>

አቶ አብነት ገብረመስቀል ከሚድሮክ ግሩፕ ተባረሩ!!(ማለዳ ኔትዎርክ)

አቶ አብነት ገብረመስቀል ከሚድሮክ ግሩፕ ተባረሩ!!

ማለዳ ኔትዎርክ

 

  አቶ አብነት ገብረመስቀል ከሚድሮክ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ተነሱ
 ቦታቸውን የተረከቡት አዲሱ የሚድሮክ አለቃ አቶ አብነት በቱጃሩ አል አሙዲ መባረራቸውን ይናገራሉ
 እሑድ ሐምሌ 25፣ 2013
የቱጃሩ ሼይኽ መሐመድ አል አሙዲ ታማኝ ሰው ነበሩ የሚባሉት አቶ አብነት ገብረመስቀል ከሚድሮክ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኃላፊነት መነሳታቸው ተነግሯል።
ፎርቹን ይዞት በወጣው ዘገባ አቶ አብነት ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸውን መልቀቃቸውን ቢገልጹም፣ እርሳቸውን የተኩት አቶ ጀማል አሕመድ ግን አቶ አብነት በቱጃሩ ውሳኔ እንዲነሱ መደረጋቸውንና ለዚህ ሰበቡ ደግሞ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ አለመወጣት ነው ብለዋል።
ከአል አሙዲ ጋር ከሠላሳ ዓመታት በላይ የዘለቀ ወዳጅነት አላቸው የተባሉት አቶ አብነት የሚድሮክ ዋና ሥራ አስፈጻሚነትን ከቀድሞው አለቃ ዶክተር አረጋ ይርዳው የተረከቡት አምና በዚህ ወቅት ነበር።
የዛሬ 35 ዓመት ገደማ በዋሺንግተን የተዋወቁት አል አሙዲ እና አብነት ግንኙነታቸው ተበላሽቶ ከሐምሌ 8፣ 2013 ጀምሮ የኩባንያው ውክልናቸው መሰረዙ ነው የተነገረው።
አዲሱ ተሿሚ አቶ ጀማል አሕመድ እምነት በማጉደል በአል አሙዲ ተባረዋል ያሏቸውን የአቶ አብነት ሥልጣን ወደ እርሳቸው መዞሩን አረጋግጠዋል።
አቶ አብነት በኃላፊነት በቆዩባቸው በሚድሮክ ግሩፕና በሸራተን አሥተዳደር ቦርድ አመራርነት ዘመናቸው ከፍተኛ የሀብት ምዝበራ መፈጸማቸው ዘገባዎች ያመለክታሉ።
በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑት የሳዑዲ ዐረቢያ ዜግነት ያላቸው የሼይኽ መሐመድ ሑሴን አል አሙዲ ንብረት የሆነው ሚድሮክ ኢትዮጵያ በስሩ ከሰማንያ በላይ ድርጅቶችን ያቀፈ ነው።
Filed in: Amharic