ጋዜጠኛ ተስፋዬ ወልደሥላሴ
*.... ማረጋገጥ ባልችልም ጀነራል አስራት ከገዳይ ቡድኑ በርከት ያለ የወንበራ ወርቅ በእጅ መንሻነት እንደተሰጠው ይነገራል፤ ይህን መረጃ አለማመን አይቻልም (ምክንያቱም ጉምዞቹ እንደ ባህል ሆኖ ሀሰት መናገር ስለማያውቁ ከእነሱ የተገኘ መረጃ ለእውነት የቀረበ ነው)
ሰሞኑን ዋነኛው ጠላት ህወሓት ወደ ጥልቅ ገደል ሊወረወር ጅራቱ በተያዘበት በእዚህ ወቅት ሌላ አጀንዳ ማስገባት ተገቢ አይደለም በሚል የመተከልን እና የወለጋን ጉዳይ ባልሰማ ዝም ብዬ ነበር ። ነገር ግን የመተከሉም ሆነ የወለጋው ነገር ብርቱ ችግር ሁኗል ።
ጀነራል አስራት ዲኔሮ መተከልን ሊያረጋጋ የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ሆኖ ከተመደ አመት አለፈው ። ነገር ግን ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሲከፋ እንጅ ሲሻሻል አላየንም ።
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉኝ ጀነራል አስራት ለጥቂት ቀናት አዲስ አበባ እያለ የ22ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ሰይፈ ኢንጌ የተባለ ሰው ተመድቦ ቀጠናውን እሱ እስከነበረበት ሰዓት ድረስ ማረጋጋት ችሎ እንደነበረ መተከሎች ይናገራሉ ።
ኮሎኔሉም በአጭር ቀናት በመተከል ህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ማትረፍ ችሎ ነበር ነገር ግን ከቀናት በኋላ ጀነራል አስራት ሲመጣ ችግሩ ተባብሶ ቀጥሏል ። ማረጋገጥ ባልችልም ጀነራል አስራት ከገዳይ ቡድኑ በርከት ያለ የወንበራ ወርቅ በእጅ መንሻነት እንደተሰጠው ሀገሬው ያወራል(ምክንያቱም ጉምዞቹ እንደ ባህል ሀሰት መናገር ስለማያውቁ ከእነሱ የተገኘ መረጃ ነው)
ዛሬ ከዞኑ ዋና ከተማ ግልገል በለስ ወደ ድባጢ ወረዳ መስመር 3 ኪ ሜ ርቀት ኤሲፃ የተባለች ንዑስ ቀበሌ ላይ ከማለዳው 1:00 ጀምሮ ይሄንን ጹህፍ እስከጻፍኩበት 5:30 ድረስ በመከላከያውና በጉምዝ ገዳይ ቡድኑ መካከል ከባድ ጦርነት እየተደረገ ይገኛል ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በልዩ ሁኔታ በሚመሩት መተከል ዞን ቦታው ድረስ በመሄድ ለህዝቡ በአንድ ወር ውስጥ ወደ ቀድሞው ሰላም እንመልሰዋለን ቢሉም ችግሩ እስከ አሁን ድረስ ሊቀረፍ አልቻለም ።
የእኔ ጥያቄ ጀነራል አስራት ለአንድ አመት የመሩት ቀጠና ውጤት ካልተገኘበት ጀነራሉን ከተቻለ በአጭር ጊዜ ሰላም ባመጡት ኮሎኔል ሰይፈ አሊያ በሌላ አመራር መተካት ያልተቻለበት ምክንያት ምን ይሆን ?
ያውም የሀገሬው ሰው በሙስና የሚያማቸው ጀነራል !! ግልገል በጦርነት እየታመሰ ቢሆንም አዛዡ ጀነራል ዛሬ ዳንግላ ከተማ ይገኛል !!