>

ነጥቦችን ስንገጣጥማቸው የሚከስቱት ምስል... ብዙ መልስ አልባ ጥያቄዎች...?!? (ዘመድኩን በቀለ)

ነጥቦችን ስንገጣጥማቸው የሚከስቱት ምስል… ብዙ መልስ አልባ ጥያቄዎች…?!?

ዘመድኩን በቀለ

“… በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት… በባድመ የጦር ግንባር ከጓዶቼ ጋር በሬድዮ የመገናኛ አገልግሎት በመስጠት በሥራ ተጠምደን ነበር። ከባድ ውጊያ እየተካሄደም ነበር። ቅልጥ ያለ ውጊያ። … ኋላ ላይ አሉ ጠቅላዩ… ኋላ ላይ እኔ ውኃ ሽንት መጣኝና በዚያውም ወገቤንም ልፈትሽ ብዬ ከጓዶቼ ተነጥዬ ወደ አንድ ሸጥ ውስጥ ዞር አልኩ። ሰከንድም አልቆየ፣ ወዲያውኑ ከሻአቢያ በኩል የተተኮሰ ከባድ መሣሪያ ጓደኞቼ በነበሩበት ሥፍራ ላይ ወደቀ። ከሽንት ቤት ስመለስ ጓደኞቼ በሙሉ እንዳልሆነ ሆነው ሞተው ጠበቁኝ። እጃቸው፣ እግራቸው፣ በየቦታው ተበታትኖም ነበር። ይዘገንንም ነበር ብለው የነገሩን ያለፈ ታሪክ ዛሬ ለምን ትዝ እንዳለኝ እንጃ።
… በራዲዮ መገናኛ ላይ መሥራታቸው… ሽንታቸው መጥቶ እሳቸው ዞር እንዳሉ ሻአቢያ ከባድ መሳሪያ አነጣጥሮ ተኩሶ ጓዶቻቸውን በሙሉ ማውደሙ… ኢንሳ እያሉ በሃገር ክህደት የተከሰሰን የኦነግ የጦር መሪን ለማዳን ይጻጻፉ ለማስመለጥም ይጥሩ እንደነበር የሰማነውም ከራሳቸው ከመሪያችን አንደበት ነው። ዛሬም መሪያችን የመገናኛ ራዲዮኑን መጠቀማቸው መቸም አይቀርም አይደል?
… ሃሎ ደብረ ጽ…  በሎም… ዐማራን በሎም። ላሊበላ ግባ… ከቆቦ አስወጥቼልሃሎ… በጋሸና በኩል ማንም የለም። ያለውም ሚኒሻ ነው በሎም። ደምስሰው። ሙጃን ተቆጣጠር። ስንቅና ትጥቅ ራያ ላይ አስቀምጬልሃለሁ። ወደፊት ግፋ። በአፋር በኩል የምር እናስመስለው። ትንሽ እንጠዛጠዝ። በጎንደር በኩል ትንሽ ያዝ እናድርግ። በሎም ደብረ ጺ የሚልማ አለ። ከምር መጠርጠር ደግ ነው።
… መከላከያ የሚታዘዘው በጠሚው ነው። ያውም በመገናኛ ራዲዮ። ሽሽ፣ አምልጥ፣ አፈግፍግ የሚሉትም እርሳቸው ናቸው። የዐማራ ልዩ ኃይልን የሚያዙት ደግሞ አገኞ ተሻገር ናቸው። ጋሽ አገኞን የሚያዘው ደግሞ አለቃው ጠሚዶኮው ነው። ያልገባኝ ነገር መከላከያውም ልዩ ኃይሉም ከሸሸ፣ ከፈረጠጠ፣ ካመለጠ ሚኒሻውን ዝመት የሚሉት የዘመተውን ሚኒሻ ማን ሊያዋጋው ነው?  ክተቱ ለማኖ? እንደወልድያ ወጣት በድንጋይ ወያኔን ግጠማት የሚሉ ጭፍን ካድሬዎችን ስታይ ደግሞ ወደላይ ቋቅ ነው የሚልህ። በመከላከያ መድፍ ያልቆመችዋ ሂዊ በድንጋይ የምትቆመው የታች ሰፈር ልጃገረድ ናት እንዴ? በዚህ ድንጋይ አናትሽን ሳልበረቅስሽ ተመለሽ ሲል ይታያችሁ። ከዚያ ህወሓት ፈርታ እየሮጠች ወደ መቀሌ። አይ የብአዴንና የኦህዴድ ካድሬ ነገር።
