>

20 የክብር ዶክተሬት ድግሪ ያላቸው የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት...!!! (ጥበቡ በለጠ) 

20 የክብር ዶክተሬት ድግሪ ያላቸው የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት…!!!

(ጥበቡ በለጠ) 

ዛሬ የተወለዱበት ቀን ነው። ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በአለማችን ካሉ 20 ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክተሬት ድግሪ ተቀብለዋል! በየዩኒቨርሲቲዎቹም ተገኝተው ታላላቅ መሪዎችና ምሁራን በታደሙበት ውብ ንግግሮች አድርገዋል፡፡ ንግግሮቻቸውን አልፎ አልፎ እጽፋቸዋለሁ፡፡ እኚህን ታላቅ ንጉስ የሚከተሉት የምድሪቱ ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክተሬት ድግሪ አበርክተውላቸዋል፡፡
1- ግንቦት 20 ቀን 1946 ዓ.ም ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
2- ግንቦት 25 ቀን 1946 ዓ.ም ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ
3- ግንቦት 28 ቀን 1946 ዓ.ም ከሞንትሪያል ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክተሬት
4- ግንቦት 30 ቀን 1946 ዓ.ም ከሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
5- ግንቦት 1946 ዓ.ም ከመክጊል ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
6- ሐምሌ 16 ቀን 1946 ዓ.ም ከኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
7- ሐምሌ 29 ቀን 1946 ዓ.ም ከአቴና ብሐራዊና ካፓዲስትሪን ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና የክብር ዶክተሬት ድግሪ
8- 1946 ዓ.ም አትላንታ ጆርጂያ ከሚገኘው ሞርሐውስ ኮሌጅ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
9- ጥቅምት 10 ቀን 1947 ዓ.ም ከኢክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
10- ከቦን ዩኒቨርሲቲ በእርሻ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
11- ሕዳር 4 ቀን 19 49 ዓ.ም ከባናራስ ሂንዱ
 ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሑፍ ዶክተሬት ድግሪ
12- ሐምሌ 5 ቀን 1951 ዓ.ም ከሞስኮ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
13- ሐምሌ 8 ቀን 1951 ዓ.ም ከፕራግ ከቻርልስ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የዶክተሬት ድግሪ
14- ህዳር 27 ቀን 1952 ዓም ከላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
15- መስከረም 22 ቀን 1956 ዓ.ም ከጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ በሥነ-ጽሑፍ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
16- መስከረም 18 ቀን 1957 ዓ.ም ከሩማኒያ ከቡካሬስት ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
17- መስከረም 30 ቀን 1959 ዓ.ም ከሊባኖስ ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ቻርልስ ሄሉ ባሉበት ክብር ዶክተሬት
18- ሚያዚያ 24 ቀን 1960 ዓ.ም ከታይላንድ ከተማስት ዩኒቨርሲቲ የህግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
19- ግንቦት 9 ቀን 1960 ዓም ከምዕራብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
20- ግንቦት 13 ቀን 1960 ዓም ከደቡብ ኮሪያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ዶክሬት ድግሪ ተቀብለዋል፡፡
  ( የምንጭ ስብስብ ከአጼ ኃይለስላሴ የታሪክ መጻሕፍት)
Filed in: Amharic