>

ቅርስ ማውደምን የዴሞግራፊ ቅየራው አካል አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የኦሮሙማ መንግስት "ኮሜርስ ካላፈረስኩ" እያለ ነው....!!! (ሀብታሙ አያሌው)

ቅርስ ማውደምን የዴሞግራፊ ቅየራው አካል አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የኦሮሙማ መንግስት “ኮሜርስ ካላፈረስኩ” እያለ ነው….!!!
ሀብታሙ አያሌው

በቅርስነት የተመዘገበውን ሁሉ እየመረጠ ካላወደምኩ የሚል ቡድን የመንግሥትን ስልጣን ተቆጣጥሮ  በየሳምንቱ  ቅርስ ለማዳን ግብግብ ሆነ፣ ወይ ፈተናችን መብዛቱ።  ኢትዮጵያ በታሪኳ እንደዚህ ባሉ መዓተኞች እጅ ወድቃ አታውቅም።  አገር በጦርነት  እየታመሰ ከተማውስጥ ቅርስ አውድመው መሬት ለመሸጥ ይረባረባሉ።
ታሪካዊ ህንጻ  እና ተማሪ ቤት ተብሎ የተመዘገበው ኮሜርስ ይፍረስ ብለው ሽር ጉድ እያሉ ነው። አዳነች አቤቤ እጅሽን ሰብስቢ።
በተለይ ኮሜርስ  የተማራችሁ፣  ያስተማራችሁ፣ የቅርስ ጥበቃ ኃላፊዎች  እና በዘርፉ የምትሰሩ ማህበራት፣ አገር ወዳድ ተቆርቋሪዎች ሁሉ ድምፃችሁን አሰሙ።  የህግ ባለሙያ የሆናችሁ በፍርድ ቤት ክስ መስርቱና ይሄንን በጥድፊያ የማፍረስ ፍላጎት ቢያንስ  በእግድ እንዲዘገይ ተረባረቡ።
Filed in: Amharic