>

በአማራና በአፋር ምድር የትግራይ ህጻናትና ሴቶች እንደ ቅጠል እየረገፉ ነው...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

በአማራና በአፋር ምድር የትግራይ ህጻናትና ሴቶች እንደ ቅጠል እየረገፉ ነው…!!!
ዘመድኩን በቀለ

*…. … የትግራይ ወታደሮች አልልም የትግራይ ልጆች እየተዋጉ ያሉት በማያውቁት መልክአ ምድር ላይ ነው። በዚያ ላይ ባዶ ሆዳቸውን በራብ ጠውልገው ነው። አይተው በማያውቁት ብርዱ ቆፈኑ ከባድ በሆነ በረዶ በዘለ ተራራ ላይ መተኮስ አቅቷቸው እንደተኮራመቱ ነው እያለቁ የሚገኙት። በዲያስፖራ በአዲስ አበባ ያለው ትግሬም “ወያኔዎቹ ጎንደር ሊደርሱ ነው፤ ደሴ ሊገቡ ነው” ብሎ ከመቋመጥ በቀር ይሄን እልቂት ሲቃወም አይታይም። ትናንት ተመልሶ እንዲመጣ የሚመኙ የድሮ ሥርዓት ናፋቂዎችም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ብቻ ነገርየው በጣም ያሳዝናል….!
 
… የትግራይ ቴሌቭዥን እንዲያው ተሳስቶ ድንገት እንኳ በትግራይ ስላለው ራብ እና ጥም… ስለተከሰተው ጠኔና ችጋርም አያወራም። በዳያስጶራ ያለው ትግሬም “በሎም” በሚለው በአሉላ ሶሎሞን የፌስ ቡክ ጥቅስ ራሱን “ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ” ከንቱ ስሜት ሲቃትት ከመዋል በቀር ቆም ብሎ ለማሰብ አይፈልግም። ስለ ድል፣ ስለ ተቆጣጠርነው ወሬ እንጂ እንደቅጠል እየረገፉ ስላሉ ምስኪን የትግሬ ወጣቶች አይተነፍሱም። እሱኛው ግድም ሲሰጣቸው አይታይም።
… ትግሬዎቹ በየትኛውም የሚድያ መርሀ ግብራቸው ላይ ስለ ችግራቸው፣ ስለ ራብ ጠኔአቸው፣ ስለ መብራት ስልክ መጥፋት እና እጥረቱ እንብዛም አይተነፍሱም። እሱኛውን ችግራቸውን ሌላው ኢትዮጵያዊ እና የፈረንጅ ጋዜጠኞች፣ የአውሮጳና የአማሪካ ባለሥልጣናት እንዲጮሁላቸው ነው የሚፈልጉት። እነሱ ስለ መከራው፣ ስለ ሰቆቃው ትንፍሽ ማለት አይፈልጉም። ስለ ምርኮ፣ ስለ አሸናፊነት፣ ስለ ድል፣ ስለ በሎም ብቻ ነው የሚደሰኩሩት። ሰቆቃቸውን ግን ሌላው እንዲያወራላቸው ይፈልጋሉ። ራስ ወዳድነት ይባላል።
… ይሄ ትክክል አይደለም። ይሄ ነውር ነው። ደግሜ እናገራለሁ። ምንም የጦርነት ልምድ የሌላቸው የትግሬ ህጻናት የጦር ልምድ ካለው፣ በዚያውም አሸናፊዋን ኢትዮጵያን ወክሎ ከሚዋጋ ሠራዊት ጋር አጋጥሞ በባዶ ሜዳ መሸለል ነውር ነው። ወንጀልም ነው። ሰንጋ እየቀረበለት የሚዋጋን ልምድ ያለው ወታደር የማሽላ ቆሎ እየበሉ እገጥማለሁ ማለት አሳዛኝም ነው። እደግመዋለሁ፣ አሁንም እደግመዋለሁ። ለጥቂት 50 ዓመት ሙሉ ከሥልጣን መውረድ ለማይፈልጉ ጥቂት ፊውዳል የህወሓት ባለ ሥልጣናት ተብሎ ምስኪኑ ትግሬ እንደ ቅጠል በዐማራና በአፋር ምድር መርገፍ የለበትም። ምክር ነው።
