>

የዳኛው ስብዕና...!!! (ጌጥዬ ያለው)

የዳኛው ስብዕና…!!!

ጌጥዬ ያለው

ይሄ ሰው እንዳሻው አዳነ ይባላል። በወያኔ ዘመን የፅናትና ሀቀኝነት ተምሳሌቱ #እስክንድር ነጋ በሀሰት ሲከሰስ 18 ዓመት የፈረደበት የያንጊዜው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ነው። ይህንን የሀሰት ክስ ተቀብሎ በመፍረዱ የሹመት ዕድገት አኝቶ ዛሬ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኗል።
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ  ፍፁም ሀሰተኛ ክስ ቀርቦባቸው በዐቃቤ ሕግ (ዐቃቤ መንግሥት)፣  በእስር ፍርድ ቤት እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት ቅብብሎሽ ሲንገላቱ ከአንድ አመት በላይ ሆኗቸዋል። ዘንድሮም በዚህ ጊዜ ውስጥ እንዳሻው ዳኛ ነው።
Filed in: Amharic