>

የወልዲያ ባህርዳር መንገድ ተቆርጧል ሰሜን ወሎ በሙሉ በህወሃት ተይዟል (ቬሮኒካ መላኩ)

የወልዲያ ባህርዳር መንገድ ተቆርጧል
ሰሜን ወሎ በሙሉ በህወሃት ተይዟል
ቬሮኒካ መላኩ

ወልዲያ  ሙሉ በሙሉ  ተከባለች- ይህንን  ያህል  እርቀት  እየተጋዘች ባለችበት  ሁኔታ  መከላከያ ተብዬው ከመፈርጠጥና መሪያቸው  አቢይ  ተብዬውም   ዝም  ከማለት  በስትቀር  የታየ  ነገር  የለም:: ከሁሉም   በላይ  አደናቋሪው  ነገር  ደግሞ  የእኛ ወገን  ሆነው   “ዝም በሉ”  እያሉ  መንግስት  ተብዬውን  ስራ  እንመልከት  እንደግፍ የሚሉ  ሀሞተ ቢስ  ድምፆች  ጉዳይ  ነው::   እነዚህ  ድምፆች የመከኑ ሀሞት የለሽ  የአማራ ጠላቶች  ድምፅ  ነው:::
 እየተፈፀመ ያለውን ሴራ የአማራ ህዝብ ለምን ማየት አቃተው? 
1. ያለምንም ወጊያ 8 የአማራ ክልል ወረዳዎች በአሸባሪው ቁጥጥር ሥር እሥኪውሉ መከላከያ ያለውን ከብድ መሳርያዎች ለህወሃት እያስረከበ ያለምም ውጊያ ወደ ኋላ ሲሸሽ ነበር! አሁንም መሸሹን ቀጥሏል!! ለምን!!?
2. ስልታዊ ማፈግፈግ ነው ብለን እንዳንቀበል አሸባሪው በሚወራቸው አካባቢ መጠነ ሰፊ እና አስከፊ ጭፍጨፋ በህዝብ ለአይ ይፈፅማል ፣ እናቶችንና ህፃናት ይደፍራል፤ ወጣቶችን ይረሽናል፤ ንብረት ይዘርፍል፤ ያወድማል!! ታዲያ ይሄን ሁሉ ለሚያደርግ አሸባሪ አይደለም ይሄን ሁሉ ወረዳ አንዲት የገጠር ከተማ እንኳን ለቀህለት የሚትሄድ ቡድን አደለም!! እንደዚህ አይነት ስልታዊ ማፈግፈግ ነው እንዳንለው ከሚሊተሪ ሳይንስ ህግ በተቃራኒ ነው!
3. በትጥቅና በዝግጅት እንዲሁም በአመራሮች ሙሉ የነበረውን ትህነግ መደምሠሥ ተችሎ ነበር አሁን ቅሪቱን ለመጨረሥ እንዴት መንግሥት አቅም አጣ!!?
4. ወታደሩና ልዩ ሀይሉ ማጥቃት ሲጀምሩ አቁመው ወደኋላ እንዲሸሹ የሚደረገው ለምንድን ነው!
5. ወታደሩ ለምን smart phone ይዞ ግንባር እንዲገባ  ተደረገ!? ይህን አመራሮቹ ለምን አላስቆሙትም!?
6. የልዩ ሀይሉ አመራሮች በስልክ ብቻ ትዛዝ እንዲያስተላልፉ የሚደረገው የሳተላይት መገናኛ ሬዲዮ ጠፍቶ ነው ወይ!?
7. ከመከላከያው በፊት ጦሩን በትነውት ወደኋላ የሚሸሹት የጦሩ አዛXኦች ናቸው? ለምሳኤ ከታች በፎቶው የሚታየው የጦር አዛዥ ትናንት ማክሰኞ ኦገስት 3 ቀን 2021 ሀራ ላይ  የነበረው  የመከላከያ  አዛዥ  መሳሪያውን ለወያኔ አስረክቦ ሲፈረጥጥ  በህዝብ ጥቆማ  መርሳ ላይ  እንዲያዝ  ተደርጏል፡፡ የጦር አዛዡ ጥሩን የሚመራውን ጦር በትኖ እና መሳሪያውን ሁሉ ለወያኔ አስርከቦ ወደ ኋላ የሚሸሸው ለምንድን ነው?
ከታች በፎቶው የምታዩአቸው እና በቢጫ ቀለም የተከበቡት ወያኔዎች የተቆጣጠሯቸው የአማራ አካባቢዎች እና ትልልቅ ከትሞች ናቸው!!
እየሆነ ያለው ሁኔታ እውነታው ለምን ለአማራ ህዝብ በግልጽ አይነገረውም??
Filed in: Amharic