>

በቅሎ ገመዱን በጠሰ ሲባል እንጀራው አሳጠረ ይባላል! (ታጠቅ መ.ዙርጋ)

በቅሎ ገመዱን በጠሰ ሲባል እንጀራው አሳጠረ ይባላል!

ታጠቅ መ.ዙርጋ


ማሳሰቢያ ፦ በዚህ ጽሁፍ  እንግሊዝኛ የተጠቀምኩበት ክፍል አለ ። ከቋንቋዬ እንግሊዝኛውን አስበልጬ ወይም መርጬ ሳይሆን ፤ ይህ ለመጻፍ ምክንያት የሆኑኝ ወጣቶች  ሃሳብና አስተያየት እነሱ በተጠቀሙ በት ቋንቋ ማስፈር/መጻፍ  ግድ ስለሆነብኝ ነው ።

የአርእስቱ ትርጉም  አማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው  ለሆኑትና የአማርኛ ተረትና ምሳሌ ለመማር ዕድሉን ለገጠማቸው ሁሉ ግልጽ ቢሆንም ፤ አባባሉ በተግባር ስላለፍኩበት ትንሽ ባፍታታው የበለጠ ግልጽ ይሆናል ።

እኔ በበዘልማዳዊ ግብርናና ከብት እርባታ ልማድ ውስጥ ተወልጄ ያደኩ ሰው ነኝ ።አባቴ በተለያየ ወቅት የተለያዩ ቁመት ፡ መልክና ጉልበት ያላቸው በቅሎዎች ነበሩት ። ያለ ልጓምና ኮርቻ  በገመድ ብቻ ለጉሜ  ዘልዬ ሌጣ ጀርባቸው ላይ በመውጣት እየጋለብኩ  ወንዝ ወስጄ ውሃ ካጠጣኋቸው በኋላ እየጋለብኩ  ወደ ቤት እመለስ ነበር ።

የአባቴ በቅሎዎች ተሰክለው ማለት አንድ የኋላና አንድ የፊት እግራቸው ላላ ተደርጎ ታስሮ ካልተለቀቁ ፤ አንዱን የፊት እግራቸው ወይም  ከአፍንጫቸው ከፍ ብሎ  በረዥም ገመድ ከጠንካራ እንጨት ፣ ዛፍ ወይም ችካል  ታስረው ሳር እንዲግጡ ይደረግ ነበር ። በሆነ ምክንያት ደንብረው ወይም  እንደ ቀድሞ ትህነጎችና  እንደ አሁኑ  ዴያስፖራ ወያኔዎች ጠግበው ሲፈነጩ የታሰሩበት ገመድ በበጠሱ ቁጥር ገመዱ እያጠረ ስለሚሄድ  ሳይጠግቡ ነበር ወደ በረታቸው የሚገቡት ። ለጽሁፌ ይህ አርእስት የሰጠሁበት ምክንያት ከታች ታገኙታላችሁ ።

ከሁለት ሳምንታት  በፊት የኢትዮጵያ መከላኬያ ሃይል ከትግራይ ዋና ዋና ከተማዎችን ለቆ መውጣትን  ተከትሎ የትግራይ ተወላጅ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን — ከኋላቸው ክፍት የሆኑ መኪናዎች በመከራየትና በመግዛት ባንድራቸውን ይዘውና ጥሩምባ ገዝተው  ፣ በምንኖርባቸው  የባዕዳን አገራት ዋና ዋና እና  የመንደር ከተማዎች በመዞር – ‘Tigraye is liberated from Ethiopia  ! ትግራይ ከኢትዮጵያ  ነጻ ወጣ  !’ እያሉ ሲጮሁና ሲፎክሩ   የነዋሩን ወይም የማኅበረሰቡን ስላም አደፈረሱ ፤ አወኩ ። ጫጫታው  ሲበዛባቸው ፖሊስ ጠርተው  ያስቆሙ እንዳሉም ሰምቼያለሁ ።  

