ከእስክንድር ጎን መቆም ማለት መስዋዕትነት ከከፈለላት ኢትዮጵያ ጎን መቆም ነው…!!!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ
* … እስክንድር ትግል ሲጀምር ያገዛዝ ምንጣፍ ይጎትቱ የነበሩ ሃሰተኞች ዛሬ ተገልብጠው “የህወሃት ደጋፊ ነው!” ይሉታል
እስክንድር የታፈነው በመንግስት ብቻ አይደለም። የእስክንድርን አላማ የሳቱ ፣ ለሃገሩና ለህዝብ የከፈለውን መስዋዕትነት አቃለው የህወሃት ደጋፊ ሊያስመስሉት በሚታትትሩ እኩያን ታላቁ እስክንድር ታፍኗል። እስክንድር የደገፉት መስለው ክብሩን ዝቅ ባደረጉ ፣በስሙ በሚተዳደድሩ ብርኩናቸውን በምስር ወጥ በሸጡ እኩይ ግለሰቦች ታፍኖ በስሙ ክብሩን የማይመጥን ግፍ እየተሰራበት ነው። ከእስክንድር ጎን መቆም ከአላማው ጎን መቆም እንጂ ፎቶዉን እያሽከረከሩ የህይወቱን አስር አመት የነጠቀውን የህወሃት አገዛዝ ማሽሞንሞን አይደለም። ከእስክንደር ጎን መቆም ማለት መስዋዕትነት ከከፈለላት ኢትዮጵያ ጎን መቆም ነው። ትላንት እስክንድር ታስሮ ረጅም ባንዲራ እየጎተተ አገዛዙን ደግፎ ሰልፍ የወጣ የረከሰ ዲያስፖራ ዛሬ ህወሃትን ተቃውመን ኢትዮጵያን ስለደገፍን ብቻ ያገዛዙ ደጋፊ ሊያደርገን ሲዳዳው ማየት አሳፋሪ ነው። ቀድሞም ከእስክንድር ጎን ያልነበሩ ፣ እሱ ትግል ሲጀምር ያገዛዝ ምንጣፍ ይጎትቱ የነበሩ ጫንቃቸው ለባርነት የደነደነ ሃሰተኞች የእስክንድርን ክብር እያራከሱ ዛሬ እስክንድር የህወሃት ደጋፊ ነው ይሉናል ። እባካቹህ ይህንን ንፁ ሰው የበደል በደል አትበድሉት ፣ ትላንት ከካዳችሁት በላይ አታቁስሉት።
Free Eskinder Nega ስንል ከሴረኛው የህወሃት ደጋፊ ዲያስፖራ ጭምር ነው !!