>

የላኮመልዛ መንገድ ለወያኔ ለምን ጨርቅ ሆነለት? (መስፍን አረጋ)  

የላኮመልዛ መንገድ ለወያኔ ለምን ጨርቅ ሆነለት?

መስፍን አረጋ  


  1. ወያኔና ኦነግ በፀረ አማራት እንደተቀናጁ እነሱ ራሳቸው በይፋ ማወጃቸውን አንድ ይበሉ፡፡
  2. ኦነገ ላኮመልዛን ሰሜን ኦሮሚያ እንደሚል ሁለት ይበሉ፡፡
  3. ጠቅላይ አዛዡ ዐብይ አሕመድ፣ ኢታማዦር ሹሙ ብርሃኑ ጁላ፣ መከላከያ ሚኒስትሩ ቀንዓ ያደታ፣ አየር ኃይል አዛዡ ይልማ መርዳሳ  ወዘተ… በሆኑበት፣  ኦነጋውያን ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ በሚቆጣጠሩት፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ አብዛኞቹ አዛዦችና የመስመር መኮንኖች ኦነጋውያን፣ በዚያ ላይ ደግሞ የሙስና ጨምላቆች (ለቃል ምርጫየ ይቅርታ) መሆናቸውን ሦሰት ይበሉ፡፡ 
  4. የኦሮምያና የትግራይ ክልሎች ልዩ ኃይሎቻቸውን ይበልጥና ይበልጥ እንዲያጠናክሩ በበጀተት ላይ በጀት እየጨመረ፣ ያማራ ክልል ግን ልዩ ኃይል እንዳያሰለጥንና ያሰለጠነውንም እንዲበታትን አብይ አሕመድ በተዛዋሪ መንገድ ቀጭን ትእዛዝ የሰጠው ደሴ ላይ መሆኑን ዐራት ይበሉ፡፡    
  5. እነዚህን አራት ነጥቦች ሲያገናኗቸው፣ የአማራ ዋናው በሽታ አቶ አሻግሬ መሆኑን በቀላሉ ይገነዘባሉ፡፡  
  6. አማራ ከኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ አፍዝ አደንግዝ ከተላቀቀ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡  

EMAIL:

mesfin.arega@gmail.com   

Filed in: Amharic