… ምንአልባት ግን ታላላቆቻችሁ ለዘመናት ዐማራውን ጠላት አድርገው በዐማራ ላይ በፈፀሙት ግፍ የተነሣ እናንተ ልጆቻቸው በዚያው በዐማራ ምድር ላይ ትረግፉ ዘንድ የፈጣሪ ፍርድ ሆኖም እንደሆን አላውቅም። ከትግራይ ምድር በኤንትሬ እየተጫኑ መጥተው በዐማራ ምድር እንደ ቅጠል መርገፍ ሌላ ምን ሊባል እንደሚችል አላውቅም። ብቻ እኔ አላውቅም። ምን የመሰለች ቆንጅዬ የትግሬ ወጣት በማታውቀው ውጊያ በማታውቀው ምድር ላይ አንጀቷ በከባድ መሳሪያ ተዘርግፎ ማየቱ ይዘገንናል። የትግሬ ትውልድ በዐማራ ምድር ላይ እያለቀ ነው። ይሄ በሜካም እያበደች ሚዲያ ላይ ቀርባ ለምትደነፋዋ መዓዛ ጊደይ ምንም ላይመስላት ይችላል። ምስኪኗ በትግራይ የምትገኝ ትግሬ ግን ዘሯ እየጠፋ ነው። ይመዝገብልኝ።
… የትግሬ ልጆች እየተዋጉ ያሉት በማያውቁት መልክአ ምድር ላይ ነው። በዚያ ላይ ባዶ ሆዳቸውን በራብ ጠውልገው ነው። አይተው በማያውቁት ብርዱ ቆፈኑ ከባድ በሆነ በረዶ በዘለ ተራራ ላይ መተኮስ አቅቷቸው እንደተኮራመቱ ነው እያለቁ የሚገኙት። በአዲስ አበባ ያለው ትግሬም ወያኔዎቹ ጎንደር ሊደርሱ ነው። ደሴ ሊገቡ ነው ብሎ ከመቋመጥ በቀር ይሄን እልቂት ሲቃወም አይታይም። ትናንት ተመልሶ እንዲመጣ የሚመኙ የድሮ ሥርዓት ናፋቂዎችም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ብቻ ነገርየው በጣም ያሳዝናል።
… ያለቀው ያልቃል እንጂ አጠፋዋለሁ የምትለው ዐማራ አጠፋሃለሁ እያልከው ናና አጥፋኝ ብሎ ቁጭ ብሎ አይጠብቅህም። ዥል አይደለም። ሞኝም አይደለም። በወሎ፣ በሰሜንና በደቡብ ጎንደር የትግሬ ጦር ገብቶ ያደረሰበትን ጉዳት ስላየ ነግ በእኔ ነው ብሎ ወጥሮ እየተገተገህም ነው። የትግሬ ጦር እንደማይራራለት ስላወቀ ዐማራውም ራሱን በሚገባ እየተከላከለ ነው። እናም እንዲሁ እየተንጓተተ ህዝቡ ሁሉ ያልቃል እንጂ ህወሓት ዳግም ወደ ሥልጣን ትመጣለች ማለትም ዘበት ነው። ይልቅ ተናግሬአለሁ ትግሬው በከንቱ አይለቅ። በጊዜ ዘራፊ፣ ገዳይ አስገዳዮቹን ወንጀለኛ የወያኔ ባለ ሥልጣናት እጅ ስጡ በሏቸውና የጦርነት ምዕራፉን ቋጩ።
… አሁን ከኋላ ያለው የትግሬ ህዝብ ከፊት የሄዱት የትግሬ ልጆች በምን ዓይነት ሁናቴ ላይ እንዳሉ መረጃ የለውም። መረጃ እንዲኖረውም አልተደረገም። አልተፈለገምም። በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ኢንተርኔቱ የተከፈተ ጊዜ። ከደጀን የሚገኘው ትግሬ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ፣ ይሄ የእልቂት መረጃ ከኋላ ላለው ደጀን ለተባለው ህዝብ በደረሰ ጊዜ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ ነው። ልክ እንደ ሳዳም ሁሴን፣ እንደ እነ ጋዳፊ ወያኔዎቹን እነ ጌታቸው ራዳንና ደብረ ጽዮንን አይቀጡ ቅጣት የሚቀጣው ራሱ ህዝቡ ነው የሚሆነው። ከምር የሚደርሰኝ መረጃ እጅግ ይዘገንናል ብቻ አይገልፀውም።