 ባለሁበት አካባቢ በብሄር ተጋሮ  ካልሆኑ  ኢትዮጵያውያን  ተወልዶ ያደጉ  የአቅመ አዳም የደረሱና ያልደረሱ ወጣት የልጄ ጓደኞችና ልጄ  ባዩትና በሰሙት ነገር ተገርመው  የሚከተሉትን ጥያቄዎች አቀረቡልኝ ፦   

“Had Tigraye ever been colonized by Ethiopia ? If so since when? ትግራይ የኢትዮጵያ ቅኝ አገር ነበርን ? ከነበረስ ከመቼ ጀምሮ ? በማለት ሲጠየቁኝ  ፦ yes it was , አው ነበር አልኳቸው  ፤ for how long ? ለምናህል ግዜ ? 

For the last eight months -ላለፉት ስምንት ወራት  በማለት ከቀለድኩባቸው በኋላ ፤ ሊረዱኝ  በሚችሉት ቋንቋ ፣ ቃላትና አገላለጽ በአገር ቤት ስለሆነው ተጨባጭ ሁኔታ አስረዳኋቸው ።  

 “We somehow know  the  history  of Ethiopia  and  we somehow know what is going on in Ethiopia right now ; but their acts and their slogan confused us ,that`s why we came to ask you” ,they said to me  . “በጥቂቱም ቢሆን የኢትዮጵያ ታሪክ እናውቃለን ፤ አሁን ምን እየተደረገ እንደሆነም  እናውቃለን ፤ ነገር ግን የነዚህ ትግሬዎች   ድርጊትና  መፈክራቸው  ግራ ስላጋቡን እንድታስረዳን ወዳ አንተ መጣን” አሉኝ ።

“How could they say and act like this ?” እንዴት እንደዚህ ሊሉና ሊያደርጉ  ይችላሉ?” አሉ ።ትንሽ ከተቀላለዱና ከሳቁ በኋላ – “are they the zombies of our contemporary time?” “አሁን ላለንበት/ለደረስንበት ግዜ  ነሆለሎች ወይም ማሰብ አልባ  ፍጥረት ናቸውን?” አሉ ።  የበለጠ ግልጽ እንዲሆንላቸው የሚከተሉትን  ንጽጽር  አስጨበትኳቸው ።

  • ዲሞክራሲያዊና ሰባአዊ መብቶቻቸውን ስጥቶ ከሚያስተዳድራቸው  ኢ-ትግሬያዊ – ጮቁኖና ረግጦ የሚገቸው ትግሬያዊ
  • ትግሬያዊ ካልሆነ ነጻ አውጪ  – በባርነት የሚገዛቸው  ትግሬያዊ
  • ኢ-ትግሬ  ከሆነ መልአክ   -ትግሬያዊ ሰይጣን
  • መሰረታዊ ፍላጎታቸን አሟልቶ (ከረሃብ ፣ከርዛት ፣ከውሃ እጦት ወዘተርፈ ከሚታደጋቸው  ኢ-ትግሬያዊ –እነዚህን የሚነፍጋቸው /የሚያሳጣቸው  ትግሬያዊ
  •  ከበሽታቸው ከሚፈውሳቸውና ከሞት ከሚያድናቸው ኢ-ትግሬያዊ ዶክተር –በሽታቸውን አባብሶ የሚገላቸው ትግሬያዊ  ዶክተር 
  • አስተምሮ ብሩህ አእምሮ እንዲኖራቸው ከሚያደርግ ኢ-ትግሬያዊ –የሚያደነቁር  ትግሬያዊ 
  • ትግሬያዊ ያልሆነ  ሰው  ፍጹም እውነትና ሳይንሳዊ ሃቅ የሆኑ ነገሮች ከሚነግራቸው   -ተጋሮ በሆነ ሰው የውሸት ክምር  ቢነገራቸው   
  • ከብዝሃን ከኢትዮ -ብሄር ብሄረሰቦች ጋር አብረን በእኩልነት እንኑር ከሚል መሪ/የፖለቲካ ድርጅት –ትግራዊ ብቻ

