>

ያልተሳካው ሴራ...!! አወድ መሀመድ

ያልተሳካው ሴራ…!!

አወድ መሀመድ

ምህራባውያኑ ሀገራችንን ኢትዮጵያን ለማፍረስ በፕሮጀክት ደረጃ C2FC በሚል ያወቀሩት ቡድን ዓለማ ሳይሳካላቸው በከፊልም ቢሆን መክኖ ቀርቶዋል። አሁንም ቢሆን ይህ ሀይል ከዚህ የጥፋት ሴራው ሙሉ ለሙሉ አልታቀበም። እኛም ይህንኑ ተገንዝበን በሀገራችን ጉዳይ እንደቀድሞውኑ በአንድነት መቆም ይገባናል። እስከ አሁንም ድረስ እየመጣብን ያለውን ክፉ ሴራ እያከሸፍነው ያለው በአንድነት መቆማችን ሞሆኑ ጥርጥር የለውም። ይህን መረጃ ያወጣው ድህረ ገፅ “ጂኦፖለቲክስ ፕሬስ” ይባላል ድህረ ገፁን በፌስቡክ መውጣት እንዳይችል ፌስቡክ ያገደው ሲሆን እናንተ ግን ከፍቶ ለማየት ካስፈለጋቹ በክሮም በኩል ገብታቹ እንድትመለከቱት ከጹሁፉ መጨረሻ ላይ አስቀምጠዋለው።
ከታች ያለውን ትርጉሙን የወሰድኩተ ከዘሐበሻ ነው
C2FC ን በጨረፍታ!
.
ህወሀት ጦርነቱን ከቆሰቆሰ ከሰባት ቀናት በኋላ ኖቬምበር 10 ቀን 2020 የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት በምስጢር ተሰብስበው በኢትዮጵያ ጉዳይ መነጋገራቸውን በመጥቀስ ጂኦፖለቲክስ ፕሬስ ዘገባውን ጀምሯል፡፡ ከስብሰባው በኋላም ባለሰባት ገፅ ሪፖርት የወጣ ሲሆን በዚህ ሪፖርት ላይ ኢትዮጵያ እንደምትበታተን እንዳሰመረበት የጠቆመው ዘገባው ይህ ደግሞ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞችን ወደአውሮፓ ሊያፈልስ እንደሚችል ማሳሰቡን አውስቷል፡፡
በተጨማሪም ሪፓርቱ የኢትዮጵያውን አብይ አህመድ፣ የኤርትራውን ኢሳያስ አፈወርቂና የሶማሊያውን መሀመድ አብዱላሂ መሀመድ የሶስትዮሽ ጥምረት ማፍረስ እንደሚያስፈልግ ማስጠንቀቁን አስረድቷል፡፡ ይህ ግጭት ወደባህረሰላጤው አገራት ሊስፋፋ ይችላል የሚለውን የሳኡዲአረቢያን ስጋትና ዩናይትድ አረብ ኤመሬትስም የምትጋራውን ይህንን ስጋት ከግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚያስፈልግም የአውሮፓ ህብረት በምስጢር ባደረጉት ስብሰባ የተስማሙበት ጉዳይ እንደነበር ዘገባው አስታውቋል፡፡
ሌላው ምእራባዊያኑ የተወያዩበት አጀንዳ የኢትዮጵያ ቀጣይ እጣ ፈንታ እንደነበርም አስረድቷል፡፡ ‹‹በዚህ ውይይት ታጣቂዎቹ(ማለትም ህወሀት) አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩና ክልሎች የራሳቸውን እድል የመወሰን መብታቸውን ተጠቅመው በድምፀ ውሳኔ ኢትዮጵያን በሰላማዊ መንገድ ሊገነጣጥሏት ይችላሉ የሚለው ስምምነት የተደረሰበት ነበር›› ያለው ዘገባው ይህም በሱማሌያ ያለውን አይነት ለፌዴራል መንግስት የማይገዛ ከፊል ነፃ አገር እንዳይመሰረት እንደሚያደርገው ማመናቸውን አስታውቋል፡፡
ይህ የምእራባዊያን እቅድ ቢሳካ ደግሞ ዘገባው እንደገለፀው አሜሪካና የአውሮፓ አጋሮቿ ዩጎዝላዊያን የመሰለ ሰላማዊ መገነጣጠል ፈፅመው እንደዩጎዝላቪያው የመጨረሻው ፕሬዝደንት ስሎቦዳን ሚሎዚቪች አብይ አህመድን አለም አቀፍ ፍርድ ቤት የማቅረብ እቅድ ነበራቸው፡፡ ዘገባው አሜሪካና አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ የያዙትን ይህንን አጀንዳ ለማስፈፀም እንዴት እየተንቀሳሱ እንደሆነም በዝርዝር አቅርቧል፡፡
