>
5:13 pm - Wednesday April 19, 9139

እየሆነ ያለው ምንድን ነው?  (አቻምየለህ ታምሩ)

እየሆነ ያለው ምንድን ነው? 

አቻምየለህ ታምሩ

እንደ ዱቄት ተበትኗል፣ እንደ ጉም ተኗል፣ ተስፋ ቆርጦ ተበታትኗል፣ የኢትዮጵያ ኅልውና አደጋ ወደማይሆንበት ደረጃ አውርደነዋል፣ ወዘተረፈ…የተባለው ነፍሰ በላ የፋሽስት ወያኔ  ጦር ከትግራይ አልፎ ባጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ የወሎ፣ ጎንደርና አንዳንድ የአፋር ካባባቢዎችን እንዲወርር የመደረጉ ጉዳይ ተራውን  ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካ እናውቃልን የሚሉትም ግራ ሲያጋባ ይታያል።   
 
የፋሽስት ወያኔ ነፍሰ በላ አራዊት ባሕላዊ ጨዋታዬ ነው የሚለውን ጦርነት ለመጀመር ለዓመታት ሲዘጋጅ ቆይቶ በያዝነው ዓመት ጥቅምት 24 ቀን ከሰማኒያ በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ የጦር ክምችት የሚገኝበትን የሰሜን ዕዝን አጥቅቶ መሳሪያውን ከቀማና  ወታደሩን ከፈጀ በኋላ ባሕላዊ ጨዋታው የሆነውን ጦርነቱን ቢጀምርም ከጥቃት በተረፈው የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩና የአፋር ኃይሎች የሰነዘሩበትን የመከላከል ጥቃት ግን መቋቋም የቻለው ለሁለት ሳምንታት ያህል ጊዜ ብቻ ነበር።
በለኮሰው እሳት በሁለት ሳምንታት ውስጥ ተለብልቦ አሳፋሪ ሽንፈት የተከናነበውና በትዕቢት ተወጥረው ሲመኩ የነበሩ የፖለቲካ አምበሎቹን ጭምር ያጣው ፋሽስት ወያኔ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በብርሀን ፍጥነት በርካታ የወሎ፣ ጎንደርና አንዳንድ የአፋር ካባባቢዎችን እንዲወርር መደረጉ ምን አይነት ኃይል አግኝቶ ነው የሚል ጥያቄ ያስነሳል።
ፋሽስት ወያኔ ሳይዋጋ እንዲገባ የተደረገባቸውን አካባቢዎች በሚመለከት ይህን ቦታ አሸንፌ ተቆጣጠርሁ፣ እዚህ ተዋግቼ ገባሁ ወዘተረፈ እያለ ከጣራ በላይ የሚያስጮኸው ነገር የተካነበትን ቅጥፈቱን እንጂ የጀግንነት ጉዳይ እንዳልሆነ ውስጡ ተክፍቶ ሲታይ  በቀላሉ የሚታይ ነው። ፋሽስት ወያኔዎች ሳይዋጉ እንዲይዙ በተደረጉባቸው አካባቢዎች ገብተው የማሸነፉ ጀግኖች ስለመሆናቸው ሲቀደዱ የሚሰሙት በሁለት ሳምንት ውስጥ ብቻ ያጠቁትና ትጥቁን የቀሙት ሠራዊት እንደገና ተደራጅቶ [ከደጀን ኃይሉ ጋር]  በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዳሸነፋቸውና በርኩሰቱ ሰይጣንን የሚያስንቀው ስብሓት ነጋ ተማርኮ ሌሎች አምባሎቹ እንደተደመሰሱባቸው ይዘነጉታል።
የሆነው ሆኖ እየሆነ ስላለው ነገር እስካሁን ከሰበሰብኳቸው መረጃዎች  የሚከተሉትን  ዋናዋና ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።
1. “የተኩስ አቁም” እና ፋሽስት ወያኔ  ወደ “አማራና አፋር  ክልሎች” እንዲገባ የመፍቀድ ጉዳይ
