ምን ነካህ የማይባለው ብአዴን!
አቻምየለህ ታምሩ
ምን ነካህ የማይባለው ብአዴን በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ላለው ጥፋት ሁሉ ራሱን ተጣያቂ አድርጎ ስልጣኑን ያስረክባል፤ የበደለውን ሕዝብ ለመካስ ራሱን ለፍርድ ያቀርባል እየተባለ ሲጠበቅ ከፋሽስት ወያኔ ወረራ በተረፉት አካባቢዎች መንግሥትነቱ ይታወቅለት ዘንድ የሥርዓተ መንግሥቱ ምልክት የሚሆነውን አርማ ምረጡልኝ እያለ ነው።
የአማራ ሕዝብ ልጅ አዋቂ ሳይል፤ አካባቢና ሃይማኖት፤ ጾታና እድሜ፤ የስራ መስክና የፖለቲካ ርዕዮት ሳይወስነው ኅልውናን ከፈጸሞ መጥፋት፣ መንደሩን ከውድመት፣ ጥሪቱን ከዘረፋ ለመታደግ በየጦር ግንባሩ ተሰልፎ እየተዋደቀ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ለብአዴን አጣዳፊ ጉዳይ የሆነው አራት የቀድሞ ጠግላይ ግዛቶች ተጠርንፈው ከተፈጠረው ክልል ውስጥ ከፈጣሪው ከፋሽስት ወያኔ ወረራ በተረፉት በሁለቱ ጠቅላይ ግዛቶች ላይ ያለው የገዢነት ሥልጣን ሙሉዕ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። እንግዲህ! አማራ ከፋሽስት ወያኔ የግፍ ወረራ ነጻ ለመውጣት በየግንባሩ መስዕዋትነት እየከፈለ ያለው በእንደነዚህ አይነት የዘመን ጉዶች እየተመራ ነው።
ያናገርናቸው በየግንባሩ የሚፋለሙ ዘማች ወገኖቻችን ሁሉ የሚነግሩን በርሀብና በውኃ ጥም እየተጠራሞቱ እንደሆነ ነው። አገኘሁ ተሻገር የሚባለው ጉድ አልዋጋም አሉኝ ያላቸው የጎጃምና የወሎ ሚሊሻዎች እንዲዘምቱ ከተደረጉ በኋላ የኔ ብሎ የሚጠይቃቸው መንግሥት አጥተው ለሶስት ቀናት ያህል ምግብ ሳይቀምሱ ሲንከራተቱ ሰንብተው በርሀብ ሕይወታችን ከሚያልፍ ምግብ በልተን ብንሞት ይሻላ ብለው ወደ ቤታቸው የተመለሱ ዘማቾችን ነው።
ሕዝባችን ለዘማቹ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ አቅርቧል። በግንባር የተሰለፉት ዘማቾች ግን የሚናገሩት ርሀብና ጠኔውን እንዳልቻሉት፤ ወገናቸው የሚያዋጣው የዘማች ስንቅ እንዳልደረሳቸው ነው። መዝመትና መስዕዋት መሆኑ ጽድቅ ሆኖ ቢያንስ ዘማቾቹ ጊዜ በማይሰጠው ርሀብ እንዳይዳከሙ መሰረታዊ የምግብ ፍላጎታቸውን ማሟላትየሚገባው በመንግሥትነት የተሰየመ አካል ዘማቾች በርሀብ አለንጋ ተገርፈው ዘመቻው እክል እንዳይገጥመው ዘማቹ እህልና ውኃ ባፋጣኝ ይቀርብለት ዘንድ የአቅርቦት መዋቅር ይዘረጋል ተብሎ ሲጠበቅ እሱ ግን ቅድሚያ የሚሰጠው የኅልውናውን ዘመቻ ሳይሆን ግዛቱ የጸና መሆኑን እንዲታወቅለት ስለሆነ የመንግሥትነት አርማውን እወቁልኝ ብሎ ብቅ ብሏል።
ሌላው ገራሚው ነገር ምረጡልኝ ብሎ ያቀረበው አርማ ይዘት ነው። ብአዴን እንደ ድርጅት ለኢትዮጵያ አንድነትና ኅልውና መጠበቅ፣ ለሕዝቦቿ ሉዓላዊነትና ክብር፣ ለታሪኳ እና ለኩሩ ሕዝቧ መሻት የሚመጥን ትግል ሲያደርግ እንደኖረ የአርበኞች ማኅበር፤ የነፍጠኛና ትምክህተኛ ምልክት እያለ ሲያንቋሽሸውና ሲዘምትበት የኖረውን በአድዋ፣ በእንዳባጉና፣ በወልወልና በሌሎች አውደ ውጊያዎች አይበገሬ የኢትዮጵያ ጀግኖች ከፍ አድርገው ያውለበለቡትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከኮረም እስከ ጋይንት፤ ከተከዜ እስከ ዛሬማ ድረስ ያለውን ግዛቱን አንድ ጥይት ሳይተኩስ ለቅቆና በሹሞቹ መንገድ መሪነትና አስተኳሽነት እነዚህን አካባቢዎች አስወርሮ ሲያበቃ “ጥይት በግንባሬ እንጂ በጀርባዬ ከመታኝ አትቅበሩኝ” ያሉትን አይበገሬ አርበኞች ሰንደቅ የአርማው ክፍል ለማድረግ መነሳቱ ድርጅቱ ተፈጥሮ ለሰው ልጆች ሁሉ የለገሰቻቸው ማፈር፣ መናደድ፣ ቁጭትና ጸጸት የሚባሉት ስሜቶች የሌሏቸው ሰዶማውያን ስብስብ ስለመሆኑ ከዚህ በላይ ማሳያ ሊኖር አይችልም።