 ሆነን  እንኑር የሚሉ ትህነግና የትህነግ መሪዮች  ወዘተርፈ  የሚመርጡ ናቸው  አልኳቸው  ።

   ትግራይ  ከኢትየጵያ ነጻ ወጥቷል ! !  መፈክራቸው በተመለከተ

እስካሁን ለብዙ ሺ ዓመታት በማንም  ሳይደፈር በነጻነት የኖረ ፣ በቅኝ አገዛዝ ሥር የወደቁትን ጥቁር ህዝቦች ነጻነታቸውን እንዲጎናጸፉ የረዳ (ኩሩ ታሪክ ፣ኩሩ የነጻነት ስነልቦና ፣ ኩሩ በየኛውም  የቀጥታ ባዕድ ተጽኖ ያልተበከለ ባህል  ወዘተርፈ        ያለው  ታላቅ ብሄርና ማኅበረሰብ አካል ነበሩ ። ከኋላቀር ንቃተ ኅሊናቸውና  ከኋላቀር አስተሳሰባቸው  ምክንያት — ያንን ኩሩ ነጻነታቸውን  ፣ ያንን ኩሩ ታሪካቸውን ፣ያንን ኩሩ ስነልቦናቸውን ፣ ያንን  ኩሩ  ባህላቸውን ወዘተርፈ  ዋጋ አሳጥተ  ውና  አዋርደው ፤  አርትፊሻል ወይም ሜካኒካል ነጻነት ከምዕራባውያን ለማግኘት አቤት አቤት ሲሉ፣ጎንበስ ቀና  ሲሉ ፣ጸት ለጥ ሲሉ  እያየናቸው ነው ። ከ (1917 – 1924) የሶቪየት ህብረት መሪና የፖለቲካ  ሳይንስ ምሁር የነበረው  (Vladimir Ilich Lenin) የዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ማለት ‘የራሱን ማንነት ክዶ ከሌሎች ማንነት መጠየቅ- ከደደብነት ጠባዎች አንዱ ነው’  ብሎዋል ። 

 ትግራይ  ከኢትዮጵያ ነጻ ወጣ ! ! መፈክራቸው  በነሱ ትርጉም  እና  እኛ እንደምናየው

 በተጋሮች እይታ ወይም ገቢታ የኢትዮጵያ መከላኬያ ሃይል ከትግራይ ዋና ዋና ከተማዎች ወጣ ማለት ከዚህ ወቅት ጀምሮ ትግራይ በኢትዮጵያ ግዛት ሥር አይደለም ወይም በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ውስጥ አይደለም  ወይም ትግራይ ሉዓላዊ አገር ሆነ ማለታቸው  ነው  ። ይህ ስሜታዊ ፣ ግንፍላዊ፣ ተመኝ ተመኛዊ ፣ሁኔታዎችን ያላገናዘበ የነጻነት ፈንጠዚያና  አዋጅ  አይሆንምን?

ያንን ለማድረግ የሚያስችሉ ፦ የምጣኔ ሃብት ፣ የማኅበረሰቡ መሰረታዊ  ፍላጎቶችን ሁሉ  ማምረት የሚያስችል መሃጸን ያለው  ለም መሬት  ፣ ኢንዱስትሪ ፣ምቹ  መልካአ ምድራዊ (convenient geo-boundary) ፣ ምቹ መልካአ ምድራዊ ፖለቲካ (suitable geo-poletics) ፣  ከሌሎች አገሮች የሚገናኙበት፣ የሚገበያዩበትና  ለማሃበረሰባቸው  ዘመናዊ ቁሳቁሶችና ሸቀጣሸቀጦች  የሚያቀርቡበት  ወዘተርፈ  ሁኔታዎች አሏቸውን ? በየብስ ደሴት የሚኖሩ መሆናቸውን አይረዱትም/አያውቁትም ማለት ይቻላልን ?  በስተ ሰሜናቸው ፣በስተ ደቡባቸው ፣በስተ ምዕራባቸው ፣ በስተ ምስራቃቸው  ጠላት ባደረጉት ሕዝብ ተክበውና  ታጥረው የሚኖሩ መሆናቸውን አያውቁትም/አይረዱትም ማለት ይቻላልን ? ወይስ 

