>

አድር ባይነት እና ፖለቲካል ኮሬክትነስ የሚሉት የመሃይምነት እና የራስ ወዳድነት መሸሸጊያ ዋሻ...!!!

አድር ባይነት እና ፖለቲካል ኮሬክትነስ የሚሉት የመሃይምነት እና የራስ ወዳድነት መሸሸጊያ ዋሻ…!!!

ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር [=] ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር።
አንዱን CRDA/በሲአርዲኤ ሰራተነቱ ዘመን በሰራው አድንቄው ነበርና የዛሬውን ስውር ጥፋት አለውቀሰውም ማለት ለእኔ አይሰራም። ከቻልክ ሁለቱን የገዳይ አስገዳይ ጠበቆች ተመሳስሎ ተረዳ እና ህዝችንን ከድምጽ አልባው ዘር ማጥፋት እናድነው። ለማሳያነት ከአባይ ሚድያና ከሪፖርተር ማህደሮች የተወሰዱ የሁለቱን ኮሚሽነሮች ሪፖርቶች መመሳሰል አቅረቤአለሁ።
ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር
የበቂሊንጦ ቃጠሎው መሠረታዊ መንስዔ በማረሚያ ቤቱ ሁከት እንዲቀሰቀስ አስቀድመው ይፈልጉ የነበሩ የሕግ እስረኞች አማካይነት ሆን ተብሎ አድማ መጀመሩ፣ አድማውን በማንኛውም ጊዜና ወቅት ለማነሳሳት ፍላጎት እንደነበራቸው በተደረገው ምርምራ ለመረዳት መቻሉን የኮሚሽኑ ሪፖርት ይገልጻል፡፡ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር (ሚያዚያ 2008 ዓ.ም. )
በሦስት ክልሎች በተፈጠሩ ‹‹ሁከቶች›› 669 ሰዎች መሞታቸውን የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ይፋ አደረገ፤፤ በጎንደር ማራኪ በሚባለው ቦታ የፌዴራል ፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ በወሰደው ዕርምጃ 12 የፀጥታ ኃላፊዎችና አራት ሲቪሎች መገደላቸውን፣ በማረሚያ ቤት የተወሰደው ዕርምጃም ሕግን የተከተለ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡ በአማራ ክልል ብሔር ተኮር ጥቃት በመካሄዱ 11,678 የትግራይ ተወላጆች መፈናቀላቸውን ገልጸዋል፡፡ በሰጡት ምክረ ሐሳብም በተፈጠረው ረብሻና ብጥብጥ ለተከሰተው ሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት መውደም አጥፊዎች ተለይተው ለሕግ እንዲቀርቡ ብለዋል፡፡(ኮሚሽነር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር (ዶ/ር)  ሐሙስ ሚያዝያ 12 ቀን 2009 ዓ.ም.)
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈፀሙ ግድያዎች የዘር ማጥፋት ወንጀልን አያሟሉም- በአብዛኛው የዘር ማጥፋት  የሚፈጸመው ለአጻፋ በሚነሳው ቅድሚያ ግድያ በተፈጸመበት የማህበረሰብ ሊሆን ስለሚችል የተፈፀሙ ግድያዎች የዘር ማጥፋት ወንጀልን ቴክኒካሊ አያሟሉም ማለታችን  ተገቢነው።
( ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የካቲት 28 2013)
ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. በታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት ከ150 በላይ ነዋሪዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና ሌሎች ሰዎች ለኮሚሽኑ አስረድተዋል። በቀጣይ ቀናት ከነዋሪዎች የተውጣጡ ሰዎች ብሔርን መሰረት ያደረገ የአጸፋ ጥቃት በማድረሳቸው 60 ሰዎች መገደላቸውን፣ ነዋሪዎችም ወደ አማራ ክልልና ወደ ኪራሙ ከተማ መፈናቀላቸውን ኮሚሽኑ ተረድቷል።( ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ነሃሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም.)
አድር ባይነት እና ፖለቲካሽል ኮሬክትነስ የሚሉት የመሃይምነት እና የራስ ወዳድነት ኮኮስ በተለቀለቀ ማህበረሰብ ያለማደጌ ማሳያው ይህ ነው።
ኑርልኝ መኩሪያው
Filed in: Amharic