>

ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ደም የሚያስተፋ ንዴትና ቁጣ በማሰማት ይህን አደገኛ ቁማር ማስቆም አለበት!   (አቻምየለህ ታምሩ)

ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ደም የሚያስተፋ ንዴትና ቁጣ በማሰማት ይህን አደገኛ ቁማር ማስቆም አለበት!  
አቻምየለህ ታምሩ

*… ዐቢይ አሕመድና ተላላኪው ብአዴን  ከመጋረጃ ጀርባ በወሎ አማራ ሕዝብ ላይ የሚጫወቱትን ይህን ነውረኛ ቁማር ሕዝብ የማይረዳ ይመስላቸዋል። ድንቄም! ዐቢይ አሕመድ  ፋሽስት ወያኔ ወረራና ውድመት እንድትፈጽም የፈቀደው በአሜሪካኖች ፍራቻ ትግራይ ውስጥ ሆኗል የሚባለው አይነት የወንጀል አቻ ለመፍጠር ነው…!!!
የጸረ ፋሽስት ወያኔ ተጋድሎ ተምሳሌት የሆነችው የሰሜን ወሎ ዋና ከተማ ወልድያ እጅግ አሳሳቢ የሆነ ጭንቅ ላይ ናት። የፋሽስት ወያኔን ወረራ፣ የጅምላ ፍጅትና ውድመት በጥናት እየታገለ ያለው ጀግናው የወልድያና አካባቢው የአማራ ሕዝብ አገዛዙ ባስቸኳይ እንዲደርስና ከተማዋ ከፋሽስት ወያኔ ወረራና ውድመት እንድትተርፍ በተደጋጋሚ ቢማጸንም መንግሥት ተብዮው ከተማዋ ከጥፋት እንድትድን ፍላጎት ስለሌለው ሕዝባችን አሁንም ሌላ ከባድ ዋጋ ለመክፈል ተቃርቧል።
ከኮረም እስከ አላማጣ፤ ከቆቦ እስከ ላሊበላ ድረስ ያለው የወሎ ክፍል በፋሽስት ወያኔ ድጋሜ የተወረረው በፌደራል  መንግሥት ተብዮው ቀጥታ ትዕዛዝና በብአዴን ታዛዥነት ነው። እነ ዐቢይ አሕመድ ከመጋረጃ ጀርባ በሕዝብ ላይ የሚጫወቱትን ይህን ነውረኛ ቁማር ሕዝብ የማይረዳ ይመስላቸዋል። ድንቄም! ዐቢይ አሕመድ በወሎ አማራ ላይ ፋሽስት ወያኔ ወረራና ውድመት እንድትፈጽም የፈቀደው በአሜሪካኖች ፍራቻ ትግራይ ውስጥ ሆኗል የሚባለው አይነት የወንጀል አቻ ለመፍጠር ነው።
ዐቢይ አሕመድ በሕዝብ ላይ እንዲህ አይነት አደገኛ ቁማር ሳይጫወት የፋሽስት ወያኔን አለማቀፍ ወንጀለኛነት ከፍጥረቱ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ሲፈጽማቸው የኖራቸው የዘር ማጥፋት፣ የጦር ወንጀልና ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በማደራጀት፤ በተለይም ደብረ ዘይት የእሬቻ በዓል ሲበበር በኦሮሞ፤  ሎቄ በሲዳማ፤  ጋምቤላ በአኝዋክ፤   ጅግጅጋ  በሶማሌ፤  ባሕር ዳር፣ ማይካድራ፣ ወልቃይት፣ ወዘተ የጅምላ ፍጅት በማካሄድና  ሴቶች እንዳይወልዱ በማምከን በአማራ ላይ  በፈጸማቸውን  የጅምላ ጅፍቶችና የዘር ማጥፋቶች ብቻ በማቅረብ በዓለም ላይ ከተፈጠሩ አሸባሪዎች ሁሉ የከፋ አለማቀፍ ወንጀለኛ መሆኑን ማሳወው ይችል ነበር።
በርግጥ ዐቢይ አሕመድና ተላላኪው ብአዴን ለሕዝብ ስቃይ በተለይም የአማራ ሕዝብ ስቃይና መከራ ደንታቸው እንዳልሆነ፤ ይልቁንም ደስታ እንደሚሰጣቸው እስኪዘገንነን ድረስ ያሳዩን ስለሆነ ትግራይ ውስጥ ተፈጽሟል የሚባለው አይነት የወንጀል አቻ በወሎ የአማራ ሕዝብ ላይ ለመፍጠር የሚጫወቱት አደገኛ ቁማራ አያስገርመን ይሆናል። በተለይ ብአዴን የወሎ አማራ የፋሽስት ወያኔ በቀል ማወራረጃ ያደረገው አካባቢውን የሚያውቁትንና ሕዝቡ በማስተባበር ሊያታግሉ የሚችሉትን የወሎ አማራ የሆኑ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችን ከአሳምነው ጽጌ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ለቃቅሞ በማሰር ጭምር ነው። እነዚህ ወታደራዊ መኮነኖች ድጋሚ በግፍ የታሰሩት በፋሽስት ወያኔ የግፍ ማጎሪያ ውስጥ ዘጠኝ ዓመታት በሚያሳልፉበት ወቅት እንደ አደም መሕመድ አይነት ብአዴኖች አለመሆናቸውንና የሕዝብ ተቆርቋሪ መሆናቸውን በማስመስከራቸው ነው።
እነዚህ የወሎ አማራ የሆኑ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተላላኪው ብአዴን ያለ ፍርድ ድጋሜ በግፍ ከታሰሩ ከሁለት ዓመታት በላይ ሆኗቸዋል። ሰሩት ስለተባሉት ወንጀል እስካሁን የቀረበባቸው ማስረጃ የለም። ፋሽስት ወያኔ ሰሜን ወሎን ሲወርር ሕዝባቸውን ይታደጉ ዘንድ ብአዴን ከእስር ይለቃቸው ዘንድ በተደጋጋሚ አቤት ቢሉም ተላላኪው ብአዴን ግን ሕዝባቸውን እንዲታደጉ ስላልፈለገ ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሊሆን አልቻለም።
ወልድያን ከፋሽስት ወያኔ ውድመትና ወረራ መታደግ የሚቻለው ዐቢይ አሕመድና ተላላኪው ብአዴን በወሎ አማራ ላይ የሚጫወቱን ቅጥ ያጣና ሕጻን ልጅ እንኳን የማይጫወተውን ቁማር ለማስቆም በአገዛዙና ተላላኪው ላይ ደም የሚያስተፋ ንዴትና ቁጣ  ከዳር ዳር ማሰማት ስንችልም ነው። በወሎ አማራ ላይ እየተፈጽመ ያለው አገዛዝ መር ጥቃት በመላው አማራ ብሎም በመላው  የኢትዮጵያውያ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመ ጥቃት ነው!
Filed in: Amharic