  1.   አሜሪካና አጋሮቹ – በቬትናም ፣ በላዎስ ፣በአፍጋኒስታን ፣ በይጎዝላቪያ ፣ በኢራቅ ፣በሶሪ ፣በሊቢያ  ወዘተርፈ  እንዳደረጉት)  (ታንክ ፣ ምሳኤል ፣ተዋጊ አይሮጵላን ፣ክላስተር ቦምብ ወዘተርፈ አስልፈው በመምጣት ከሱዳን ጋር የሚያገናኝ መስመር እንከፈትላች   ኋለን  ብሏቸው  ይሆን ? ወይም   
  1. አሜሪካና አጋሮቹ ፣ ግብጽና አጋሮቹ የሉዓላዊ ኢትዮጵያ ሰማይ/ አየር ክልል ጥሰው በመብረር ከሰማይ               በሚወረ ውሩላቸው  የነፍስ  አድን ቁሳቁስና አስቤዛ  በማግኘት ለመኖር አስበው ይሆን ? ወይም
  2. ምንም ሰው በሌለበትና  ህይወት ለማቆየት አስቸጋሪ በሆነ በርሃ ውስጥ  ወይም አሳም ሆነ ሌላ የሚበላ ነገር በማይሰጥ  ባህር ወይም ውቅያኖስ በተክበበ ደሴት ተጥለው  ፣ የፈጠራ ችሎታችሁን ተጠቅማችሁ በደሴቱ የምታገኙትን በመጠቀም  ባልሞትባይ ተጋዳይነት ጥበብ  ለአራት ወይም ለስድስት ሳምንታት ቆዩ ተብሎ እንደሚጣሉ አስደናቂ  የጥንካሬ ተወዳዳሪዮች ? (fascinating survival in island contest TV show)   ትሪኢት ዓይነት  ፤ትግራይን ብቻ ተጠቅመው ለመኖር በመፈለግ ይሆን ?

“A far away field always looks green -ሩቅ ያለ ሜዳ ሁሌ አረንጓዴ መስሎ ይታያል” እንደሚባለው  ተጋሮች ከላይ የጦቆምኳቸው አማራጮች  በመጠቀም  ለመኖር  ከኢትዮጵያና  ጋር  ያላቸው  ግንኙነት ቢበጥሱ ፤ ገመዳቸው  እንዴት እንደሚያጥር ላስጨብጥ

ጥናት የሚያስፈልጋቸው ፣ ነገር ግን ሊሆኑ የሚችሉ ግምታዊ ይሁንታዎች

  • ከየትኛውም በኢትዮጵያ ምድር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር መገበያየት አይችሉም
  • ከትግራይ ውጭ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ዘርፈው ያካበቱት ሃብት ወደ ትግራይ መውሰድ አይችሉም
  • በኢትዮጵያዊ/ዊት ዜግነት ፣ በትውልደ ኢትዮጵያዊ/ዊት መስፈርቶች መኖር የማይፈልጉ ፤ ልክ እንደ ኬኔያና እንድ ጅቡቲ ዜጋ ተቆጥረው ወድ ትግራይ ይወረወራሉ
  • ከላይ  የጠቀስኳቸው  መስፈርቶች የማያሟሉ   ከየትኛውም የመንግሥት ፣ የካፓኒ፣ የግል ሥራዎች ይባረራሉ
  • በኢትዮጵያ በየትኛውም ደረጃ ባሉ ት/ቤቶች ፣ ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዮች መማር አይችሉም
  • ከኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ኑሮ ፣ ልማዳዊና  ባህላዊ ክብረ በዓሎች  ይገለላሉ 
  • በኢትዮጵያውያን ስነልቦና (psychodynamic) እንደ ባዕድ ይታያሉ/ይቆጠራሉ  ወዘተርፈ 

ትግራይ ከኢትዮጵያ መገንጠል የሚፈልጉ ተጋሮች ከላይ በጠቀስኳቸው አጣብቂኝ ሁኔታዎች ሁነው መገንጠል ይፈልጋሉን ?

