>
5:21 pm - Tuesday July 21, 2826

እኮ ለምንድን ነው ዝም የምንለው? ለምንስ ነው የወገንን ፍጅት የምንደብቀው??? (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

እኮ ለምንድን ነው ዝም የምንለው? ለምንስ ነው የወገንን ፍጅት የምንደብቀው???
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ተመልሻለሁ ወገኖቸ እንዴት ሰነበታቹህ??? 
ባለፈው ለአንድ ወር አግደውኝ ቆይተው ለቀቁልኝና ጥቂት ቀናት እንደተጠቀምኩ እንደገና ደገሙና ለአንድ ወር አግደውኝ ሰንብተው አሁን ከደቂቃዎች በፊት መልቀቃቸው ነው፡፡ ምንምኮ መተንፈስ አልተቻለም ወገኖቸ፡፡ ፌስቡክ ለታፈነው ሕዝባችን ድምፅ ማሰሚያና የመወያያ መድረክ በመሆኑ በእግዚአብሔር እንደተፈጠረልን በጎ ዕድል ወይም መልካም አጋጣሚ ቆጥረን በጣም የመረቅነውንና ያመሰገንነውን ያህል ወደኋላ ግን አፋኙንና አሸባሪውን አገዛዝና ጭፍሮቹን “ለምን ተናገራቹህ?” እያለ አላስተነፍሰን በማለቱና አፈና በመፈጸሙ እየጠላሁት ነው!!! “በቂና አሳማኝ ምክንያት አላቸው ወይ?” ብሎ ሳይመረምር እንዲያው ዝም ብሎ በውኃ ቀጠነ “የጥላቻ ንግግር ነው!” እያለ የምንለጥፋቸውን ጽሑፎች ማስወገዱና ለወር ለወር የእገዳ ቅጣት መጣሉ የአንባገነኖችን የጥቃት ሰለባ ሕዝብና ድምፅ የሆንነውን እኛን እያንገላታና እየጎዳ፣ ሐሳብን የመግለጽ መሠረታዊ ሰብአዊ መብትንም እየነፈገን ነውና ፌስቡክ ይሄንን ጉዳይ ቢያስብበት መልካም ነው!!!
ከዚህ ቀደም ሲያግዱኝ የማልጠቀምበትን ሁለተኛ አካውንቴንም ያለምንም ምክንያት አብረው ያግዱት ነበር፡፡ በዚህኛው ግን ያንኛውን አብረው አላገዱት ስለነበር ጽሑፎቸን እዚያ ላይ እየለጠፍኩ ይሄንኛውን አካውንቴን ታግ እያደረኩ በታይም ላይኑ ላይ እንዲታይ በማድረግ ጽሑፎቸን ሳደርሳቹህ እንደቆየሁ ብዙ ሳይቆዩ እሱንም ላልተወሰነ ጊዜ አገዱት፡፡ ከዚያም ቢያንስ እንኳ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የምጽፋቸውን ፈቃደኛ የሆኑ የፌስቡክ ጓደኞቸን እያስቸገርኩ ጽሑፎቸን ታግ አድርገው እንዲለጥፉልኝ በማድረግ ጽሑፎቸን ላደርሳቹህ ስሞክር ቆይቻለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ላመሰግናቸው እወዳለሁ!!!
