>

ለትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ የትኛው ወደብ ይቀርባል⁉ (አቻምየለህ ታምሩ)

ለትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ የትኛው ወደብ ይቀርባል⁉

አቻምየለህ ታምሩ

• ለመቀሌ ከ1 ሺህ 306.8  ኪሎ ሜትር እና ከ398 ኪሎ ሜትር ርቀት የቱ ይቀርባታል ⁉
ወደ ትግራይ ርዳታ ለማድረስ በሱዳን በኩል ሰብዓዊ መተላለፊያ  (humanitarian corridor) ይከፈት የሚለው ግፊት ግቡ ትግራይ ውስጥ ሰብዓዊ ርዳታ ማድረስን አላማ ያደረገ ከሆነ ወደ ትግራይ ሰብዓዊ ርዳታ ለማድረስ የሚቀርበው ኤትርራ በመሆኑ ሰብዓዊ መተላለፊያው በኤትርራ በኩል እንዲከፈትና ከምጽዋ ወደብ ወደ ትግራይ ርዳታውን በሰዓታት ውስጥ እንዲጓጓዝ በማድረግ ሰብዓዊ ድጋፉ ለትግራይ ወገናችን ባስቸኳይ እንዲዲደርስ ማድረግ ይቻላል በሚል ትናንትና የሰጠሁት ምክረ ሀሳብ እዚያ መንደር ቁጣ ቀስቅሷል። የሰጠሁት ምክረ ሀሳብ እዚያ መንደር የቀሰቀሰው ቁጣ በግልጽ የሚያሳየው ሰዎቹ ሰብዓዊ መተላለፊያውን የሚፈልጉት ሰብዓዊ ርዳታ ባስቸኳይ ለትግራይ ሕዝብ ለማድረስ አለመሆኑን ነው።
አንድ አንድ ምዕራባዊያን አገራትና ተቋሞቻቸው ከሱዳን ወደ ትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ለማጓጓዝ መተላለፊያ  ኮሪደር ይከፈት ሲሉ መንግስት አጥብቀው ይጠይቃሉ።
የአሸባሪው ህወሓት አመራሮችም በተለይም አፈቀላጤው ጌታቸው ረዳ እና ጻድቃን ገ/ትንሳኤ በሱዳን በኩል ለተረጂዎች እርዳታ ለማስገባት መተላለፊያ ኮሪደር ለማስከፈት መንግስት ላይ ጫና እንፈጥራለን ሲሉ መናገራቸውም ይታወቃል።
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ሳማንታ ፓወር በተመሳሳይ ይህ ኮሪደር ይከፈት ዘንድ በአካባቢው ያለው የአማራ ሀይል ለቆ ይውጣ ሲሉ በግልጽ ተናግረዋል።
ለመሆኑ ለትግራይ ክልል እርዳታ ለማቅረብ የትኛው ወደብ ይቀርባል….⁉
• ከፖርት ሱዳን  መቀሌ 1 ሺህ 306.8 ኪሎ ሜትር ሲረዝም በተሽከርካሪ በአማካይ 17 ሰአት ከ36 ደቂቃ ይወስዳል፤
• ከጅቡቲ መቀሌ 779 .1  ኪሎ ሜትር ሲረዝም በተሽከርካሪ በአማካይ 12 ሰአት ይወስዳል፤
• ከምጽዋ መቀሌ 398 ኪሎ ሜትር ሲረዝም በተሽከርካሪ በአማካይ 5 ሰአት ከ31 ደቂቃ ብቻ ይወስዳል፤
ታዲያ ጥያቄው ለተረጂዎች የሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ ብቻ ከሆነ ዓላማው እነዚህ አገራት እና ተቋሞቻቸው ለ ምን ሩቁን የፖርት ሱዳን ወደብ የሙጥኝ አሉ ⁉
እርዳታ ለማቅረብስ የቱ ይቀርባል⁉
Filed in: Amharic