>

ሕወሓት የአማራና የአፋር ክክልሎችን ለቅቆ እንደማይወጣ   አስታወቀ...!!! (D W)

ሕወሓት የአማራና የአፋር ክክልሎችን ለቅቆ እንደማይወጣ   አስታወቀ…!!!

D W

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የአማራና የአፋር ክክልሎችን ለቅቆ እንዲወጣ  ዩናይትድ ስቴትስ  ያቀረበችለትን ጥሪ እንደማይቀበል አስታወቀ። የሕወሃት ቃል አቃባይ ጌታቸው  ረዳ የሰብአዊ ተደራሽነትን ጠቅሰው «የተጣለብን እገዳ እስካልተነሳ ድረስ ያንን ማድረግ አንችልም» ብለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት (USAID) ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወርና የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ በትግራይ ያለውን የሰብአዊ ቀውስ ለመፍታት ሕወሓት ከተቆጣጠራቸው የአጎራባች ክልሎች ለቆ እንዲወጣ እና ሁሉም ወገኖች የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጥሪ አድርገው ነበር። የሕወሓት ታጣቂዎች ትናንት ያለ አንዳች ውግያ የላሊበላን ከተማ ከተቆጣጠሩ በኋላ አቶ ጌታቸው እንዳሉት «ላሊበላን መቆጣጠራችን በሰሜን አማራ የሚገኙ መንገዶችን የመቆጣጠር አካል ሆኖ የመንግስት ኃይሎች በድጋሚ እንዳይደራጁ ለመከላከል ያግዘናል » ማለታቸውን የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል።
በተያያዘ የአማራ ክልል ባለስልጣናትም በታሪክ «የአማራ ግዛት አካል» ካሏቸዉ አካባቢዎች ለቀው እንደማይወጡ አስታውቀዋል። የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ የህወሃት ታጣቂዎች በክልሉ ሰላማዊ ሰዎችን እየገደሉ ነው የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶችን እያደረሱ ነው» በማለት ከሰዋል።  የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ  ቃል አቃባይ ቢለኔ ስዩም በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ  በአፋር እና አማራ ክልሎች ጦርነቱን ሽሽት 300,000 ኢትዮጵያውያን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።
Filed in: Amharic