ሰሞኑን እንደምታዩዋቸው የምንጽፋቸውን የወገን ብሶትና የፍትሕ ጥያቄ ጽሑፎቻችንን “የጥላቻ ንግግር ነው!” እያሉ ለፌስቡክ እያመለከቱ አካውንቶቻችንን የሚያሳግዱብን እነኝህ ቅጥረኛ ሕሊናቢስ የጉድ ፍጥረቶች ወያኔ/ኢሕአዴግ አማራን ለመፍጃ ሰብበ እንዲሆነው በማሰብ ለሁለት ተቧድኖ “ሕግ የማስከበር ጦርነት” በሚል ሽፋን ሲያኪያሒደው በቆየውና አማራን እየለየ ከጨፈጨፈበት የሰሜን ዕዝ አንሥቶ ከ1500 በላይ ወገኖችን እስከፈጀበት የማይካድራው ፍጅት ድረስ ከዚያም አልፎ “ርስትህን አስመልስ!” ብለው አታለው ከየስውራው እየጫኑ ወስደው አስገብተው ከኋላ በመከላከያ ከፊት በወያኔ እየተመቱ እንደቅጠል እስከረገፉት ፋኖ ወይም የአማራ ሚኒሻና የአማራ ልዩ ኃይል ድረስ ልትገምቱት ከምትችሉት በላይ በዐሥር ሽዎች የሚቆጠር አማራ በፈጁበትና ሕዝቡ “የወያኔ ባለሥልጣናትን በቁጥጥር ስር በማድረግ ሕግ እናስከብራለን ብላቹህ ጦርነት አድርጋቹሃል የታሉ ታዲያ በቁጥጥር ስር የዋሉት?” ተብለው እንዳይጠየቁና ሴራቸው እንዳይነቃበት የተወሰኑ የወያኔ ባለሥልጣናትን ሁነቱ እውነት እንዲመስል ተጎሳቁለው እንዲታዩ በማድረግና “በቁጥጥር ስር ዋሉ!” በማለት “ወያኔ ተደመሰሰ!” ብለው በማብሰር ሕዝብን አጃጃሉ አቄሉ አሞኙ!!!
መቸም ምንም ቢሉ እንደፈለጉ የሚያቄሉት ሕዝብ አለላቸውና አሁን ደግሞ እንደገና “ጠፋ ተቀበረ ተደመሰሰ!” ያሉትን ወያኔ እንደገና ነፍስ ዘርተው በማስነሣትና “የግፍ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ!” እንዲሉ አማራ ተጨፍጭፎ ባለቀ እንደጥፋተኛ ተቆጥሮ እንደገና ደግሞ “በአማራ ላይ ሒሳብ እናወራርዳለን!” ብለው አሁንም አማራን ለመፍጀት በቀጠሉት የውሸት ጦርነት እየሰማቹህት እንዳላቹህት በራያ እና በጠለምት ግንባር መከላከያ ተብየውን “ቶክስ ማቆም!” በሚል ፈሊጥ ከውሸቱ ጦርነት እንዲገለል አደረጉና የአማራን ገበሬ ከወሎና ከጎንደር ብቻ ሳይሆን ከጎጃምና ከሸዋም ጭምር አጉዞ ወስዶ ያለ ስንቅና ትጥቅ በአሻጥር እየማገደ በማስፈጀት “እናወራርዳለን!” ያሉትን የግፍ ሒሳብ “ተዋጋ!” ተብሎ ከእርሻው ላይ እየተለቀመ የተወሰደውን የአማራ ገበሬ ብቻ ሳይሆን “ወያኔ ተቆጣጠራቸው!” በተባሉት ስፍራዎች ያለውን የአማራ ሕዝብንም ጭምር በመጨፍጨፍ እንደጉድ የግፍ ሒሳባቸውን እያወራረዱበት ይገኛሉ፡፡ ነውረኛ ቅጥረኞችም ይሄንን ግፍና አሻጥር የሚያጋልጡትን የግፍ ሰለባ ወገኖቻችንንና ሌሎች ተቆርቋሪ ወገኖቻችንንም “ዝም በሉ! ምንም አትናገሩ! መንግሥትን እመኑት!” እያሉ ለማፈንና እውነቱ እንዳይታወቅ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ!!!
እነማን እንደሆኑ ታውቋቸዋላቹህ! ከኢዜማ ቡችሎች እስከ አብን የሚባለው የፀረ አማራው የወያኔ አህያ የብአዴን ካድሬዎች ያሉት ናቸው ይሄንን እያደረጉ ያሉት!!! የእነሱ ፍላጎት አሻጥረኛው፣ ሴረኛው፣ ሸፍጠኛው፣ መሠሪው፣ አረመኔው፣ አሸባሪው ወያኔ/ኢሕአዴግ በሽፍንፍን፣ በድብቅብቅ፣ ሕዝብ የሚሠራበትን ሳያውቅ፣ ሳይሰማ፣ ጥንቃቄና ዝግጅት ሳያደርግ ምስቅልቅል ላይ እንዲወድቅ ለማድረግ፣ እንዲሁም ነቅቶ ሴራቸውን ሳያደናቅፍ ወያኔ/ኢሕአዴግ የሚያደርገውን አድርጎ ድራማውን እንዲያጠናቅቅና ምስለኔዎቹን ወይም ታማኝ ባለአደራዎቹን እነ ዐቢይን አሰናብቶ ድንገት አራት ኩሎ ጉብ እንዲል ነው!!!
