>
5:33 pm - Wednesday December 6, 9076

ልታድን የተነሳህዉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ከሆነ ታሸንፋለህ ! (ሸንቁጥ አየለ)

ልታድን የተነሳህዉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ከሆነ ታሸንፋለህ !

ሸንቁጥ አየለ

ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር ናት::የኢትዮጵያ ህዝብም የእግዚአብሄር ነዉ::ይሄን የሚያምን ሀይል በእግዚአብሄር ሀይል ያሸንፋል::ተቆርጦ የሚድን ወይም ተቆርጦ የሚጠፋ  ነገድ የለም::
ወያኔዎች 27 አመታት እንዲሁም ኦህዴዶች አራት አመታት የሞከሩት አንዱን ኢትዮጵያዊ አድኖ ሌላዉን ማጥፋት ነዉ::በወያኔ እና በኦህዴድ መርህ መሰረትም አማራ ነገድን:ክርስቲያን ተዋህዶን እና ኢትዮጵያዊነት እሴት ተሸካሚ ሀይላትን እናጠፋለን የሚል ምናምንቴ ሀሳብ አራምደዋል::እያራመዱም ነዉ::ግን ይሄ ሀሳብ ከሰይጣን ነዉና አልሰራም::አይሰራምም::
እናም አንዱን ነገድ አጥፍቶ አንዱን ነገድ ማዳን አይሰራም:: ትግሬዉም:አማራዉም:ኦሮሞዉም:አፋሩም:ሲዳማዉም:ወላይታዉም:ሶማሌዉም በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የእግዚአብሄር ህዝብ ነዉና በኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳይ ባለቤት እግዚአብሄር ነዉ::
ኢትዮጵያዊ ሁሉ የእግዚአብሄር ነዉ ሲባል የአጋንንት መንፈስ የገራቸዉ ሰዎች/በተለይም ከምዕራባዉያን ክህሎትን ከመማር ይልቅ ሀሰተኛ የፖለቲካ አሉባልታን የተማሩ የፖለቲካ ቀሻቢዎች/ የሚጮሁት ጩህት ኢትዮጵያዊነትን ለክርስቲያን ኦርትዶክሶች ወይም ለአማሮች ጠቅልለዉ ሰጡብን እያሉ ነዉ::
የእግዚአብሄር ሀሳብ ግን እንደሱ አይደለም::በመዝሙር ዳዊት:በነቢያት መጽሃፍት በአዲስ ኪዳን መጽሃፍት ስለ ኢትዮጵያዊነት እግዚአብሄር ሲናገር ስለ አይሁድ ወይም ስለ ክርስቲያን ወይም ስለ ሙስሊም ወይም ስለ ኢአማኝ  አይደም::ስለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በአጠቃላይ እንጂ::
ስለሆነም የእግዚአብሄር  ሀይል እንዲረዳህ ከፈለግህ ኢትዮጵያን ሁሉ አድን::ኢትዮጵያን ሁሉ ጠቅልለህ ዉረስ::የነገድ ፖለቲካን ሁሉ ከስሩ ነቅለህ ጣል:: ራዕይህም ኢትዮጵያን ለማዳን የተሰነቀ ይሁን::ወታደራዊ ስልጠናዎችህ:ወይም የፖለቲካ ርዕዮት አለምህ ብሎም የፖለቲካ ፕሮግራምህ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ሁሉ ለማዳን የተቀመረ ይሁን::
ይሄ እንዴት ይሆናል አትበለኝ::መልሴ የሚሆነዉ ከአምላክህ ጋር ተነጋገር የሚል ነዉ::
ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ያድናታል::እዉነተኛ ኢትዮጵያዊ ከሆንክ አሜን እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ያድናት የሚል ሀይል እዉስጥህ ሲዘምር ታደምጣለህ::
እግዚአብሄር በዘመናት ሁሉ የተመሰገነ ይሁን !
Filed in: Amharic