ኢትዮጵያ በፋሽስት ጣሊያን በተወረረችበት ወቅት ከሕዝብ በፊት ወራሪውን ጠላት ለመፋለም የዘመቱት መሪዎች ነበሩ። ፋሽስት ጣሊያን ተከዜን ተሻግሮ ስሜንን እንዳይወርር በደጃዝማች አያሌው ብሩ የሚመራው የሰሜን ጦር ዋና አዛዡ የጋይንቱ ጀግና ፊታውራሪ ሺፈራው ጌታሁንና በራስ እምሩ የሚመራው የጎጃም ጦር ዋና አዛዡ ፊታውራሪ ክንፌ ማን ያህልሀል በተከዜ ግንባር ሲፋለሙ መስዕዋት ሆነዋል። ፋሽስት ጣሊያን ተከዜን የተሻገረው በፊታውራሪ ሺፈራው ጌታሁንና በፊታውራሪ ክንፌ ማን ያህልሀል መቃብር ላይ ነው። በማይጨው ግንባር የተካሄደን ጦርነትም ያየን እንደሆነ ፋሽስት ጣሊያን ማይጨውን አልፎ ኮረምን የረገጠው የጦር መሪው ራስ ሙሉጌታ ይገዙና ረዳታቸው የነበሩትን ደጃዝማች በየነ ወንድማገኘሁ [ሊጋባው በየነን] መስዕዋት ከሆኑ በኋላ ነው። በምስራቅ በኩልም ፋሽስት ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት የረገጠው እነ ፊታውራሪ አለማዬሁ ጎሹ ወልወል ላይ፤ እነ ደጃዝማች አፈወርቅ ወልደሠማያት ደግሞ ቆራሄ ላይ ከወደቁ በኋላ ነው።
ፋሽስት ወያኔ ባካሄደብን ወረራ ግን ሕዝብን ጥለው ወራሪውን ጠላት በመቶዎች ማይል ርቀው የፈረጠጡት የብአዴን ሹማምንት ናቸው። የሰሜን ወሎ የብአዴን ሹማንምት ወደ ደሴና አዲስ አበባ የፈረጠጡት ፋሽስት ወያኔ ኮረም መያዙን ሲሰሙ ገና ቆቦ ከመድረሱ በፊት ነው። ሕዝብ ወራሪውን ጠላት ለመፋለም ከደቡብ ወሎ፣ ከሸዋ ከጎጃምና ጎንደር ወደ ራያ ግንባር እየዘመተ በነበረበት ባለበት ወቅት የሰሜን ወሎ የብአዴን ሹማምንት መላ ቤተሰባቸውን ይዘው ወደ አዲስ አበባና ደሴ እየሸሹ ነበር። በደቡብ ጎንደር፣ በሰሜን ጎንደርና በዋግ የነበሩት የብአዴን ምንደኞችም ግንባር ላይ እየተፋለመ የነበረውን ሕዝብ ትተው ወደ ባሕር ባርና ጎንደር የሸሹት ፋሽስት ወያኔ ተከዜን፣ ደብረ ዘቢጥን [አንቺምን] እና አሸንጌን ከማለፉ በፊት ነው።
ቀደም ብዬ እንዳልሁት ፋሽስት ጣሊያን ተከዜን፣ ማይጨውንና አሸንጌን ተሻግሮ ወሎና ጎንደርን የወረረው የየአካባቢው መሪዎች ከወደቁ በኋላ ነው። ባሌላ አነጋገር ፋሽስት ጣሊያን ወሎና ጎንደርን የወረረው የነ ፊታውራሪ ሽፈራው ጌታሁንን፣ የነ ፊታውራሪ ክንፌ ማን ያህልሀልን፣ የነ ራስ ሙሉጌታ ይገዙንና የነደጃዝማች በዬነ ወንድማገኘሁን አስከሬን ተራምዶ ነው።
ፋሽስት ወያኔ ግን መላውን ሰሜን ወሎን፣ ደቡብ ጎንደርን፣ ዋግና ሰሜን ጎንደርን በወረራ ሲይዝ እንኳን የበላይ አመራር የሆነ የብአዴን ሰው የአንድም እንኳን የብአዴን ካድሬ አስከሬን አልተራመደም። አንድም የብአዴን ካድሬና አመራር ለጎንደርና ለወሎ መስዕዋትነት የከፈለ የለም። በሌላ አነጋገር ፋሽስት ወያኔ ወሎና ጎንደርን የወረረው ብአዴን በሕይዎት እያለ፤ አይደለም የብአዴን አመራር አንድም እንኳን የብአዴን ካድሬ መስዕዋትነት ሳይከፍል እግሬ አውጪኙን ወደ ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴና አዲስ አበባ ሸሽቶ በሚገኝበት ወቅት ነው። የእነዚህ ሰዎች ድርጅት ነው እንግዲህ ፋሽስት የነ ፊታውራሪ ሽፈራው ጌታሁንን፣ የነ ፊታውራሪ ክንፌ ማን ያህልሀልን፣ የነ ራስ ሙሉጌታ ይገዙን፣ የነደጃዝማች በዬነ ወንድማገኘሁን፣ የነፊታውራሪ አለማዬሁ ጎሹ፣ እነ ደጃዝማች አፈወርቅ ወልደሠማያትና እልቆ ቢስ “ጥይት በግንባሬ እንጂ በጀርባዬ ከመታኝ አትቅበሩኝ” ባይ አርበኞችን ሰንደቅ አላማ ሳያፍርና ሳይከብደው የአርማዬ ክፍል ላደርግ ነውና ምረጡልኝ የሚለን!