እግዚአብሔር ያሳያቹህ ግልጽ በሚታይ አሻጥርና ሴራ እያስጨፈጨፈን እያስበላን እንደሆነ በግልጽ ያየነውንና ያወቅነውን አገዛዝ አስቀድሞም ከመተከል እስከ ወለጋ፣ ከአጣዬ እስከ ሻሸመኔ መከላከያንና ልዩ ኃይሉን ሳይቀር አሰልፎ ሲጨፈጭፈን፣ ሲያፈናቅለን፣ ሲዘርፈንና ንብረት ሲያወድምብን የከረመውን አሸባሪ የወያኔ ቅጥረኛ ጭፍራን እኮነው “እመኑትና ዝም በሉ!” እያሉን ያሉት!!! አይገርሟቹህም???
አገዛዙ እንዲህ ዓይነት ግፍ የፈጸመብን ባይሆንና “ዝም በሉ መንግሥትን እመኑት!” ቢሉን እንኳ ኖሮ ባማረባቸው እኛም በተቀበልናቸው ነበር፡፡ ነገር ግን በየስፍራው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ሲፈጽምብን፣ ሲያፈናቅለንና ንብረት ሲያወድምብን የቆየውንና አሁንም በተለያዩ ስፍራዎች ይሄንኑ ግፍ እየፈጸመብን ያለውን አሸባሪ የጥፋት ኃይል “ዝም ብላቹህ እመኑት!” ማለት “ዓይናቹህን ጨፍኑና እናሞኛቹህ!” ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡ ከሁሉም ነገራቸው የሚገርመኝ ድርቅናቸው ነው፡፡ ለነገሩ ተረቱስ የሚለው “የሌባ ዓይነደረቅ መልሶ ልብ ያወልቅ!” አይደል የሚለው???
ሰው እንዴት የራሱን፣ የቤተሰቡን የሀገሩን ጉዳይ “አያገባህም ዝም በል!” ይባላል??? ጉዳዩ የእነሱ ጉዳይ ብቻ ቢሆን እንኳ “እሽ!” ብለን ዝም ባልን ነበር፡፡ ነገር ግን ሰው እንዴት የራሱ፣ የቤተሰቡ፣ የሀገሩ ህልውናና ደኅንነት ጉዳይ የሆነውንና ሕዝብ እየተጨፈጨፈ፣ ወገኑ ቤተሰቡ የሚጨፈጨፍበትን ሰው “ዝም ጭጭ ብለህ እለቅ እንጅ ምንም ነገር አትተንፍስ አትናገር!” ለማለት ድፍረቱን ከየት እንዳገኙትና ድንቁርናቸው ነው የሚገርመኝ!!!
እንዴት እንዲህ ይባላል??? ሲሆን ሲሆን ሰብአዊነት ተሰምቷቸው የሚፈጸምብንን ግፍ እነሱም ባጋለጡልን መልካም ነበር፡፡ ይሄንን ማድረግ ባይችሉ እንኳ እንዴት “ዝም ብላቹህ በደላቹህን ማንም ሳያውቅላቹህ እለቁ!” ይባላል??? ይሄ በሰው ቁስል ላይ እንጨት መስደድ አይሆንም ወይ??? ይሄ empathy ማጣት ወይም የሰው ችግርን እንደራስ አለማየት ወይም በሰለባ ወገኖች ጫማ ሆኖ ጉዳትን ለማየት አለመፈለግ አይደለም ወይ??? ለመሆኑ ሰው ለእናንተ እንዲህ ቢሆንባቹህ ምን ይሰማቹሃል???
ሲጀመር ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለን ነገር ከሕዝብ መደበቅ ይቻላል ወይ??? ለምንስ ነው የሚደበቀው??? ኢሳቶችማ ጭራሽ “ፌስቡክ ይዘጋ ስልክም ይቋረጥ!” እያአሉ ነው፡፡ ወገኖቸ የእነኝህ ነውረኞች ነገር አይግረማቹህ! እነዚህ ነውረኞች እኮ ወገን በተቀነባበረ ጥቃት በየስፍራው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ሲፈጸምበትና እኛ ይሄንን ስንናገር ስናጋልጥ “ዝም በሉ!” ሲሉን የነበሩና በወገን ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ለመደበቅ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ከዚያም አልፈው “የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ አልተፈጸመም!” በማለት የአረመኔ አሸባሪዎችን ወንጀል ለመደበቅና ሕዝብ ፍትሕ እንዳያገኝ ለማድረግ ሲጥሩ የከረሙ ከሆዳቸው በስተቀር ሌላ ምንም የማያውቁ ነውረኞች እኮናቸው!!! ከእነኝህ ጉዶች ታዲያ ምን ይጠበቃል???