… የሚደንቀው ነገር አሁን ዐማራ እና የዐማራ ህዝብ የማይዋጋውን ጥሎት የሚሸሸውን የሃገር መከላከያ ሠራዊቱን ወጥሮ ይቀልባል። ልዋጋ እያለ ልቀቅ፣ ሽሽ እየተባለ የሚሸሸውን ልዩ ኃይሉንም ይቀልባል። እግር ሁላ እያጠበ ነው እኮ እየሳመ የሚለማመጠው።  ከጎጃም፣ ከሸዋ፣ ወሎና ጎንደር በግድ ከእርሻው ላይ አንሥተው እንዲዘምት ያደረጉትን ሚኒሻም ይቀልባል። ከክልሎች ተውጣጥቶ ዐማራ ክልል የተከማቸውን ልዩ ኃይል ተብዬም ይቀልባል። መዋጮውም እንዳለ ነው። ወይ መከራ።
… ይቆይና ያ ተቀላቢው፣ ሰንጋ ሲታረድለት የከረመው የመከላከያ ሠራዊት በስልታዊ ማፈግፍግ ሰበብ ወደኋላ ከሸመጠጠ በኋላ የተራበው የህወሓት ሠራዊት እዚያው ዐማራ ህዝብ ላይ አናቱ ላይ መልሶ ይፈስሳል። ደሀው ዐማራም በተራው ህወሓትን ይቀልባል። ትቶት ለሚሸሸውም ባንዲራ አንጥፎ፣ ድንጋይ ኮልኩሎ ይለምነዋል። ወርሮ ለያዘውም ለህወሓት በተራው በዋቃውን አራግፎ ይቀልበዋል። እንደ ዘንድሮ ዐማራ ላይ መዓት ወርዶበትም የሚያውቅ አይመስለኝም። ኦህዴድ፣ ብአዴንና፣ ህወሓት የሌለ ነው ተጠቃቅሰው የሚጫወቱበት።
… ዐማራን በኢኮኖሚ ድቅቅ። በዘዴ ከዐማራው ገበሬ ላይ የጦር መሣሪያውንም ስብስብ፣ ግፍፍ ነው ያደረጉት። በሰላሙ ጊዜ መሣሪያህን አስረክብ ሲሉት የማይሰማን ዐማራ የህልውና ዘመቻ ብለው በግድ ወጥረው ገፋፍተው ወደ ጦር ገንባር ወስደው ከመትረየስም ፊት አቁመው፣ ምስኪኑን ገበሬ ከፊትም ከኋላም ነፃ እርምጃ ወስደው ገድለው ነው የገፈፉት። ከጎጃም፣ ከሸዋ ያለውን ገበሬሁላ ትግራይ ድንበር ወስደው ራቅ አድርገው ነው የቀበሩት። የሚገርመው ነገር ደግሞ በአጋጣሚ እንደ ድንገት የሚደመሰስ የህወሓት ጦር ሲገኝና ሲማረክ የጦር መሣሪያውን የሚረከበው ደግሞ የሚሸሸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊቱ ነው። ጉድ እኮ ነው። ሰራዊቱ አይዋጋም፣ እየሸሸ ሌሎች በቆመህ ጠብቀኝ ተዋግተው የሚማረኩትን የጦር መሳሪያ ለመረከብ ግን አንደኛ ነው። አይ አቢቹ የሥራህን ይስጥህ።