ብአዴን ከአማራ ሕዝብ ባሕል፣ ታሪክ እና እሴት የተፋቱ፣ እንጥፍጣፊ ኢትዮጵያዊነት፣ ኅሊና እና ወገናዊነት የሌላቸው ወያኔዎች “ገ’ለን ቀብረነዋል” ያሉት አማራ መቃብሩን ፈንቅሎ እንዳይወጣ መቃብር ጠባቂ እንዲሆኑ ተደርገው የተፈጠሩ የሕወሓት ነውረኞች ድርጅት እንደመሆኑ መጠን የሚመጥነት አርማ እስካሁን ድረስ ሲገለገልበት የኖረው የሕወሓት አርማ ነው። በርግጥ ዛሬ ብአዴን ከሕወሓት ድርጅት ወደ ኦሕዴድ/ኦነግ ንብረትነት ተላልፏል። ብአዴን ባለፉት ዘመናት ሲገለገልበት የኖረው አርማ ላይ ባለጊዜዎቹ ካልወደዱለት ወይም የቀድሞዎቹ ጌቶቹ በአርማው ላይ የባለቤትነት ጥያቄ ካነሱበትና አርማን መቀየር ካስፈለገው በሕወሓት ዘመን እንዳደረገው ሁሉ የዛሬውን ጌታውን አርማ [የአባገዳ አርማ የሚሉትን ማለቴ ነው] አደራደሩን በመለዋወጥ አርማው ሊያደርግ ይችላል። የአባ ገዳ አርማ የሚባለውን አርማ እነ የዶክተር ገላና ድርጅት ቀድሞኛል የሚል ከሆነ ብአዴን የጫኑትን ሁሉ የሚሸከም አህያ ስለሆነ ከሕወሓት ወረራ በተረፉት ጠቅላይ ግዛቶች ካርታ ላይ የአህያ ምልክት አድርጎ አርማውን ሊቀርጽ ይችላል።
ከዚህ ውጭ ሕዝብን ለወራሪ ትተው የፈረጠጡ የባንዳና ሰዶማውያን ስብስብ “ጥይት በግንባሬ እንጂ በጀርባዬ ከመታኝ አትቅበሩኝ” ይሉ የነበሩና ከሕዝብ በፊት ከጠላት ጋር ሲፋለሙ መስዕዋት የሆኑ ጀግኖች አርበኞቻችን ምልክት የሆነውን የኢትዮጵያን ሰንደ ዓላማ እንዲቀልድበት አንፈቅድለትም። ብአዴን የሽንፈት፣ የነውረኛነት፣ የአድር ባይነትና የሆዳምነት ጥግ፤ የባንዳነትና የጠላት አስተኳሽ ማሳያ፤ የእፍረት የለሽነትና የጽልመት ተምሳሌት የሆነ የታሪክ አተላው እንደመሆኑ መጠን ያለ ባሕሪው፣ ያለ ስሪቱ፣ ያለ ተፈጥሮው፣ ባልዋለበትና በማይመለከተው ታሪክ ውስጥ ገብቶ የጀግንነት፣ የአይበገሬነት፣ የአትንኩኝ ባይነትና የኢትዮጵያዊነት ምልክት የሆነውን የኢትዮጵያን ጀግኖች ሰንደቅ አላማ የአርማዬ ክፍል አደርጋለሁ ብሎ ዝሆን አክል ብላ ተሰንጥቃ እንደሞተችው እንቁራሪትም መሰቃየት የለበትም።
In all, changing ANDM’s emblem is like putting lipstick on a pig. It is a superficial and cosmetic change to a soulless and sellout organization in a futile attempt to disguise its fundamental failings.