አንዳንድ እነኝህ ቅጥረኞች ያጃጃሏቸው ቂሎች ደግሞ ምን ይላሉ መሰላቹህ “መንግሥት ወያኔን እስከ ቆቦና ዛሪማ ድረስ እንዲገባ ያደረገው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወያኔ በእነዚህ ስፍራዎች የሚፈጽመውን ግፍና ጭፍጨፋ እንዲያይ በማድረግ የወያኔን ማንነት እንዲያውቅ እንዲረዳ ለማድረግ ነውና መታገስ አለብን!” ሲሉ ይሰማሉ፡፡ አይገርሙም???
አንደኛ ነገር የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወያኔ በማይካድራ የፈጸመውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ አውቆ የለም ወይ??? ግን ለይምሰል “ሕውሓትን በዚህ ድርጊቱ እናወግዛለን!” አሉና ደገፉት እንጅ ይሄ አሸባሪ የጥፋት ኃይል እንዲጠፋ ፈረዱበት ወይ??? የወያኔ አረመኔነትንስ ሠላሳ ዓመት ሙሉ ሲታዘቡና ለይምሰልም ቢሆን በመግለጫዎቻቸውም ሲያወግዙት የኖሩት አይደሉም ወይ??? አሜሪካ እራሷ ወያኔን በአሸባሪ ቡድንነት ፈርጃው አልነበረም ወይ???
ሁለተኛ ደግሞ እንዲህ የሚሉ ሰዎች ይሄ ከአገዛዙ የተሰጣቸው ሸፍጠኛ ምክንያት እውነት ቢመስላቸው እንኳ ወያኔ እየፈጃቸው ያሉ ወገኖቻችን የእነሱ ቤተሰቦች ቢሆኑ ነፍሳቸው እንዲህ ለመቆመሪያነት ፍጆታ እንዲውል ፈቅደው “የወያኔን አረመኔነት ለማሳየት ነውና ታገሱ!” ይሉ ነበረ ወይ??? ስለሆነም ቅጥረኞቹ ከአገዛዙ የተሰጣቸው ይሄ ምክንያት አዲስ የሚያሳየው የወያኔ ባሕርይ ወይም ማንነት የሌለ በመሆኑ አማራን ለማስፈጀት ሽፋን እንዲሆን የተሰጠ የውሸት ምክንያት ነው!!!
እነኝህ ቅጥረኞች ለወራት ያህል “ወያኔ ተደምስሶ ሥርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል! ከዚህ በኋላ ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል ወያኔ ተመልሶ አይመጣም! የእከሌ አንገት ተቆረጠ፣ እከሌ በድሮን ጥቃት ድምጥማጡ ጠፋ!” ምንንትስ ቅብርጥስ እያሉ የወያኔን የማዘናጊያና የማጃጃያ ወሬዎችን ተቀብለው በማስተጋባት ሕዝብን ሲያጃጅሉና ሲያዘናጉ እንዳልቆዩ ሁሉ አሁን ወደ መጨረሻ ደግሞ ጥቂት እንኳ ሳያፍሩ ምን ማለት ጀምረዋል “ሞቷል ተቀብሯል!” ያሉትን ወያኔን “ወያኔ እንኳንና ወልዲያና ደባርቅ አዲስ አበባ ቢገባም እንደገና ከዜሮ ተነሥተን ማሸነፍ እንችላለን፡፡ ጣሊያንም ለአምስት ዓመት ኢትዮጵያን ተቆጣጥሮ ነበር!” ምንንትስ በማለት የወያኔን አዲስ አበባ የመግባትን ዜና ሕዝብ እንዲላመደው እያደረጉ ይገኛሉ!!!