… ዐቢይ አሕመድ መጨረሻውን ያሳምርለት እንጂ በዐማራ ጠሉ ኢዜማና በሻአቢያ አማካሪዎቹ ምክር ሰሜኑን ትግሬና ዐማራን የማድቀቁ ነገር የተሳካለት ይመስላል። ዐቢይ መጀመሪያ በዐማራው ኃይል ወያኔን አደቀቃት። በሻአቢያ ጦር ትግራይን አወደማት። የሸአቢያ እስላም ተዋጊዎች የትግራይን ገዳማት አቃጠሉ፣ አፈረሱ፣ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ መነኮሳትና ምእመናንን ረሸኑ። የኦሮሞ የእስላምና የፕሮቴስታንት  ኮሎኔሎች በትግራይ ኦርቶዶክሳውያን በማኅበረ ዶጌ ገዳም ረሸኑ። በማርያም ደንገላት ካህናት ታረዱ። ከደቡብ የዘመተው የደቡብ ዕዝ የፕሮቴስታንት የመከላከያ ሠራዊት የትግራይን ኦርቶዶክስ ጨፈጨፈው። ሸአቢያና ዐቢይ በትግራይ የኦርቶዶክስን ቅርሷን አወደሙ። ቀጥሎ ለደቃቃዋ ወያኔ ወታደርም፣ ስንቅና ትጥቅም እየሰጠ ዐማራውን እንኩቶ እያደረገው ነው። እያደቀቀው ነው። አጀሁን ላሊበላ እየተዘረፈ ነው። በትግራይ በዐቢይ ጦር ተዘርፋ የነበረችው ህወሓት አሁን ራሱ አቢይ መንገዱን አመቻችቶላት ላሊበላን እንዲዘርፉት ሰተት አድርጎ አስገብቷል። ከላሊበላ የሚሰማው ጥሩ አይደለም። ይሄ ሁሉ የፀረ ኢትዮጵያው የዐቢይ አሕመድ ሴራ ነው። አቢቹ እርስ በእርስ አባልቶ፣ አባልቶ፣ መጨረሻ ላይ ምን ሊያደርገን እንዳሰበ ፈጣሪ ይወቀው። አማካሪው ኦርቶዶክሳዊው ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ግን ደህና ነው? ቀሲስ መንግሥቱ ጎበዜ እስቲ ስለ ላሊበላ መረጃ ስጠን።
… የአርቲስት ኮሎኔል ጌትነት አዳነን የዛሬ መግለጫ ብቻ ለምሳሌ እንመልከት። በራያ ግንባር በኩል ፦
በመስክ፣ ድልብ፣ በተኩልሽ፣ በሙጃ እና በጋሸና አካባቢዎች በሽብርተኛ ድርጅትነት የተፈረጀው የህወሓት ቡድን ሰርጎ ገቦች በአካባቢው #ሚሊሻ ድል እየተመቱ ነው። ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀድ ህወሓት ሰርጎ ገቦቹ በወልድያና ቆቦ ጫና ለመፍጠር የገቡ እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን ከአማራ ሚሊሻና ልዩ ኃይል ጋር የመዋጋት አቅም የላቸው ነው ያሉት።
… በጉባ ላፍቶ፣ በሀብሩ፣ በወርቄ፣ በሀራ፣ በደሀና እና ወንዳችም አውደ ውጊያ የአካባቢው ሚሊሻና ወጣቶች ህወሓት ላይ ያደረሱትን ኪሳራ ቡድኑ ከዐማራ ሚሊሻና ልዩ ኃይል ጋር ፊት ለፊት ገጥሞ እንዳማያሸንፍ የታየበት ነው። ከላይ በተገለፁት አካባቢዎች በርካታ የህወሓት ቡድን ሰርጎ ገቦች ከነጦር መሳሪያቸው ጭምር መማረካቸውን ሲናገሩ…
