>

ከፍታህን ጠብቀህ ኢትዮጵያን ስላከበርክ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ይህን ክብር አበርክቶልሃል !!  ( ሀብታሙ አያሌው)

ከፍታህን ጠብቀህ ኢትዮጵያን ስላከበርክ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ይህን ክብር አበርክቶልሃል !!

      ሀብታሙ አያሌው

 

*….እንደ አገር በገጠመን ከባድ ፈተና መካከል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንካችሁ የደስታ ዜና ብሎናል !!
ይህ ታላቁ  አንጋፋ  ዩኒቨርሲቲ ለታላቁ ሰው  ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የክብር ዶክትሬት ለመስጠት ዛሬ ባካሄደው የሴኔት ስብሰባ ማፅደቁን ይፋ አድርጓል።
 ቴዲ  ነገ ወደ ጎንደር በመምጣት ቅዳሜ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም በተማሪዎች ምረቃ ዕለት ተገኝቶ የክብር ዶክትሬቱን እንደሚቀበል ተረጋግጧል !!
ተስፋ አደርጋለሁ ተወዳጁ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ቀጣዩ ተረኛ ይሆናል !!
ቴዲ ከዚህም በላይ ክበርልን …  ኢትዮጵያ አንተ በዜማ በቅኔህ ፀባዖት እስክትደርስ ከፍ ስታደርጋት ከፍ ያደረገችህ ታላቅ አገር እንጂ ጌታቸው ረዳ ቮድካ ባናወዘው ህሊና ሊያራክሳት የሚሞክራት በድኩማን ህሊና የኮሰሰች ጎጅ እንዳልሆነች የመይሳው አገር ጎንደር ምስክር ሆናለች።
Filed in: Amharic