>

‹‹አሜሪካ እያደረገች ያለው ተግባር ከ100 ዓመት እድሜ በላይ ያለውን የኢትዮ-አሜሪካ ግንኙነት ድልድይ ሰባሪ ነው›› (ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ )

‹አሜሪካ እያደረገች ያለው ተግባር ከ100 ዓመት እድሜ በላይ ያለውን የኢትዮ-አሜሪካ ግንኙነት ድልድይ ሰባሪ ነው››
ሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ የአሜሪካ ዲያስፖራ የሰላም ጓድ ሰብሳቢ
(ኢ ፕ ድ)

አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወነ ስላለው እውነታ እያወቀች አይናችሁን ጨፍኑ ማለቷ የ100 ዓመት እድሜ ያለውን የኢትዮ-አሜሪካ የህዝብ ለህዝብ የግንኙነት ድልድይ ሰባሪ መሆኑን የአሜሪካ ዲያስፖራ የሰላም ጓድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ አስታወቁ። የአሜሪካንን ፖለቲካ መለወጥ መቻል አለብን፤ እንለውጠዋለንም ብለዋል።
ፕሮፌሰር ብሩክ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ አሜሪካ በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ ላይ የያዘችው አቋምም ሆነ ፖሊሲ የኢትዮጵያን አንድነት የሚያናጋ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም የሚጎዳና በሀገራቱ መካከል ከ100 ዓመት እድሜ በላይ ያስቆጠረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚያፍረስ ብሎም የግንኙነትን ድልድይ የሚሰብር ነው ።
እኛ በአሜሪካ አገር ታክስ ከፋይ ሆነን እየኖርን በአገራችን ላይ የሚደርሰውን ተጽዕኖ እንዲሁ ማለፍ አንችልም ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ የጆባይደን አስተዳደርን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ናሽናል ሴኩሪቲ ካውንስሉም ሆነ ኮንገረንሱ በጉዳዩ ላይ አቋም ወስደው መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በውድቅት ሌሊት በጁንታው ሲመታ እየታወቀና ጀማሪው ራሱ ሆኖ እያለ እስካሁን አይናችሁን ጨፍኑ እያሉን ነው፤ የመከላከያ ሠራዊታችን መስዋዕትነት ከፍሎ የትግራይን ህዝብ ነጻ እንዲወጣ ለማድረግ ሞክሯል፤ ስለዚህ ጉዳይም አይወራም።
መከላከያ ሠራዊታችን መቀሌ ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ ሁኔታዎች እየሰከኑ መምጣታቸው ቢስተዋሉም እውነቱን በእውነትነት አላቀረቡትም ብለዋል።
በሌላ በኩል መንግሥት ለህዝቡ በመቆርቆር እርዳታ እንዲገባ ለማድረግ ጥረት እያደረገ እንኳ የሰብዓዊ መብት አይከበርም፤ እርዳታ እየተሰጠ አይደለም እየተባለ ጥፋተኛ እየተደረገ ነው።
የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንኳ ይህን በአግባቡ ለመረዳት አልፈለጉም። መጠየቅ ያለበትን አካልም ለመጠየቅ ፈቃደኝነት እንዳላሳዩ አስታውቀዋል ።
Filed in: Amharic