>

ፕሮፌሰር መረራ እራሳቸውን ገሰጹ - አቋማቸውን ለወጡ...!!! (አሳዬ ደርቤ)

ፕሮፌሰር መረራ እራሳቸውን ገሰጹ – አቋማቸውን ለወጡ…!!!

አሳዬ ደርቤ

“የብልጽግና መንግሥት በፓርቲያችን እና በአመራሮቻችን ላይ የፈጸመው ድርጊት ባሳደረብን ሕመም ለሕዝባችን የማይመጥኑ ውሳኔዎችን ስናስተላልፍ መቆየታችን ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን አሁን ያለውን ሥርዓት መገርሰስና በኦሮሚያ ሕዝብና ቄሮ ላይ በርካታ ግፍ ሲፈጽም የኖረውን የህውሓት ሥርዓት ወደ ሥልጣን መመለስ የተለያዩ ነገሮች በመሆናቸው ቆም ብለን ለማሰብ ተገደናል፡፡ ሕዝባችንም እንዳዘነብን ተረድተናል፡፡
በእውነቱም በዚህ ሰዓት ስለ ሽግግር መንግሥት ማሰብ ከአራት ዓመት በፊት የሕይወት መስዋዕትነት በከፈሉ ቄሮዎች መካነ መቃብር ላይ ተረማምዶ ከገዳያቸው ጋር እንደመደራደር የሚቆጠር ነው። ብሎም “አሸባሪ” የተባለውን ሃይል ለመደምሰስ ከኦሮሚያና ከሌሎች አካባቢዎች የሚዘምተውን ወጣት ከህውሓት ጋር ተሰልፎ እንደ መውጋት የሚታይ ነው። በዚህም ምክንያት ዘመቻው በድል ተጠናቅቆ የህውሓት ሥርዓተ-ቀብር እስኪፈጸም ድረስ በምንችለው ሁሉ ትግሉን የምንደግፍ ይሆናል።”
Filed in: Amharic