>

የፌዴራል መንግስት መግለጫና መሬት ላይ ያለው ሃቅ...!!! (ጎበዜ ሲሳይ)

የፌዴራል መንግስት መግለጫና መሬት ላይ ያለው ሃቅ…!!!

ጎበዜ ሲሳይ

የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢለኔ ስዩም  በሰጡት መግለጫ አሸባሪው ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች በተከታታይነት ትንኮሳ እየፈጸመ  ነው ሲሉ መናገራቸው  ይታወሳል።
ታጣቂው ቡድን በአማራ እና በአፋር ሁለቱ  ክልሎች የተለያዩ ወረዳዎችን እና ቀበሌዎችን ይዞ የህዝቡን ሐብት እና ንብረት እየዘረፈ ፤ ወጣቶችን አድኖ  እየገደለ እና  ገበሬውን ስንቅ እና መሳሪያ በማሸክም አስገድዶ ከኋላው በማስከተል  ዘመቻ በከፈተበት ወቅት መንግስት ትንኮሳ ነው በሚል እያቃለለው ይገኛል።
በሌላ በኩል  ደግሞ ቀደም ሲል የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ለክልሉ ሕዝብ የክተት ጥሪ ባስተላለፉበት ወቅት ሕወሓት ወረራ እየፈጸመብን ነው ። ሕልውናችንም  አደጋ ላይ ነው ማለታቸው ይታወሳል።
ይህም የፌዴራሉ እና የክልሉ መንግስት ችግሩን እኩል ክብደት እንዳልሰጡት ያመላክታል።
ያም አለ ይህ የራያ እና ቆቦ ወረዳ (ከ50 ቀበሌዎች በላይ ይኖር የነበረ  ህዝብ) ተፈናቅሎ በወልዲያ እና በመርሳ እንድሁም በደሴ ከተማ  በችግር ላይ ይገኛል።
Filed in: Amharic