… በሌላ በኩል ይህቺው ህወሓት በአፋር ክልል ጭፍራ እና ሚሌ በኩል ሀገር ለማፍረስ ያደረገው ሙከራም በአፋር ህዝብና #ልዩኃይል፣ #በፌደራልፖሊስና  #በሀገርመከላከያሠራዊት የመከላከል ርምጃ መክሸፉን ነው አርቲስት ኮሎኔሌ ጌትነት አዳነ የገለጹት። በአፋር በኩል ሃገር ስለሚፈርስ ራሱ ዐቢይ አሕመድ ጭምር ዘምቶ ይዋጋል። በዐማራ በኩል ደግሞ ኤታባቱንስና ለምን አይወድምም ወጣቶች በድንጋይ ሂዊን እያጣደፉ ነው ይለናል መከላከያችን። ስለ ቅዱስ ላሊበላ ኮሎኔል ጌትነትም ጮጋ ነው ያሉት። አገኘሁ ተሻገርም በወልቃይት አይምጡበት እንጂ ለምን ባህርዳርን አይዙትም። ኬሬዳሽ ይመስላል። አቤት እንዴት እንዳቆላለፏቸው እኮ የመድኃኔዓለም ያለህ። የጎንደር አክቲቪስት፣ የወሎን ሲሰድብ ይውላል። በድንጋይ አትዋጉም እያለ ያላግጣል። እነ መስከረም አበራ ራሱ ጠፍተዋል። ተማረኩ ይሆን እንዴ? መስከረም አበራ ጴንጤ ናት። ስለ ላሊበላ ምን ብላ ትጻፍ ብለህ ነው አለኝ አንዱ። ከምር የት ጠፋች ግን? መስኪዬ ብቅ በይ በሞቴ። እኔ የምፈራው ግን በላሊበላ ዐቢይና ህወሓት የሆነ ነገር  መጥፎ ነገር ፈጥረው የኢትዮጵያን ምድር አኬልዳማ የደም መሬት እንዳያደርጓት ነው። እሱ ነው ስጋቴ። የፈረንሳይ መንግሥት ለላሊበላ የሰጠውን ብር እንደሆነ አንዴ ተበልቷል። የጦር መሳሪያ ለሸኔ ተገዝቶበታል የሚሉም አሉ።
… ዐቢይ አሕመድ በሚደንቅ ሁኔታ ዐማራውን ዙሪያውን አስከብቦታል። ሱዳን ራሷ እና በሱዳን ሳምሪ የተባለ የሂዊ ሳምሪ ሌላ ስጋት እንዲሆንበት ጠላት ተክሎበታል። የጉምዝ ታጣቂዎች የጎጃም ዐማራን እየተገተጉት ነው። በወለጋ የዐቢይ ሸኔ ሥራውን እየሠራ ነው። ሰሜን ወሎ በጅራፍ እና በጊንጥ እየተገረፈ ነው። ሸዋ የተደገሰለትን እንጃ። ድቅቅ ነው ሰሜኑን ያደረገው። ኦሮሚያ ግን እስከ አሁን ሰላም ናት። ልማት ላይ ናት። የትምህርት ቤት ግንባታ ላይ ናት። ኦሮሞዎቹ እንዲያውም ለሁለት ተከፍለው ዐማራና ትግሬን እየደገፉ እያበረታቱም ነው። ኦህዴድ በርታ ዐማራ፣ አይዞን፣ ቻልአድርገው እያለ ዐማራ በባዶ ሆዱ በድንጋይና በዱላ እንዲዋጋ ሲያበረታታው እና ሲደግፈው። ኦነግ ደግሞ በበኩሉ በርቺ ትግሬ፣ ወጥሪ ሂዊ፣ አጆሃ፣ ጀባዱ እያለ ህወሓት እየደገፈ ይገኛል። ኢዜማ ይስቃል። ጮቤ ይረግጣል። ከዳር ቆሞም ቦሎም ይላል። መከላከያን የሚመሩ፣ አብዛኛዎቹ አዋጊ ጀነራሎች፣ የመገናኛ ራዲዮ አገልጋዮች