>

አሸባሪው ሃይል መቀሌ ከተማ ላይ ያደረሳቸው ጉዳቶች፦

አሸባሪው ሃይል መቀሌ ከተማ ላይ ያደረሳቸው ጉዳቶች፦


➜ዳቦ የሚጋግሩ የዳቦ ማሽኖች የሸረሪት ድር አድርቶባቸዋል።
➜”ለሰፈሩና ለከተማው የበረሃ ከሰል ሲያከፋፍሉ የኖሩ የከባድ መኪና ሹፌሮች በብርድ የሚንገበገቡ ሆነዋል
➜መንግሥት የለሽ እና ደሞዝ አልባ መንግሥት ሠራተኞች ተፈጥረዋል፤
➜የስንዴ እንጀራ ዋጋ አምሳ ብር በመሆኑ የተነሳ በፌስታል የሚሄደው እንጀራው ሳይሆን ብሩ ሆኗል።
➜ትልልቅ እንግዶችን ሲያስተናግዱ የነበሩ ባለ ኮከብ ሆቴሎች የሽብር ቡድኑ መሪዎች ነፍስ ያላወቁ ልጃገረዶችን የሚደፍሩባቸው ቤርጎዎች ሆነዋል።
➜ውስኪ የሚርከፈከፍባቸው ናይት ክለቦች ካቲካላ የሚጠርርባቸው መሸታ ቤቶች ለመሆን ተገድደዋል።
➜የእርዳታ እህል ለማግኘት የሚፈልጉ ወላጆች አሸባሪ ቡድኑ ባወጣው አዲስ ሕግ መሠረት ልጃቸውን ወደ ጦርነት መሸኘት ግድ ብሏቸዋል።
➜የአሸባሪውን ፕሮፖጋንዳ ሲያሰራጩ የኖሩ ቴሌቪዥኖች በሃይል እጥረት ምክንያት ግድግዳ ላይ የተለጠፉ ጥቁር መስታዎቶች ሆነው ቀርተዋል፤
➜ቡናና ሻይ መጠጣት ውስኪ የመጠጣት ያህል ከብዷል።
➜ከጦርነቱ በፊት አሸባሪው ክላሽ አስይዞ በየአደባባዩ ሲያስጨፍራቸው የነበሩ እናቶች ዛሬ የባዶ ቤታቸውን በር ከፍተው ወደ ጦርነት የሄዱ ልጆቻቸውን የሚጠብቁ ሆነዋል፤
➜ከተማው ውስጥ ሲፏልሉ የኖሩ ዘመናዊ መኪኖች በነዳጅ እጥረት ምክንያት አንድ ቦታ ተገትረው ጎማቸው ላይ ሳር በቅሎባቸዋል፤
➜ሌባና ዘራፊ በመስፋፋቱ የተነሳ እነዚያ የጌጣ ጌጥ መሸጫ ሱቆች “ወርቅ ቤት” የሚል ታፔላ የተለጠፈባቸው መኖሪያ ቤቶች ሆነዋል፤
➜ሥልጣን ያላቸው ሰዎች መፈንጫ የነበረው ከተማ በጉልበተኞች ቁጥጥር ስር በመውደቁ የተነሳ ሽሮ የሚሸጡ ምግብ ቤቶች “ቅድሚያ ሒሳብ ይክፈሉ” የሚል ማስታወቂያዎችን ለመለጠፍ ተገድደዋል።
➜ፍራፍሬና አትክልት ከከበሩ ማዕድናት ተርታ ሰፍረዋል፤
➜ሲዘንጡ ውለው የሚያድሩ ቀበጦች ፆታዊ ጥቃት በመበራከቱ የተነሳ ከግቢያቸውና ከቤታቸው የማይወጡ ሆነዋል፤
➜ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር ሲያስተናግዱ የኖሩ ባንኮች የዘበኛ ቤቶች ለመሆን ተገድደዋል።
በአጠቃላይ ከጌታቸው ረዳ ንግግር ውጭ ያለው ነገር በሙሉ እጅግ የሚያሳዝን ሆኖባቸዋል።
 የትሕነግ አሸባሪ ወገኖቻችን ላይ ያደረሰውን ጉዳት ለሁሉም  እናሳውቅላቸው።
አሳዬ ደርቤ
Filed in: Amharic