… በዐማራ መ እና በአፋር ምድር የትግሬ ህጻናት ወጣቶች እያለቁ፣ እየረገፉም ነው። እያለቁ ያሉት ደግሞ ከትግራይ ክልል ውጪ ለወረራ በሄዱበት በዐማራና በአፋር ምድር ላይ ስለሆነ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ትንፍሽ ሊልላቸው አልቻለም። በሰው መሬት ላይ ነው መጥተው እየረገፉ ያሉት። በሳምንት አዲስ አበባ እንገባለን ብለው ቃል ስለገቡላቸው ነጮቹም እነ ጻድቃንን አምነው ነበር። ይኸው ለወራት በጎንደርና በወሎ፣ በአፋርም ምድር እየረገፉ ነው። ነገርየው ከባድ ነው።
… አሁን በትግራይ ህክምና፣ መድኃኒትም ስለሌለ የታመመ ሰው አይድንም። ይሞታል። የሚበላ ምግብ ስለሌለም የራበው ሰው አይድንም። ይሞታል። ይሄ በእውነት የእግዚአብሔር ቁጣ እንጂ ሌላ ምንም ሊባል አይችልም። ከእልቂት በቀር በጦርነት የሚመጣ ለውጥ የለም። ኢትዮጵያን ሰድቦ፣ ኢትዮጵያን አዋርዶ፣ ኢትዮጵያን አክፋፍቶም ድል የለም። ይልቅ በሥጋም በነፍስም ቅጣቱ ከባድ ነው። አባ አመሀ ኢየሱስ እንደተናገሩት የትግሬ ህዝብ ድንጋይ ተሸክሞ ከወንድሙ ዐማራ ህዝብ እና ከመላው ኢትዮጵያዊ እግር ስር ተደፍቶ ይቅርታ መጠየቅ ያለበት ዘመን አሁን ይመስለኛል። ከምር ጨከን ብላችሁ ሞክሩት። ያለበለዚያ 11 ሺ ወጣት በ4 ሰዓት ውስጥ በማስፈጀት የምታመጡት ለውጥ፣ የምታገኙት ድልም የለም። አበቃ። አለቀ። አከተመ።
••• ፎቶዎቹን የለጠፍኩት ተዘልለው ለተቀመጡት ሁሉ ጦርነት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ ለማሳየት ነው። በሰላም ቀጠና ያላችሁ እናንተ ከመጋረጃው ጀርባ እንዴት የሰው ልጅ እረገፈመ እንዳለም ለማሳየት ነው። አዎ ይሄን መመልከት የሚረብሻችሁ ይኖራል። እህል የማይበላችሁ። ሙዳችሁ የሚሰረቅ፣ ቀናችሁ ያውም ቅዳሜያችሁ የሚበላሽ ይኖራል። ለደንታህ ነው። በኢትዮጵያ ምድር የሰው ልጅ አስከሬን እንዴት ምድሪቱን እንደሞላት ማየት ግን አለብህ። ለዚያ ነው እየደበረህም ቢሆን የለጠፍኩልህ። ጠግባችሁ አትብሉ።
… በግዳጅም፣ በስሜትም ተገፋፍተው ዘምተው በዐማራና በአፋር ምድር ላይ እየረገፉ ያሉትን የሟቾች አንገት ስትመለከቱ ደግሞ ሟቾቹ፣ እያለቁ ያሉት እነማን እንደሆኑ ይገባችኋል። ከዚህም ከዚያም ወገን ማለት ነው። አዎ ሟቾቹ በሙሉ ባለማዕተብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ናቸው።
Filed in: Amharic