እነማን እንደሆኑም ይታወቃል። አምልጥ፣ ሽሽ፣ ንካው እያለም እንደ ግሪሳ ዐማራን አጋፍጦ የሚወጣውም ማን እንደሆነ ይታወቃል። በራያ ግንባር ከህወሓት ወገን ሆነው የሚዋጉ ኦነጎች መማረክ መገደላቸውንም የሰማነው በቅርቡ ነው። ወይ መሳሪያውን አይሰጡት፣ ወይ አይዋጉ አይጠብቁት፣ መፈርጠጥ ብቻ። ጭራሽ በድንጋይ ግጠማት አላለም። እሱ መትረየስ ይዞ እየሮጠ የዐማራን ገበሬ በዱላ ግጠም። ወይ ቀልድ።
… ሌላው ኢትዮጵያዊ ደግሞ እንዲህ እያሰበ፣ እየሆነም ነው። የትደረሱ እያለ የሚጠይቀኝን ቤቱ ይቁጠረው። ጨረቃ ላይ ሆኜ ወደታች የማይ የሚመስለው ነፍ ነው። አሹ ሥጋቤት ኪሎውን በ1ሺ ብር እየቆመጠ ዘመዴ ህወሓት የትደረሰች በእናትህ፣ ምንም መረጃ አጣን እኮ ከሚል ጎፍላም ይሰውራችሁ። ጦርነቱ አፍንጫው ስር ደርሶ እሱ ምንተዳዬም ያለው የበለፀገውንም ቤቱ ይቁጠረው። በአፋር ግንባር የሬሳ ክምር ፎቶም እየደረሰኝ ነው። በጣም ነው የሚዘገንነው። እሱን እያየሁ የካድሬን ቀልድ ስሰማ ይዘገንነኛል።
… የተቀረው ምስኪን ዜጋ ደግሞ በመዋጮው በቁሙ እንዲዝግ እየተደረገ ነው። ያላዋጣ ድርጅቱ እየታሸገም ነው። ጦርነቱ ለሕጋዊ ዘራፊዎች ሎቶሪ ነው ያወጣላቸው። በጁንታ ስም እየታሰሩ ብር እየከፈሉ የሚለቀቁም እልፍ ናቸው ተብሏል። ትግሬ ከሆንክ ትያዛለህ፣ ገንዘብ ካለህ እዚያው ተደራድረህ ትለቀቃለህ፣ ከሌለህ የለህም ትባላለህ። በዚህ ላይ ህዝብ አርቴፊሻል የሆነ የኑሮ ጫና እየተፈጠረበት ይገኛል። አንድም የዐቢይ መንግሥት ሃገር መምራት ከብዶታል። አንድም በአሻጥር አዙረው በአፍጢሙ ሊደፉት የደረሱ ኃይላት መሃል ሃገር ተሰይመው እየገዘገዙት ነው። ሲመስለኝ ከጦርነቱ ይልቅ የዐቢይ ታዬ ደንደአን መንግሥትን የሚያስወግደው የሰሜኑ ጦርነት ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱ የኑሮ ውድነት ራሱ ጭምር ይመስለኛል። ማርክ ማይወርድ አለ አጎቴ ሌኒን።
• አሁን የልጆች ትምህርት ቤት ዋጋው ስንት ብር ደረሰ?
• ደብተር፣ ጫማ፣ ዩኒፎርሙ ስንት ገባ?
• የቤት ኪራዩስ?
• ዘይት?
• መኮሮኒ?
• ፓስታ?
• ዱቄት?
• ምስር?
• ስኳር?
• ሳሙና?
• ሙዝ፣ ቡርቱካን፣ ማንጎ፣ ፓዬ፣ አናናስ፣ አፕል…
• ሽንኩርት፣ ድንች፣ ጎመን፣ ሰላጣ፣ ካሮት?
• ሥጋን እርሱት፣ ጤፍም ይቅር፣
• ዳቦ ስንት ገባ?
• ትራንስፖርት ስንት ደረሰ?
• ጨው እንኳ በአቅሟ የትናየት ደረሰች?
