>

ጁንታው በአርብቶ አደሮች ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ አስመልክቶ የሶስት ቀን ሀዘን ታውጇል...!!! (የአፋር ክልላዊ መንግስት ህዝብ ግንኙነት)

ጁንታው በአርብቶ አደሮች ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ አስመልክቶ የሶስት ቀን ሀዘን ታውጇል…!!!
 
የአፋር ክልላዊ መንግስት ህዝብ ግንኙነት

አሸባሪው የህወሀት ጁንታ በአፋር ክልል በፈንቲ ረሱ በጋሊኮማ ጊዚያዊ መጠለያ ተጠልለው የነበሩ በንፁሀን አርብቶ አደሮች ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሀዘን ቀን እንዲሆን የአፋር ክልል መንግስት አውጇል።
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አሚና ሴኮ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ  በሰጡት መግለጫ ጁንታው በጋሊኮማ በንፁሀን ላይ ያደረሰው ጭፍጨፋ እጅግ ዘግናኝ እንደነበር ገልፀው የክልሉ መንግስትም ይህን ጥልቅ ሀዘን አስመልክቶ የሶስት ቀናት ሀዘን ማወጁን ገልፀዋል።
ታሪክ የማይረሳው 107 ህፃናትን, 89 ሴቶችን እና 44 አዛውንቶችን ህይወት የቀጠፈውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ያካሄደው የህወሀት ጁንታ ድንገት በከፈተው በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ንፁሃን አርብቶ አደሮች መገደላቸውና መቁሰላቸው እንዲሁም በመጋዝን የነበረ  የአስቸኳይ እርዳታ ሙሉ በሙሉ ማውደሙ ይታወሳል።
ጁንታው ገና ቀድሞ በረሀ እያለ የነበረውን የአፋርን መሬቱ ወደ ራሱ የማካለል ቅዠትን በግርግር መፈፀም የሚያስችለው መስሎት በፈፀመው ወረራ አርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የጥቃት ሰለባ አድርጎታል።
በተለይም በጋሊኮማ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ጥቃት ፈፅሟል አሽባሪው ህወሀት። ይህንንም ዘግናኝ ጭፍጨፋ አስመልክቲ በአፋር ክልል ውስጥ ከዛሬ ነሀሴ 05 /2012 እስከ ነሀሴ 07/2013 ድረስ የሀዘን ቀን እንዲሆንና የአፋር ክልል ባንዲራም ዝቅ  ብሎ እንዲውለበለብ የክልሉ መንግስት ወስኗል።
ይህን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ውድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች  በያሉበት ሆነው እንዲቃወሙና እንዲያወግዙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
Filed in: Amharic