>

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ…!!!

አቻምየለህ ታምሩ

 

ክብር ለወልድያው መሐመድ ያሲን! 
ከዓለም ታሪክ እንደተማርነው የተሻለና ብቃት ያለው መሪ (Charismatic leader) የሚፈጠረው ሕዝብ የኅልውና አደጋ፣ አገር ደግሞ የብተና ስጋት በሚወድቁበት ወቅት ነው። ዓለም በጀግንነታቸው የሚያደንቃቸውን የውትድርና ጠበብት (Military Genius) አምጦ የወለደው አገራቸውና ሕዝባቸው የገቡበት ጭንቅ ነው።
የአገርና የሕዝብ ጭንቅ አምጦ የወለዳቸው እነዚህ መሪዎች የሰጡት ብቃት ያለው አመራር አገሮቻቸው ከብተና፣ ሕዝባቸውን ደግሞ ከዘር ማጥፋት ታድጓል። አገራቸው የጭንቅ ምጥ ስታምጥ ብቅ ብለው ሕዝባቸውን ከዘር ማጥፋትና አገራቸውን ከብተና አደጋ ከታደጉ ዝነኛ የጦር ገበሬዎች መካከል የሩሲያ የውትድርና ጠበብት የሆኑት ጆርጂ ጁክኮቭ እና ኮንስታንቲን ተጠቃሽ ናቸው።
በምዕራቡ ዓለም የውትድርና ጠበብት (Military Genius) እየተባሉ ሲደነቁ የሚኖሩ አይነት ጀግኖች በኢትዮጵያ ምድርም  ያምው በብዛት ተፈጥረው ያውቃሉ። እነዚህን የውትድርና ጠበብት ያገራችን ሰው “የጦር ገበሬ” እያለ በአድናቆት ሲያስታውሳቸው ይኖራል።
በዚህ ወቅትም በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም የአማራ ሕዝብ ጭንቅ የወልድያውን ከንቲባ መሐመድ ያሲንን አምጦ የወለደ ይመስለኛል። አገራችንንና ሕዝባችንን ባጋጠመው አደጋ ውስጥ እንደ ወልድያው መሐመድ ያሲን አይነት ብቃት ያለው አመራር በመስጠት ሕዝባቸውንና አካባቢያቸውን ከፈጽሞ ጥፋት የሚታደጉ የሕዝብ ጭንቅ አምጦ የሚወልዳቸው ሌሎች ጠበብቶች በሌሎች የአገራችን አካባቢዎች ይፈጠሩ ይሆን?
ክብር የሕዝብ ጭንቅ አምጦ ለወለደው ለወልድያው የጦር ገበሬ መሐመድ ያሲን ይሁን!
Filed in: Amharic