• የማገዶ እንጨት አንዷ ፍልጥ 20 ብር ከገባች…
• መብራት ክፍያው ገራሚ አስማት ሆኗል ተብሏል።
• ውኃ የለም።
• የሞባይል ካርድ ብቻ ነው አሉ እንዳለ ያለው። ባለ 10፣ ባለ 50፣ ባለ መቶ…
… ይሄን በቅጡ የሚመራ አዋቂ በሌለበት ሃገር፣ ካድሬ ሃገር ሲመራ ገና ከዚህ በላይ ብዙ ይጠበቃል። ካድሬ ሆድ እንጂ መች ጭንቅላት አለው የሚሉም አሉ። ሃኣ
… ኦቦሌሶ ዶላር ስንት ገባ? ዩሮስ ስንት ደረሰ? የሸቀጣ ሸቀጥ አስመጪዎች ዶላር ኢንጅሩ ተብለዋል። ንግድ ቀዝቅዟል። በብላሽ የሚጋየውና በውድ ዋጋ ያውም በውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ መጥቶ ለህወሓት በስጦታ የሚበረከተውም የጦር መሣሪያ የሚገዛው በዶላር ነው። አቢቹ መቼም ቀልዱ አይጠገብም። የሃገር ደም እያፈሰሰ፣ እሱ በመርፌ ግማሽ ሊትር ደም እየተቀዳ የሚያሳይ ፎቶ ለጥፎ ይሳለቃል። ችግኝ እየተከለ ሰው ይነቅላል። የሳዳም ሁሴንና የጋዳፊን መጨረሻም የሚያውቅ አይመስለኝም እንዳልል የቦለጢቃ ሊቅ ነው። እናም ነገርየው ግራ የሚያጋባ ነው። ከምር ዶላር ስንት ገባ ነው ያላችሁኝ? በዚንባቡዌ ስንስቅ ከርመን ውሎ ሳያድር ዐቢቹ የዚንቡዋቤ መሳቂያ ሊያደርገን ነው አይደል?
… ለማንኛውም የራበው ህዝብ መሪውን ይበላል የሚባለው አበባባል በቅርቡ በተግባር ይታያል። ራብ ጥጋቡም፣ ለቅሶና አምባውም ወደ ቤተ መንግሥትም በቅርቡ ይገባል። ወዳጄ ራብ ክፉ ነው። በራብ ከመሞት በሰይፍ መሞት ይመረጣል። ገበሬ ዘምቶ እንዲሞት፣ እንዲማረክ ተደርጓል። አሁን አምራቹም ምርትም የለም። አምራች አካባቢ የሚገኙ ገበሬዎች ማዳበሪያ ስላላገኙ ዘንድሮ ምርት የለም። ቡቃያውም የዘንድሮው ያስፈራል ነው የሚባለው። መጪው ዓመት ከዘንድሮው በእጅጉ ያስፈራል።
… ዐማራና ትግሬን አድቅቄ እገዛለሁ የሚለው ቁማር የተባነነበት ጊዜ፣ የከሸፈ ጊዜ ነው ያኔ ሁሉን ማየት። ትግሬና ዐማራ ተስማምቶ ለሂዊ የማርያም መንገድ የተሰጣት ጊዜ ያኔ ነው ሁሉን ማየት። የፕሮቴስታንትና የእስላም አክቲቪስቶችን መጨረሻ ሳታሰየኝ አትግደለኝ ብላችሁ ጸልዩ። ከበሮ እኮ ነው እየደለቁ ያሉት። ሃሌሉያ እያሉ እኮ ነው። ሂዊ እያለች ይሄ አይሆንም እንጂ ሁለቱ የተስማሙ ጊዜ የዐቢቹም፣ የእነ ሽሜና የኢዜማ ቁማር ውኃ ነው የሚበላው። አሁን መደማመጥ ስለሌለ ሰሚም የለም። ለመስማት ደግሞ በደንብ መራብ፣ መቸገር እና መድቀቅ አለብን። ደክሞን አረፍ አረፍ ካላልን በቀር እንዲህ እየተዋከብን፣ እየተናናቅን፣ መስማት፣ መምከር፣ መደማመጥም አልተቻለም። አዎ መጀመሪያ በደንብ በራብ፣ መጠውለግ፣ መኮርኮም፣ ማዘን፣ ማልቀስ አለብን። በደንብ መዠለጥ አለብን። በሜካፕ ያበዱትን የብልጥግና ሰዎችን በደንብ እንድንለያቸው እኛ መጀመሪያ መጠውለግ፣ ከንፈራችን መድረቅ፣ መሰነጣጠቅ አለበት። በየቤቱ ዋይ ዋይ የሚል ህዝብ መፈጠርም አለበት።
