>

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለትግራይ ሕዝብ ቀርቶ ለአሸባሪው ሃይልም ቢሆን ባለውለታ ነው...!!!"  አሳዬ ደርቤ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለትግራይ ሕዝብ ቀርቶ ለአሸባሪው ሃይልም ቢሆን ባለውለታ ነው…!!!” 
አሳዬ ደርቤ

➜አሸባሪው ከፌደራል መንግሥቱ ምንም ዓይነት ትዕዛዝ በማይቀበልበት ሁኔታ ከNGO ባለፈ መደበኛ በጀቱን እየላከ ይደግፋቸው ነበር
➜መቀሌ ላይ ተቀምጠው ውስኪ እየጠጡ በተለያዩ የሽብር ጥቃቶች ኢትዮጵያን ሲያምሷት ጠሚው ተመሳሳዩን በማድረግ ፈንታ አገሪቷን ትቶ ቤተ-መንግሥቱን ያሰማምር ነበር።
➜ህውሓት ክልላዊ ምርጫ አድርጎ ዳንኪራውን ሲረግጥ ጠሚው ችግኝ ይተክል ነበረ፤
➜ጌታቸው ረዳ በየቀኑ በቲቪ እየቀረበ “ጨቅላው” እና “ወፈፌው” ሲለው፥ ጠሚው “ደብረ ጽዮንን እገዙት” እያለ ይመልስ ነበር
➜ጁንታው በየሳምንቱ እሁድ ወታደራዊ ትርዒት ሲያሳይ ጠሚው ቀበናን እያለማና ቀይ ቀበሮ እያላመደ ነበረ
➜አሸባሪው ሃይል ከፌደራል ተሹመው የሚላኩ የሰሜን እዝ አዛዦችን በመጡበት አውሮፕላን እየሸኘ ያለመጠን ሲጨማለቅ፥ ጠሚው አቅሙን ከማሳየት ይልቅ አቅም አልባ መባልን መርጦ ነበረ፥
➜ትሕነግ ገዳም መግባት የሚገባቸውን አሮጊቶች መሳሪያ አስይዞ በቲቪ እያቀረበ ጥጋባቸውን ሲያሳይ፥ ጠሚው ከትሕነግ ጋር አስታርቁኝ” ከሚል ልመና ጋር  ሽማግሌዎችን ሰብስቦ ወደ መቀሌ ይልክ ነበረ።
➜ከግብጽና ሱዳን ጋር መሥራታቸው አልበቃ ብሎ “ግድቡን ሽጦታል”  እያሉ ሲያብጠለጥሉት ጠሚው በሩ ላይ ያለችውን ፒኮክ አሻግሮ እያዬ “ጌታ ይቅር ይበላችሁ” ይል ነበረ።
➜እንዳጠቃላይ አሸባሪው ሃይል ሰሜን እዝን ጨፍጭፎ በቅራቅርና በራያ በኩል ወደ ሸገር መገስገስ እስኪጀምር ድረስ ጠሚው ፓርክ ልማት ላይ ነበረ፥
.
➜ የአማራ ክልል ሁለት ዙር ልዩ ሃይል ማሰልጠኑ ለጠሚው ትልቅ የስጋት ደመና በሃገሪቱ ላይ እንዳንዣበበ ሆኖ ተሰምቶት ፣ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ፣አይተነው የማናውቀው ንዴት በፊቱ ላይ እየነደደ ነበር ድርጊቱን ያወገዘው። ተናዶም አልቀረም የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ስልጠና ፀሃይ ያየው ጤዛ ሆኖ ቀረ! ይህ ሲሆን  እነሆ   ወያኔ 250,000 ልዩሃይል አሰልጥና ሰሜን ኮሪያነቷን በትርኢት ጭምር እያሳየች፣”እኛን መንካት በእሳት መጫወት ነው” እያለች እየፎከረችና እየሸለለች  ነበር።
ስለዚህ የትግራ ሕዝብ ጠምዶ መያዝ ያለበት ከውስጡ የወጣውን አሸባሪ እንጂ አራት ኪሎ ያለውን መሪ አይደለም።
Filed in: Amharic