ለሕዝቡና ለወታደሩ ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ከአሜሪካ ጫና ለማምለጥ ሲባል ፋሽስት ወያኔ “አማራና አፉር ክልሎች”ን ያለመከላከል  እንዲወርር ተደርጓል። ይህ የጎዳው ሲቪሉን ማኅበረሰብ ብቻ ሳይሆን መከላከያ ሠራዊቱንና ወረራውን ያልጠበቀውን የአካባቢውን አስተዳደር፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ጭምር ነው። መከላከያ ሠራዊቱ ከትግራይ እንዲወጣ የተደረገበት አሰራር የተቀናጀ  እንዳልነበረው ሁሉ ሰሜን ወሎ አካባቢ ካምፕ ሰርቶ በሰፈረው መከላከያ ሠራዊትም በነበረው መዝረክረክ ፋሽስት ወያኔ ምርኮኛ ወታደሮችንና ከባድ መሳሪያ እዲያገኝ አድርጎታል።
2. የፋሽስት ወያኔ “የጅግኛ፣ ጅግና” ቀረርቶ   
ፋሽስት ወያኔ “አማራና አፋር ክልሎች”  እንዲገባ ከተደረገ  በኋላ እነ ዐብይ አሕመድ ወረራውን ማስቆም አልፈለጉም አልያም እንደፈለጉት ወስነው ማስቆም አልቻሉም። ጭራሹን የአዲስ አበባ ጅቡቲን መስመር ለመያዝና ወደ ሱዳን ለማስከፈት ተንቅሳቀሰ። ሆኖም ግን  በሁሉቱም ግንባሮች ጠንካራ መከላክል ስለተደረገ ፋሽስት ወያኔ ሳይስካለት ቀርቷል። የፋሽስት ወያኔ “ጅግና”፣ “ጅግና” ቀረርቶ ባዶ የሆነው እዚህ ላይ ነው። ፋሽስት ወያኔ በውጊያ ብልጫ ቢኖረው ኖሮ ጅቡቲ መስመር ወይንም ሱዳን ደርሳ ነበር። ሆኖም የ“ጅግና”፣ “ጅግና” ጨዋታው ባዶ ቀረርቶ ስለሆነ ሱዳን መድረስና የአዲስ አበባ ጅቡቱን መስመር መቆጣጠር ሕልም ሆኖ ቀርቷል።
3. ፋሽስት ወያኔ ሰሜን ወሎን እንዲወርር የተፈጠረለት ምቹ ሁኔታ 
የፋሽስት ወያኔ ሰሜን ወሎና ጋይንትን አሸንፌ ተቆጣጠርኩ ፕሮፓጋንዳ ባዶ ቀረርቶ ነው። ዐቢይ አሕመድ  የአዲስ አበባ ጅቡቲ መስመር እንዳይያዝ በአፋር ግንባር ያለው ኃይል ካጠናከረ በኋላ ሰሜን ወሎን ብአዴን ያሰማራው ሚሊሻና የተወስነ ልዩ ኃይል እንዲከላከለው ከፍቶ ለቆለታል ማለት ይቻላል። ፋሽስት ወያኔም ይህን  የተፈጠረለትን አጋጣሚ በብልጠት ተጠቅሞበታል። በአንድ ጊዜ ብዙ ከተምችን ለማጥቃትና ለማያዝ የሚያስችል አቅም የሌለው ፋሽስት ወያኔ ብልጠቱን ተጠቅሞ የሰሜን ወሎ አካባቢዎችን እንዲወርና የዘር ማጥፋት እንዲፈጽም ተደርጓል።
4. ወያኔ ወደ ሰሜን ወሎና ጋይንት የገባበት ስልቱ 
ፋሽስት ወያኔ ወደ ሰሜን ወሎና ጋይንት የገባው አለኝ የሚለውን ዋናውን ኃይሉን ካስጠጋ በኋላ 30ና 40 የሚሆኑ ተዋጊወቹን ወደየከተማው አስቀድሞ ይልካሉ። የነዚህን ጥቂት ተዋጊዎቹ ተኩስ ሲሰማ ከተማው ተያዘ በሚል ሕዝቡ ይበረግጋል። ከዚያ ቦታው/ከተማው ተያዘ ይባላል። በዚህ ተወናብዶ የአካቢው ታጣቂም ይሽሻል።  ከዚያ ፋሽስት ወያኔ ያስጠጋችውን አለኝ የምትለውን ጦሯን  የበለጠ ታስጠጋና ይዞታዋን ታሰፋለች። የየአካባቢ የብአዴን ባላደራዎች [ባለሥልጣናት ላለማለት ነው] ሕዝቡን በማደራጀትና መረጃ በመስጠት በነዚህ ፋሽስት ወያኔ በሚልካቸው ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መውሰድ ሲገባቸው ከሕዝቡ አስቀድመው አካባቢውን/ከተማውን ለቀው ይሸሻሉ። እነዚህ የብአዴን ባላደራዎች ባካባቢያችን ወፍ የለው እያሉ ሕዝቡን ከሚዋሹ የየአካቢያቸውን ሚሊሻና አስታጥቁን  አታስፈጁን የሚለውን  የወጣት ኃይል አደራጅተው ጠንካራ መከላከል  ቢያደርጉ ኑሮ በሰሜን ወሎ ተያዙ ከተባሉት ከተሞች ግማሹ አይያዙም ነበር::
5. የጋይንት ሁኔታ