… ያኔ ነው የአቶ ደመቀ መኮንን እንጆሪ የመሰለ ጉንጭ፣ የጠሚዶኮ ዐቢይ አሕመድና የቀዳማዊት እመቤት ጎንደሬዋ ዝኑ ቦንቦሊኖ ኡምንዱኖኢሹ የመሰለ የቤተመንግሥት ፊት፣ የወሮ ሙፈሪያት ካሚል ዱንቡሼ ገላ ያቡርቱካኔ ኮ የመሰለ ጉንጭ፣ የላቀ አያሌው ወዝ፣ የገዱ አንዳርጋቸው ቅንድብ፣ የአምባሳድር ዲና ሙፍቲ፣ የሬድዋን ደንደን ያለ ሻኛ አንገት፣ የቢልለኔ ስዩም ጠሐይ የመሰለ አብረቅራቂ ፊት፣ የመንገድ ትራንስፖርቷ የሐረር ሰንጋ የመሰለ ዳሌ፣ የሞዴሊት ሞዴላ ሞዴሎቹ የወሮ አዳነች አበቤ እና የታከለ ኡማ  የፋሽን ትርኢት፣ የሽመልስ አብዲሳ ድል ያለ ሠርግ የሚታይህ በደንብ ስትደቅ ነው። አንተ ተርበህ በሰፈርህ እየጨፈረ በዳንኪራ እየደነከረ የሚያመሸው ካድሬ ሁሉ ያነዜ በዓይንህ ይንከራተታል። ሲርብህ ነው የቴሌዋ የፍርዬ ውበትና የአንተ አመዶ፣ የአሸቦ ዕቃ የመሰለ ፊት በደንብ የሚታይህ። አዎ ዘይት ይናር፣ ጨው ይወደድ፣ መኮሮኒ ይሰቀል፣ ክክ ይከካን። ሂዊ ዱቄቷም ታቡካን ታስቦካን፣ አቢቹም በአናታችን ይትከለን። ታዬ ደንደአም ያሹፍ ይቀልድብን። ይበለኝ የእጄን ነው ያገኘሁት አለ አዝማሪው።
… እነ አበበ ገላውን ግን ብዙ አትስሙአቸው። እነሱ አይርባቸው፣ አይጠማቸው። እነ ጋሽ ነአምን ዘለቀንም ብዙ አትስሟቸው። እነሱም ምንም አያገኛቸው። እነ ታማኝ በየነ እንዲያውም ” ዲያስጶራ ክተት” ብለው ላሜ ቦራ ዲያስጶራውን ሊያልቡት ፕሮጀክት ቀርጸው ሰሞኑን በአዲስ ቢዝነስ ብቅ ሊሉ በዝግጅት ላይ ናቸው አሉ። የፊታችን ቅዳሜ እንዲያውም እነ ሰማኀኝ ጋሹን ሁላ ጨምረው ዲያስጶራ ዐማራው መሰባሰብ መጀመሩን ሊበትኑት መላ ፈጥረው ሊያልቡት የመጀመሪያ ስብሰባቸውን ለማድረግ በዝግጅት ላይ ናቸውም አሉ። የፈረደበት ዐማራ !!
… የሆነስ ሆነና እንዲያው ለመሆኑ ሻአቢያ ግን በዚያን ጊዜ ምን ዓይነት የራዲዮ መረጃ ብታገኝ ነው ጠሚያችን ወደ ሽንት ቤት ሲሄዱ ጠብቃ አነጣጥራ ተኩሳ ኢትዮጵያውያኑን ጓዶቻቸውን ያወደመች። አጋጣሚ ነው? ተአምር ነው? ወይስ ሌላ። ጊዜ ይፍታው። አሜን ሃሌሉያ !!
• ሰላም ዋሉ አምሹልኝም።
Filed in: Amharic