አህመድ ሱሌይማን
*…. መከላከያው ” ከበላይ አልታዘዝኩም” በማለት ትላልቅ መሳሪያ ጥሎ ለጠላት ትቶ እየሄደ ገበሬው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት ነው። እነሱ ወደ አማራ ክልል እየገቡ ጥቃት እየፈፀሙ ምንም አይነት የአፀፋ ምላሽ እየሰጠ አይደለም፤ እኛ ወደፊት እንዳንሄድ መሀል ላይ ሆኖ ማነቆ የሆነብን መከላከያ ሰራዊቱ ነው የመከላከያ አዛዦችን ልትመረምሩ ይገባል ! እየተወጋን ያለነው በሁለት በኩል ነው።
መንግስት አሻጥሩን ሊያቆም ይገባል !
ራያ ግንባር ላይ ራያን እያስጠቃ ያለው መከላከያ ሰራዊት ነው መጡባችሁ ሽሹ እያለ ህዝብ እያሸበረ ወጣቱ እንዳይሄድ የሄደውም እንዳይዋጋ ማነቆ ሆኗል መከላከያ ሲሸሽ መሳሪያውን ይዞ ባይችል አቃጥሎ መሄድ እየቻለ አስረክቦ እየወጣ ህዝቡን እያስጨረሰ ነው።
የሽብርተኛው ቡድን እየወጋን ያለው መከላከያ እየጣለለት በሚወጣው ከባባድ መሳሪያዎች ነው !
መከላከያው ወይ አልተዋጋ መሀል ላይ በመሆን ለእነሱ መሳሪያ እያስረከበ ገበሬው ላይ ጉዳት እንዲያደርሱ እያደረገ ይገኛል !
መከላከያው ወይ ለቆ ይውጣ ወይ ይዋጋ !
መንግስት በመከላከያ ስም እየተሰራ ያለውን አሻጥር ሊያስቆም ይገባል :
የከባድ መሳሪያ ተኩስ ይሰማ እንደነበር #ከወልዲያ ካለ ሰው የሰማሁት ትናንት ነበር። የከባድ መሳሪያ ተኩስ እየሰማን ነው ነበር ያለኝ። የከባድ መሳሪያ ተኩስ ከወልዲያ በቅርብ እርቀት ማለት ነው። ከባድ መሳሪያ የሚለው ይሰመርበት።
ማን ነው ይህን ከባድ መሳሪያ ያስታጠቃቸው? ይህን ለመጠየቅ ልብ ካላችሁ፣ ከባባድ መሳሪያዎችን እንዴት አገኙ ብላችሁ የምትጠይቁ ከሆነ፡ አዎ መልሱ መከላከያ ነው የሚል ነው። እንዴት መከላከያ? ካላችሁም ትግራይን ጥሎላቸው ሲወጣ የአገር ብረት ለበስ መሳሪያውን ነው ጥሎላቸው የወጣው።
መከላከያ በእጁ ላይ የቀረው መሳሪያ ምን አለው እስክትሉ ድረስ። እያጋነንኩኝ አይደለም። 39 howitzer ከታች በምስሉ የምታዩትን አይነት መሳሪያዎችን ከነ ኦራል ሳቢ ትራኮች ድረስ ጥሎላቸው ወጥቷል። ማስረጃውን ማሳየት ይቻላል። በቪዲዮም በሰነድም።
ከከባባድ መሳሪያዎች ሌላ በሺዎች የሚቆጠሩ የመከላከያ ወታደሮቻችንን ነው የመከላከያ አመራሮች ለትህነጎች አስረክበዋቸው የወጡት። ዛሬ እነዚህ ወታደሮች የትህነግን ምሽግ በመቆፈር፣ እርሻ በማረስ፣ የጉልበት ስራዎችን በመስራትና ገሚሱን በተሀድሶ ጭንቅላቱን አጥበው እንዲዋጋላቸው በማስደረግ ላይ ናቸው።
ይህንን ማን አደረገ? ያደረገውማ መንግስት ያስቀመጣቸው የመከላከያ አመራሮች ናቸው!!
ትናንት ክላሽ ይዞ ጉድጓድ ለጉድጓድ ሲሄድ የነበረ ሀይል፣ ይሄው ዛሬ በ 15 ቀን ውስጥ የመከላከያን ብረት ለበስ ታጥቆ ወልዲያ ጫፍ ለመድረስ በቅቷል። እውነታው ይህ ነው።
እንደሰለጠኑ አገሮች እንደነ አሜሪካና እንደነ አውሮፓ እንደ ሌሎቹም አገሮች እያንዳንዱን አውደ ውጊያ ከወታደሮቻችንና አመራሮቻችን ጋር ከምሽግ ሆኖ የሚዘግብና የሚያስተላልፍ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ባይኖረን፣ ከቦታው በራሳቸው ተነሳሽነት ለመዘገብ የሚሞክሩን ማንጓጠጥ በራሱ ጁንታነት ነው።
ህዝብ መጠየቅ መጀመር አለበት፣ ጥያቄዎችን መጠየቅ ከአንድ አገር ወዳድ ዜጋ የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው። አመራሮቹ መጠየቅ አለባቸው። አካውንተብሊቲ ያስፈልጋል። አዎ! ምን እያደረጋችሁ ነው ተብለው ሊጠየቁ ይገባል።
ለምን የውሸት ዜናዎችን ለምን misinformation ኖችን ትለቃላችሁ ወይም ታስለቅቃላችሁ ሊባሉ ይገባል። እየተቆመረ ያለው በህዝባችን ህይወት በህዝባችን ህልውና ላይ በመሆኑ አመራሮቹን ማንቁርታቸውን ይዞ መጠየቅ ከተገቢም በላይ ነው። አትጠይቁ፣ አትናገሩ፣ አታስተላልፉ፣ ዝም በሉ የሚሏችሁን ደናቁርቶች እንዳትሰሟቸው ግላዊ መልዕክቴ ነው። ሁላችሁም በግላችሁ የምታውቁትን ዘገባ በመናገር የኢንፎርሜሽን ልውውጥ እናድርግ እላለሁ።
በነገራችን ላይ አሁናዊ ሁኔታውን በመዘገብ እውነቱን ስላሳወከንና የመንግስታችንን ስራ ስላጋለጥክልን በድጋሜ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ላመሰግንህ እወዳለሁ።
*****
ወልዲያ፣ ደሴ፣ ደብረ ብርሃን፣ አዲስ አበባ፣ በመንግስት ሰዎች ምንጣፍ አንጣፊነት…… የተቀራችሁት እስከዛው ዝም በሉ እንዳትናገሩ፣ ስራቸውን አመራሮቻችን ስለሚያውቁ መረጃ አታውጡ። ስልታዊ ማፈግፈግ ስለሆነ ዝም በሉ።