ፋሽስት ወያኔ ጋይንትም 30ና 40 የሚሆኑ ተዋጊወቹን በመላክ ተመሳሳይ ብልጠት ለመጠቀም ሞክሯል። ይህ የፋሽስት ወያኔ ብልጠት በተወስነ ደረጃ መደናገጥና የመፈናቀል ነገር ቢያግጥትም የጋይንት ሕዝብ የተሻለ የተደራጀ ስለሆነ “ከተማ ያዝን፤ ጋይንትን ተቆጣጠርን” የሚል ፕሮፓጋንዳ ለመንዛት ፋሽስት ወያኔ የላካቸው 30ና 40 የሚሆኑት ተዋጊዎቹ ወደ ጋይንት ለመግባት ሲሞክሩ ሕዝቡ ባደረገው መከላከል የሳት እራት ሆነዋል።  ባለኝ መረጃ መሰረት አንድ ጊዜ የተላከው ቡድን ከተበተነ በኋላ  በደጋሜ የሚላኩ 30ና 40 የሚሆኑ ተዋጊዎች እዚህም እዚያም የሚፈጽሙት የሽፍትነት ተግባርና ሽብር ያለፈ ጋይንትን ያዝነው የሚለው ውሸት ነው። ፋሽስት ወያኔ በጋይንት ያጋጠመው መከላከል በአፋር በኩል ከገጠመው ሕዝባዊ መከላከል ጋር ተመሳሳይ ነው ማለት ይቻላል።
6. የመረጃ ክፍተት
ለፋሽስት ወያኔ ወረራ ትልቅ እድል የፈጠረለት የፌዴራና የክልሉ መንግሥት ተብዮዎቹ  ለሕዝብ ትክክለኛ መረጃ በአገባቡ ለመስጠት አለመቻልና አለመፈለግ ነው። ፋሽስት ወያኔ የፈለገውን ሽብር በሕዝብ ዘንድ ሲዘራና ሽብርና ፍርሀት ሲፈጥር ያንን የሚቋቋም መረጃ የመስጠትና የማንቅት ስራ መንግሥት ነኝ በሚለው አካል አልተሰራም። ባጭሩ ፋሽስት ወያኔ  ዞን፣ ወረዳና ከተማ ያዝኩት እያለ እደፈለገ እንዲፈነጭ እድል የሰጠው መንግሥት ተብዮው ጋዜጠኞችን ልኮ ማረጋገጥ የሚቻለውን በቀላሉ ማጋለጥ አለማቻሉ ነው:። ይህም ለብዙ መላምት እና ለፋሽስት ወያኔ ተከፋዮች ሕዝብ ለማሸበር እድል ከፍቷል።
ምን ይሄ ብቻ! ፋሽስት ወያኔ  ተቆጣጠርኳቸው ባላቸው አካባቢዎች የዘር ማጥፋት፣ የጦር ወንጀል፣ ግድያ፣ ዝርፊያ፣  አስገድዶ መድፈር እየፈፀመ ይገኛል። ይህንን ሁሉ  የፋሽስት ወያኔን አለማቀፍ ወንጀል አገዛዙ ለማጋለጥ ፍላጎ የለውም ወይም በቂ ስራ እየሰራ አይድእለም። አገዛዙ በሚቆጠጠረው የአፋር ክልል ውስጥ ፋሽስት ወያኔ ከሁለት መቶ በላይ ንጹሐንና ከመቶ በላይ ሕጻናትን ሲፈጅ  ስለዚህ የፋሽስት ወያኔ የጦር ወንጀል በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜና የተሰራው ጋዜጠኞች ወደ አካባቢው ተልከው  ግፉአን በማናገር ሳይሆን ዩኒሴፍን ዋቢ በማድረግ ነው። ፋሽስት ወያኔ በመርሳ የመርዝ መርፌ እየወጋ የፈጃቸው የአማራ ወጣቶች እልቂት እስካሁን በአገዛዙ ሜዲያ አልተዘገበም።
7. ማጠቃለያ
ፋሽስት ወያኔ ወደፊትም ወደ ሌሎች አካባቢዎች 30 እና 40 የሚሆኑ ተዋጊወቹን እያስገባ ጥይት በማጮህ ተቆጣጥሬያለሁ እያለ ሕዝብ ማሸበሩን ይቀጥላል። ሕዝብ ይህን የወያኔ ስልት አውቆ በተለይ ወጣቱ በየአካባቢው የተጀመሩ አደረጃጀቶችን በማጥናከር፤ የኅልውና ተጋድሎ የጎደለውን በመሙላት፤ የላላውን በማጥበቅ፤ የተኙትን በመቀስቀስና የነቁትን ይዞ ወደፊት በመሮጥ የፋሽስት ወያኔን ሽብር በቀላሉ ማክሸፍ ይኖርበታል። በየትኛውም አካባቢ የሚኖረው ሕዝብ ከማንም አካል ምንም ነገር ሳይጠብቅ በየአካባቢው የጀመረውን አደረጃጀት በማጥበቅ  አካባቢውን ከወራሪ መጠበቅ አለበት። ከየትኛው አካል በላይ አካባቢውን ከወራሪ የመጠበቅ ኃላፊነቱ በዋናነት የራሱ መሆኑን ሕዝቡ ማመን ይኖርበታል።
Filed in: Amharic