>

ኢትዮጵያን የሚያስፈልጋት ሌላ ጥገናዊ ለውጥ ወይስ ስር ነቀል? (ጎዳና ያእቆብ)

ኢትዮጵያን የሚያስፈልጋት ሌላ ጥገናዊ ለውጥ ወይስ ስር ነቀል?

ጎዳና ያእቆብ

 

* 4 ኪሎን መቆጣጠር እና የማእከላዊ መንግስቱን ስልጣን መልሰን መቆጣጠር አንፈልግም ጀነራል ፃድቃን ብለዋል:: 
(1) ስንቶቻችሁ ይህንን ንግግር ታምናላችሁ::
(2) ካመናችሁ ጦርነቱ ላይ ያለውን አመለካከት ይቀይረዋል ወይስ አይቀይረውም?
** ፌደራል መንግስቱ በሚስጥር እንወያይ እያለን ነው እኛ ግን ውይይቱ ይፋ ይሁን ብለናል ማለቱን እንዴት ታዩታላችሁ?
 
*** የትግራይ ተወላጆች ብቻ ሳይሆን ሁሉም የፓለቲካ እስረኞች ይፈቱ የሚል የውይይት ቅድመ ሁኔታ ተቀባይነት ቢያገኝና እነ እስክንድር ነጋ: ስንታየሁ ቸኮል: ቀለብ ስዩም እና አስካለ ደምለው ቢፈቱ ምን ይሰማችኃል? በሌላ ወገን ደግሞ እነ ጃዋር መሀመድ በቀለ ገርባና ሌሎች የኦሮሚያን እስር ቤት ያጨናነቁ እስረኞች ቢፈቱስ?
*** ሁሉን አቀፍ ውይይት ብለው ቀድመው ያወጡትም ቅድመ ሁኔታ (አሁንም በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ የደገሙት) የሲቪል ማኅበረሰብን: የሀይማኖት አባቶችን: የሀገር ሽማግሌዎችን: በህዝብ የተወከሉ ግለሰቦችንና ብድኖችን የሚያካትት አልመሰለኝም:: የፓለቲካ ፓርቲዎችን ብቻ ያካተተ በይዘቱ በቂ ያይደለና ሁሉን ባለድርሻ አካላትን ያላካተተ መሆኑ 1983ን የሚደግም አይመስልም? በሌላ አነጋገር ሁሉን ያላቀፈና የኢትዮጵያን እጣ ፋንታ በፓለቲካ ሀይሎች የሚበዙት ብሔር ተኮር እና ነፃ አዊጪ ግንባር መሆናቸውና አሁንም ውህድ ማንነት ያላቸውና ኢትዮጵያንስት የሆኑ ሀይሎች ፍፁም የማይወከሉበት አይሆንም? ከሆነስ ህገራችን የገባችበትን ጣጣ መልሶ የሚያመጣ አይሆንም?
**** ወልቃይት እና ራያን መለለስ (status quo ante bellum) እንደቅድመ ሁኔታ አለማቅረባቸውስ የሚለውጠው ጭንቅላት ይኖራል?
***** ውይይቱና ድርድሩ አይቀሬ ነውና እንዴት መወያየት እንዳለባቸው: ቀይ መስመሮቹ ምን እንደሆኑ ሁሉም ተወያዮች እያሰቡበት ነው ወይስ የፓለቲካ ቀውስን በጦርነት እንፈታለን የሚለው ገዢ ሀሳብ ሆኖ ይቀጥላል?
****** የሰማንታ ፓወር ወደ ኢትዮጵያ ጎዞና ልክመጣ ያለው ጠንካራ ማእቀብ ለውይይት ገፊ ምክንያት ይሆናል?
******* በቤንሻንጉል: በኦሮሚያ: በማይካድራ በማንነታቸው ብቻ የፈሰሰው ለአማራ  ደም ፍትህ መጠየቅ እና የህግ ተጠያቂነትን ማምጣት የውይይቱ አካል ይሆናል ወይስ ደማቸው ደመከልብ ሆኖ ይቀራል?
******* በኦሮሚያ ነፃ እርምጃ የተወሰደባቸውና በእምነታቸው ደማቸው ለፈሰሰው እንዲሁም በእስር ለሚንገላቱት ፍትህ ይጠየቃል ወይስ ተጠያቂ አካላት ከፍትህ በማናለብኝነት አምልጠው በምቾትና በስልጣን ይቀጥላሉ?
******* የጎሳ ፌደራሊዝም መጨረሻው ምን ይሆናል?
*** የጎሳ ፌደራሊዝሙ መዋቅራዊ የተደረገበት ህገ መንግስትስ መጨረሻው ምን ይሆን?
***** የአማራ የፓለቲካ ሀይልስ between Scylla and Charybdis እንደሆነ ይቀጥላል ወይስ ለለውጥ የማኅበረሰቡን ጥቅም ለማስከበር የራስጅን አቋም ይይዛል?
Filed in: Amharic