አይመስለኝም  ፣ በሥልጣን በነበሩበት ግዜ በሃይል የውሰዷቸው መሬቶች ማስመለስ ካልቻሉ  በአሜሪካና አጋሮቹ ታግዘው ከሱዳን ጋር የሚያገናኝ መስመር ወይም ኬላ ቢከፈትላቸውም አይገነጠሉም ባይነኝ ። አሁን የሚያሳዩት ድራማና አክሮባት የምዕራባውያን ምክር ያለበት ነው ።  ቶሎ ሳይምበረከኩ አቅማቸውን  የሚፈቀድላቸ ውን ሁሉ ተጠቅመው  በማስቸገር  ከውንጀል ነጻ ሊያደርጋቸው የሚችልና ቀድም ወደ ነበሩበት ወይም ከዚያም ከፍ ያለ  የሥልጣን እርከን የሚያበቃቸው የዕርቅ ድርድር  ለማመቻቸት/ ለመፍጠር ነው ።  

  የኔ ሥጋት ፣እኔ በጣም ያስጨነቀኝ ፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ  እሽሩሩ ማለት ይብቃን ፣( ከኢትዮጵያዊነታቸው  – ጠላትነታቸው ፣ ከጥቅማቸው – ጉዳታቸው ፣ከማምረታቸው -ብዝበዛቸው ፣ ከመስጠታቸው -መውሰዳቸው ፣ ከሰላማዊነታቸው – ጠባቸው ፣ ከውዳጅነታቸው -ኩርፌያቸው)  ወዘተርፈ  እጅግ በጣም አመዝኖብናል ይሂዱልን ፤ አንፈልጋቸውም እንዳይል ነው   ።  የኢትዮጵያ ሕዝብ  ይቅር በለን ! አጥፍተናል ! ተዳፍረናል ፣ ማረን! ብለው  ጸባያቸውን አሳምረው  የማይኖሩ ከሆነ  ትልቅ ዋጋ የሚያስከፈላቸው ቀን ይደርሳል ። ያኔ ሁለገብ ትሥሥራቸው ፣ ያኔ ሁለገብ እትብታቸው፣ ያኔ ሁለግብ ቅንጦታቸው ፣ያኔ ሁለገብ ጥቅማቸው  ይበጠሳሉ ፣  ገመዳቸው  ያጥራል ።

የኢምራሊስት አሜሪካ ጦር ሠራዊት በደቡብ ቬትናም VS (ሲነጻጸር) የኢትዮጵያ መከላኬያ ሃይል በትግራይ

እ.ኤ.አ በ1954 ዓ.ም  በሆችሜን (Hochi Minh) መሪነት   ከፈረንሳ  ቅኝ አገዛዝ  ነጻ በውጣው  በሰሜን ቬትናም መንግሥት በመታገዝ  ከ1960  እስከ 1973 ዓ.ም በነበረው ግዜ  የአሜሪካ  ሞግዚት ከነበሩ  የደቡብ  ቬትናም ገዢዮች ወታደሮችና ከግዙፍ  የአሜሪካ የጦር ሃይል ፤ በደፈጣ ውጌያ (by guerrilla warfare) ተዋግተው  ደቡብ ቬትናም ነጻ ያወጡ (ቬትኮንግ -Vet Cong) ይባላሉ ። ቬትኮንግ  ማለት የኮሚኒስት ርዕዮት ተከታይ  የነጻነት  ታጋዮች  እንደ ማለት ነው ። 