 እንዳስረዳውም ባስማን የመሰለ ‹‹ኮማንድ ኤንድ ኮንትሮል ፊውዥን ሴንተር›› ወይንም በምህፃረ ቃል (ሲቱኤፍሲ #C2FC ) የተሰኘ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ በስራ ላይ ይገኛል፡፡ ሲቱኤፍሲ ራሱን የቻለ የተወሰነ ድርጅታዊ ነፃነት ያለው አካል ሲሆን የተሰጠው ግዳጅም ጠቅለል ብሎ ሲገለፅ ማስተባበር፣ አቅም መገንባት፣ ማማከርና መሰለል ናቸው፡፡
አቅም በመገንባት በኩል የመረጃን ፍሰት በመጠቅል ማናቸውንም የፕሮፓጋንዳ ስራ መስራት እንደሆነ ዘገባው አስረድቷል፡፡ ለዚህም እንዲረዳው ሲቱኤፍሲ የኢትዮጵያን ግጭት በተመለከተ በሚሰራጩ ዘገባዎች ላይ የኢትዮጵያን መንግስት በሚያጣጥሉና የትግራይና የኦሮሚያ ታጣቂዎችን በሚጠቅሙ መንገድ ዜናዎችን እየለወጠ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል፡፡
 ግብረ ሀይሉ ይህንን የሚያከናውነው ኬንያ ከሚገኙ ተባባሪዎቹ ጋር በመሆን እንደሆነ የጠቆመው ዘገባው በተጨማሪም በኬንያ ውስጥ የኦሮሚያ የሽግግር መንግስትና የትግራይ መንግስት ለማቋቋም እንዲቻል በግል የደህንነት ድርጅቶች አማካኝነት ለአክቲቪስቶችና ለፕሮሞተሮች ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልጿል፡፡
 ሲቱኤፍሲ በተሰኘው ግብረ ሀይል ውስጥ ታዋቂ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ምሁራን፣ ጠበቆች፣ የዲሞክራሲ አክቲቪስቶች፣ የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች፣ የግል የደህንነት ተቋማት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንደሚገኙበት የገለፀው ዘገባው ከእነዚህ መካከል የአውሮፓ የአፍሪካ የውጭ ፕሮግራም አንዱ እንደሆነ አስረድቷል፡፡ እነዚህ በግብረ ሀይሉ ውስጥ ያሉት ሰዎችና ድርጅቶች የሚገኙትም በኢትዮጵያ፣ በኬንያ፣ በታንዛኒያ፣ በሶማሊያና በኡጋንዳ ሲሆን ከአፍሪካ ውጭም በአውሮፓ፣ ኦሺያና ሰሜን አሜሪካ የሚገኙ እንደሆነም ጠቅሷል፡፡
ሲቱኤፍሲ የስለላ አክቲቪስቶችንና ገዳይ ጋዜጠኞችን ያካተተ መሆኑን ያስረዳው ዘገባው የግብረ ሀይሉ አባላት ማናቸውንም ኢትዮጵያን የተመለከቱ መረጃዎችን እንደሚሰስቡ አስታውቋል፡፡ እነዚህን መረጃዎች ከማህበራዊ ሚዲያ፣ ከህወሀት ካድሬዎች፣ ከጦርነቱ ተጎጂዎችና ከትግራይ ዲያስፖራዎች እንደሚያገኙም አመልክቷል፡፡
እነዚህን መረጃዎች ባሻቸው ጊዜ መረጃን ለማዛባትና ሀሰተኛ ዜናን ለማሰራጨት እንደሚጠቀሙበት የገለፀው ዘገባው የሲቱኤፍሲ አባላት ዋነኛ አላማ የኢትዮጵያን መንግስት ከስልጣን ለማስወገድ ማናቸውንም ኪሳራ ቢያከትለም የገዳይ ጋዜጠኝነት ተግባር ላይ መሰማራት እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በቅርቡ አዲስ ስታንዳርድ በተሰኘው ሚዲያ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ቅጣት ጥሎ በነበረበት ወቅት ምእራባዊያን ያደረጉት የተቃውሞ መረባረብ ሲቱኤፍሲ ምን ያህል ተፅእኖ የመፍጠር አቅም እንዳለው እንደሚያሳይም አመልክቷል፡፡
ይህ አይነቱ ድርጊት ባስማ በሚል መጠሪያ በሶሪያ ውስጥ መከናወኑን ዘገባው ጨምሮ አውስቷል፡፡  ሲቱኤፍሲን በተመለከተ መረጃዎችን እየተከታተልን ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡ በተለይም አዲስ አበባ ውስጥ ተቀምጠው በጋዜጠኝነት ሽፋን የአገርን ሚስጥር እየሰለሉ ስላሉ የሲቱኤፍሲ አባላት የምንለው ይኖረናል።
Filed in: Amharic