ይሄንን ነገር ከቅጥረኞችና ከካድሬዎች እየተቀበሉ የሚያስተጋቡ የዋሃንን መጠየቅ የምፈልገው ነገር ቢኖር እነ ዐቢይ የወያኔ ቅጥረኞችና በወያኔ የሚታዘዙ መሆናቸውን የማታውቁ የዋሃን ሆይ! ለመሆኑ “ወያኔ ተመልሶ አራት ኪሎ ገባ!” ካላቹህና ሀገሪቱን ከተቆጣጠረ “የት ሆነን ሠልጥነን፣ የት ሆነን ተደራጅተንና ታጥቀን ወያኔን ወግተነው እንደመስሰዋለን!” ብላቹህ አስባቹህ ነው የቅጥረኞችን የማታለያና የማጃጃያ ወሬ አምናቹህ ተቀብላቹህ እናንተም መልሳቹህ ልታስተጋቡ የቻላቹህት???
በወቅቱ በተደጋጋሚ እንደነገርኳቹህ ወያኔ በእነ ባራክ ኦባማና ከዚያም በፊት ሲያደርገው እንደኖረው ሁሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደፈለገ እየረገጠና እየጨፈጨፈ እንዲገዛ የሚፈቅድለትና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ተጽእኖ እንዳይደርስበት የሚከላከልለት መንግሥት በአሜሪካ ስላልነበረ ወይም የትራምፕ መንግሥት ወያኔ ከአሜሪካ የለመደውን ድጋፍና ሽፋን ስለነፈገው የሚደግፈው የዲሞክራቶች መንግሥት እስኪመጣለት ድረስ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለውጥ በሚል አታሎ ሕዝባዊ ዐመፁን እንዲተው ለማድረግ በማሰብ የለውጥ ድራማ አምጥቶ እነ አቶ ዐቢይን በምስለኔነት እስቀምጦ ዞር እስካለበት ጊዜ ድረስ ለ27 ዓመታት ሙሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ ቀፍድዶ ይዞ መፈናፈኛ በማሳጣት እንኳንና የትጥቅ ትግል ለማድረግ የሚቻልበትን ስፍራና ክፍተት ሊተው ይቅርና ሰው የገዛ ጥላውን እንኳ እንዳያምን አድርጎ በፍርሐት ቆፈን ጠፍንጎ ይዞ ሲገዛ እንደነበረ አታውቁምና ነው ወይ አሁን “ወያኔ እንደገና የኢትዮጵያ መንግሥት ቢሆንም ከዜሮ ተነሥተን ተዋግተን እናሸንፋለን!” የሚለውን የካድሬዎችንና የቅጥረኞችን የማጃጃያ ወሬ አምናቹህ ተቀብላቹህ የምታወሩት??? ፀረ ሕዝብ ፀረ አማሮቹ ብአዴን፣ ኦሕዴድ፣ ደኢሕዴንና ሌሎቹ የወያኔ አህዮች ወይም ዘበኞች በየት በኩል አፈናፍነውህ ነው “ይሄንን ማድረግ እንችላለን!” ብላቹህ ልታስቡ የቻላቹህት???
አየ ጉድ! በዚህች ሀገር እንደናንተ ያለው ደንቆሮ በዝቶ እኮነው የማንም መጫወቻና መቀለጃ ሆነን የቀረነው!!! ብቻ ግን ምድረ ዘገምተኛ ዛሬም ከቁም ቅዠትህ ላለመንቃት የምታደርገው ጥረት በጣም ገርሞኛል!!! እጅግ በጣም ያሳዝናል!!!
ወያኔ ድጋፍ የሚሰጡትና እንደፈለገ ቀጥቅጦ እንዲገዛ የሚፈቅዱለት የዲሞክራተቶች መንግሥት በአሜሪካ መቀመጡን ተከትሎ ለውጥ ብሎ ሲተውንብን የከረመው ድራማ የውሸት እንደነበረ በማያስታውቅ ሁኔታ በምታዩት መልኩ ተዋግቶና አሸንፎ የተመለሰ ለማስመሰል የምታዩትን የውሸት ጦርነት እየተወነብን ይገኛል!!!
ይሄው ነው እንግዲህ እውነቱ! ይሄንንም አስቀድሜ ከመጀመሪያው ጀምሬ እያንዳንዷን ሴራ እየተነተንኩ ስነግርህ ሳስጠነቅቅህ ነበረ አልሰማ አልክ እንጅ!!!
Filed in: Amharic