራት ቢችሉማ እምባገነን አይሆኑም ነበር ።
~~~~~~
ህውሀት-ኢሀዴግ በአብዬታዊ- ዲሞክራሲ መርህ መሰረት በለስ በቀናት እና ስልጣን ላይ ከቆየችበት ጊዜ ኢትዮጲያውያንን ገድላለች ! አፈናቅላለች ! አሰድዳለች ! ደፍራለች ! ዘርፋለች ! አሳብዳለች ! የግፍን ሁሉ ጥግ ፈፅማለች ! ይሄን ሁሉ ፈፅማ ህውሀት-ኢሀዴግ ማንም አልጠየቃትም ። ልጇ የሆነው ተረኛውም ኦህዴድ-ብል()ግና ከአባቱ የተማረውን ሁሉ ግፍ በመደመር ስሁት አስተሳሰብ በኢትዮጲያውየን ላይ እየፈፀመ ይገኛል ! ይሄን ሁሉ በአባት እና ልጅ የተፈፀመውን በደለ ፤ ግፍ እና መከራ ተቀብሎ ለህዝብ ያጋለጠ እና መስዋት ሆኖ ያረጋገጠ ብቸኛው ሰው የማይበገረው እና የማይሰበረው #እስክንድር_ነጋ ብቻ እና ብቻ ነው ።
ዛሬም እስክንድር ነጋ እና ደቀ መዝሙሮቹ በቂሊንጦ እና በቃሊቲ እስር ቤት ስለ #ዲሞክራሲ ስለ #ፍትሕ ስለ #እኩልነት ሲሉ ዋጋ እየከፈሉ እና እየታገሉ ይገኛሉ ። ነፃነት በነፃ አይገኝም ! በአላማ ቁሞ ዋጋ መክፈልን ይጠይቃል ! እራስን ለህዝብ ሲባል አሳልፎ መስጠት ግድ ይላል ! አምባገነኖች ከፈጣሪ በታች የሚፈሩት ነገር #ሀሳብ ያላቸውን #በብዕር የሚታገሉትን እና #ሰላማዊ ታጋዬችን ነው ! ለዚህም ማረጋገጫ ከሚሆኑት አንዱ እና ዋነኛው የእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ነው ። ፊት ለፊትም አሸንፈዋል ! እስር ቤት ሆናውም አሸንፈዋል ! በምርጫ ተወዳድሮም አሸንፈዋል ! ዛሬም መሪያችን እስክንድር ነጋ ድል ለዲሞክራሲ ይላል ! እኛም ድል ለዲሞክራሲ ብለናል ! መዳረሻችን ዲሞክራሲ ፍትሕ እና እኩልነት ነውና ።
ድል ለዲሞክራሲ
” የእስክንድር ነጋ የመንፈስ ልጆች ፍትሕ አፈላላጊ ! “