>

ጨጨሆ መድኃኒዓለም በከባድ መሳሪያ ተመታ...!!! (ታደለ ጥበቡ )

ጨጨሆ መድኃኒዓለም በከባድ መሳሪያ ተመታ…!!!

ታደለ ጥበቡ


ጨጨሆ መድኃኒዓለም ጉዳት እንደደረሰበት የሰማሁት ማታ ላይ ነበር። ገዳሙን በሚገባ ስለማውቀው እንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር። በካህናቱ ላይ ጉዳት ይደርስ ይሆን እያልሁ  የሰቀቀን ሌሊት ነው ያሳለፍኩት። መረጃውን አስቀድሜ ያልጻፍኩት በመንግሥት ሚዲያ ይዘገባል በሚል ነበር።

ጨጨሆ መድኃኒዓለም  ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተ 1500 አመት አስቆጥሯል። የበርካታ ቅርሶች ባለቤት ነው። በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ 754 ኪ.ሜ፣ ከባህር ዳር 195 ኪ.ሜ፣ ከደብረ ታቦር 90 ኪ.ሜ ይርቃል፡፡ ከጥንት ጀምሮ መንገደኞች ከወሎ ወደ በጌምድር ወይም ከበጌምድር ወደ ወሎ ጉዞ ሲያደርጉ ጨጨሆ ላይ ዕረፍት ማድረጋቸው ዛሬድ የደረሰ ባህል አለ፡፡

ጨጨሆ መድኃኒዓለም ሙሉ ሥሙ የበቅሎ አግድ ጨጨሆ መድኃኒዓለም ይባላል፡፡ የጥንት ነገሥታት ሳይቀር በጨጨሆ ሲያልፉ ከበቅሏቸው ወርደው፣ ተሳልመው የሚያልፉበትን ቅዱስ ቦታ ነው። ነገርግን
ይሄ ሽፍታ ቡድን በከባድ መሳሪያ  አውድሞታል።

በርግጥ ትህነግ ገና ከጥንስሱ የትግሉ ዋና ዓላማ ፀረ-ፅዮዊናዊ ነበር። ታፍራና ተከብራ የኖረችውን   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን “አከርካሪዋን ለመስበር” በማኒፌስቶአቸው ላይ ጭምር ጽፈው በእጅጉ ሲተጉ የነበሩ ናቸው።

ፋሽስት ወያኔ በሽፍትነት ዘመኑ ቤተ ክርስቲያንን አምርሮ መታገልና ማዳከም የፈለገበት ምክንያት ከህውሓት ጥንስስ ጀምሮ ፖሊሲ አውጪ አመራር ስጭና አዋጊ ኮማንደር የነበሩት ያሁኑ ዶ/ር አረጋዊ ብርሄ  ዶክተር አረጋዊ   “የሕዝባዊ ወያና ሓርነት ትግራይ ፖለቲካዊ ታሪክ (1967-1983) በሚለው መጽሐፋቸው፣ ወያኔ በወቅቱ ቤተክርስትያንን አምርሮ መታገልና ማዳከም የፈለገበት ምክንያት የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሕዝቡ ውስጥ ያላት ተቀባይነትና በሀገር አንድነት ላይ ያላት ጽኑ አቋም፣  እግዚአብሔር የለም ብሎ የሚያስተምረውን ሶሺያሊዝምን መቃወሟ፣ በሰንደቅ ዓላማና መሰል ኢትዮጲያዊ መገለጫዎች ላይ የነበራት አስተምህሮ እና መገንጠልን መቃወምና የሀገሪቱን አንድነት ደጋፊ በመሆኗ፣ በወያኔ ጥርስ ውስጥ እንድትገባ ምክንያት እንደሆነ  ነግረውናል። ህውሓት ከዚህ ስሪቱ አንጻር ቤተ ክርስቲያን ቢያወድም የሚያስገርም አይሆንም።

Filed in: Amharic