በትግሉ ወቅት ያልታጠቀው  ሲቪሉ ዜጋና የቡዲሂስት መነኩሴዎች (Buddihist monks) ከቬትኮንጎች ጎን በመሰለፍ  ለትግሉ አጋር ሆኗል ። ምግብ በማብላት ፣ ውሃ በማጠጣት ፣ በቤታቸው በመደበቅ ፣ ስልለው  የጠላት አቅጣጫ በመጠቆም ፣ ጠላት በሚንቀሳቀስበት  አካባቢ እግር የሚጠልፉ  ወጥመዶች  ሰርተው  ሣር በማልበስ  ፣ የቀርካሃ ጫፎች ጠርበውና አሹለው ባደገና ምን እንዳለ በማያሳይ ሣር ውስጥ በአግድም በመትከል፣ ለትግሉ የሚረዱ ዕቃዎች በማጓጓዝ   ወዘተርፈ ብሄራዊ ግዴታቸውን ተወጥቷል  ።  

  ስለሆነም የአሜሪካ ወራሪ ሠራዊት  በሲቪሉ ማኅበረስብና  በቡዲሂስት መኖክሴዎች  ላይ ለመናገር ቃላት የማይገኝላቸው  ግፎች  ፈጽመውባቸዋል ። እቤታችሁ የተደበቁትን  ቬትኮንጎችና የጦር  መሳርያ አውጡ  እኛን ትሰልላላችሁ ፣ቬትኮንጎች ያሉበት ንገሩን/ምሩን  ወዘተርፈ በማለት  አንገላቷቸው ፣ ደበደቧቸው ፣ ገደልዋቸው ፣ ከእነ-ቤታቸው  አቃጠሏቸው ፣ መንደራቸው በክላስተር  ቦምብ አቃጠሉባቸው ወዘተርፈ  ። 

የወቅቱ የዓለም ፖለቲካ ቀሳሚው  የ1960ዎችና  1970ዎች  ኢትዮጵያዊ/ት ትውልድ  ይህ ታሪክ ያውቃል  ።  በደቡብ ቬትናም ዋና ከተማ (ሳይጎን ወይም ሆችሜን ሲቲ) የጦርነቱ ስማዕታት ገጽታ የሚያሳይ ቤተመዘክር ወይም ሙዚየም ሲጎበኝ ለዓይን  የሚዘገንኑና መንፈስ የሚረብሹ  ምስሎች ለሚያይ ፤ እውነትም በዲሞክራሲያዊነት የዓለም ማማ ነኝ ከሚል የአሜሪካ መንግሥት የተፈጸመ  ነው ብሎ ለማመን እጅግ በጣም ያስቸግራል ። 

ከዚያ ይልቅ በዲሞክራሲዊ  መርህ የተገዙ/የታነጹ  ናቸው በማለት የሚመጻደቁባቸውን (ህገመንግሥታቸው ፣ፓርላማቸው  ፣መንግሥ ቶቻቸው  እና  መሪዮቻቸው )  የአሜሪካን ጥቅም ለማስጠበቅ  ወደ ሥጋ በል አውሬነት (bestiality) ፣ወደ የጫካ እንስሳት ጨፍጭፎ የሚበላ  አንበሳነት ይቀየራሉ ቢባል የበለጠ ያሳምናል ። 

ከላይ ባስቀመጥኩት  ንኡስ አርእስት ልገልጸው  ወደፈለኩት ፍሬ ጉዳይ ልመለስ ፦ የኢትዮጵያ መከላኬያ ሃይል  ተጋሮችን   ጮቁኖና በጠመንጃ አፈሙዝ ረግጦ ለመግዛት ሞክሯልን ? (የአሸባሪዩ  ህወሃት አባል/ት ደብቃችኋል ፣ መሳሬያ ደብቃችኋል ፣  ያሉበት አሳዩን ፣ እኛን ትሰልላአላችሁ) ወዘተርፈ በማለት ትግራውያንን (አንገላቷልን  ?ደብድቧልን  ? ገሎዋልን ? ቤታቸውና መንደራቸውን አቃጥሎዋልን) ? ወዘተርፈ  ። ያ እንዳላደ ረጉ  ገሃድ ሃቅ ስለሆነ ማብራሪያ አያስፈልገውም ። 

መከላኬያው ፦ (ሕዝቤን ፣ አባቶቼን፣ እናቶቼን ፣እህቶቼን ፣ ወንድሞቼን) መታደግ አለብኝ ፣ መንከባከብ አለብኝ ፣ ደህንነታቸውና ሰላማቸውን ማስጠበቅ አለብኝ በሚል የወገናዊነትና የሕዝባዊነት መንፈስ ተላብሶ  ነበር የታጓቸው ፤ ያገለገሏቸው ።  አጸፋው ግን ‘ባጎርስኩ እጄ ተነከስኩ’ ዓይነት ሆነ ።

ከላያ ለመግለጽ እንድሞከርኩት ያልታጠቀው  የደቡብ ቬትናም ሕዝብ  በመግደልና  በመጨፍጨፍ የቅኝ ተገዢ ሊያደርጋቸው   በሞከረው  የአሜሪካ ሠራዊት ላይ  የተለያዩ  ስውር ጥቃቶች  በማድረስ ታግሏቸዋል ። ጥቃቶቹ ፍጹም ( ፍትሃዊ  ፣ ሞራላዊ ፣ ሃቀኛ) ነበሩ ። ለአሜሪካኖች ግን ኢፍትሃዊ ነበሩ  ፤ ስለሆነም  ቬትናሞችን ጨፈጨፉ ፣ አሽማቀቁ ፣አሰቃዩ ። 

 አውደ ሕዝበ ተጋሮ ይህ ያደርጋል ለማለት ብንቸገርም  ወይም  የንቃተ ኅሊና ሚዛን የሚፈታተን ቢሆንም ፣ ተጋሮች በመከላኬያ ሃይላችን ላይ የፈጸሙት  ጥቃት  ቬትናማውያን በአሜሪካን ሠራዊት ላይ ከፈጸሙት  ጥቃት እጅግ በጣም የከፋ ነው ። ምክንያቱም  ቬትናማውያን ለጠላቶቻቸው  –  መርዝ በውሃ ጨምረው  አልሰጧቸውም ፣ ምግብ ስጥተው ከኋላ /አልጨፈጨፏቸውም ፣ የቡዲሂስት መነኩሴዎች  የጦር መሳርያ ደብቀው  አልቶኮሱባቸውም  ወዘተርፈ ። ነገር ግን የኢትዮጵያ መከላኬያዎች  እንደ አሜሪካኖች መበቀል አልፈለጉም ፣ ተጋሮቹ ከውጭ አገር እንደመጡ  እንደ ባዕድ ቢቆጥሯቸውም ፣መከላኬያው  ግን እንዴት በወገኖቼ የብረት ቃታ እስባለሁ ? በማለት ራሱን መግደል ፣ በነሱ መገደል ፣  መቁስል ፣መደብደብ  ወዘተርፈ  መረጠ ።

 መከላኬያችን  ያ በማድረጉ የፍጹም  ወገናዊነትን ! የፍጹም ሕዝባዊነትን ! የፈጹም የአገር ልጀነትን መርህና የንቃተ-ኅሊና ምጥቀታቸውን  ለተጋሮች አስተምሯል ። ተጋሮች ፍጹም (ኢፍትሃዊ ፣ኢሞራላዊ  ፣ኢሰባዊ ጥቃትና ክህደት) ፈጽሞባቸዋል ።  የማይረሳ የታሪክ ጠባሳ  ፤ የማይረሳ የባንዳነት  የታሪክ አሻራ አኑሯል/አስመዝግበዋል ።  

ሞት ለጠባቦች ! ሞት ለአካል ሰንጣቂዮች ! ሞት ለጸረ አንድነቶች ! ሞት ለኢትዮጵያ ጠላቶች ! 

ድል ለመከላኬያችን ! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ! ድል ለኢትዮ – (ብሄር -ብሄረሰቦች ልዩ ሃይሎችና ሚሊሺያዎች !

Filed in: Amharic