>

አማራ ወይም ሞት እንዳትል! አማራ ወይም ትህነግ በል...!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

አማራ ወይም ሞት እንዳትል! አማራ ወይም ትህነግ በል…!!!

ጌታቸው ሽፈራው

አማራ ወይንም ሞት ልትል ትችላለህ አይደል? ከሞት የባሰ አለ ተብለሃል። ትህነግ በቁም የምታየው በመሬት ላይ የሞት ክፉው ወኪል ነው ይልሃል ከስር ያለው ፅሁፍ! አማራ ወይንም ሞት እንዳትል! አማራ ወይንም ትህነግ በል! ከከፋው ሞት (ትህነግ) እና ከአማራ ማንን ትመርጣለህ???
 
አማራ ወይም ትህነግ 
የቱን ትመርጣለህ…?
በርዕሱ ላይ የተቀመጠው መፈክር ሳይሆን የዕጣ ፈንታ ምርጫ  ጉዳይ ነው፡፡ ‹አማራ ወይም ሞት› ልንል እንችላለን። ሞትን በቁሙ አይተነው አናውቅም። አሸባሪው ትህነግ ግን ሞትን ወክሎ ሊያጠፋን ምሎ እንደተሳ ኑረንበትም ዛሬም ደግም ወርሮን በተግባር አይተነዋል። አሸባሪው ትህነግ ለአማራ የሚመኘው ሞትን ነው። ከሞትም የክብርም ሞት አለ። ደመኛ ጠላታችን ትህነግ ግን ጨፍጭፎ፣ አሰቃይቶ ነው የሚገድል። ከሞት የከፋ ነው። ለአማራ ክፉው የሞት ቁጥር አንድ ተወካይ ትህነግ ነው። ስለሆነም የማናየውን ሞት ይዘን አማራ ወይንም ሞት አንልም። የከፋ ሞት ያቀደልን ትህነግ አለ። አማራ ወይንም ትህነግ ብለን እንምረጥ!
አሸባሪው ትህነግ ገና ሲመሰረት የተነሳው የትግራይን መልካም ጉዳይ ይዞ አይደለም። የአማራን ሞት አስቀድሞ ነው የተነሳው። አማራ ሞቶ ሲቀበር ነው ትግራይ መልካም የሚገጥማት ብሎ የተነሳ እርጉም ድርጅት ነው።
አሸባሪው ትህነግ በማንፌስቶው ሦስት ጠላቶች አሉኝ ብሎ ነበር የተነሳው።
አንደኛ፡- በኢምፔሪያሊዝም ፍረጃ የተጋረደው ሲገለጥ…
ትህነግ አንደኛ ጠላቴ ያለው ኢምፔሪያሊዝምን ነበር። ይህ ቃል በወቅቱ አፍለኛ ስለነበርና ትህነግም አብዮተኛ ለመባል በማኒፌስቶው አጠቃልሎ አካቶት ነበር። ላይ ላዩን ካልሆነ በስተቀር ፍረጃው በተግባር ከአማራ ራስ አልወረደም ነበር።
ኢምፔሪያሊዝም ሀገራት በተለይ በወቅቱ ምዕራባዊያን ወታደራዊ ኃይላቸውን ተጠቅመው፣ በቅኝ ግዛት ፖሊሲያቸው መሰረት በሌሎች ሀገራት ላይ የሚያደርሱትን ጫና ለመግለፅ የዋለ ነው። በወቅቱ አብዮተኛ የተባሉ ድርጅቶችም መንግሥትነትን ይዞ የነበረው ደርግም ‹ኢምፔሪያሊዝም ይውደም› እያሉ ይፎክሩ ነበር። ትህነግ ግን ኢምፔሪሊያሊዝምን ጠልቶ አልነበረም። ኢትዮጵያ ወደ ምሥራቁ ዓለም በተለይም ሩሲያ አይኗን ስታዞር ትህነግ ይታገዝ የነበረው በወቅቱ ኢምፔሪያሊስት በሚባሉት የምዕራብ ኃይሎች ነው።
ትህነግ አብዛኛውን አመለካከቱን የወረሰው ከፋሽስት ነው። ፋሽስት ደግሞ አንደኛ ደረጃ ኢምፔሪያሊስት ነበር። ትህነግ በእውኑ ኢምፔሪያሊዝምን ጠልቶ አይደለም። አንድም በወቅቱ ተቀባይነት ለማግኘት ነው። ግን ደግሞ ኢምፔሪያሊዝም በወቅቱ የሚረገም ስለነበር ትህነግ ሄዶ ሄዶ ወደ አማራ ያስጠጋው ነበር። ትህነግ እንዲህ ነው መርህም አቋምም የለውም! ያልቀየረው ቋሚ ባህሪው ቢኖር ከአማራ በተቃራኒ መሰለፍና ለደጉ የአማራ ሕዝብ የማይበርድ ጥላቻን ማሳደር ነው፡፡
ኢትዮጵያ ከበርካታ ሀገራት ጋር መልካም ግንኙነት ነበራት። በአጤ ምኒልክ በይበልጥ ደግሞ በአጤ ኃይለሥላሴ ዘመን ከምዕራባዊያኑ ጋር መልካም ግንኙነት ፈጥራለች። ለአሸባሪው ትህነግ ደግሞ የነገሥታቱ ዘመን ‹‹የአማራ አገዛዝ ነው›› ተብሎ በሐሰት የተፈረጀ ነው። የነገሥታቱን ዘመን ለአማራ ሰጥቶ፣ ኢትዮጵያ በነገሥታቱ ዘመን ከምዕራባዊያን ጋር የነበራትን ግንኙነት ለአማራ አስረክቦ ኢምፔሪያሊስት አደረገው። ዙሮ ደግሞ ኢምፔሪያሊስት ካለው ኃይል እግር ስር ወድቆ ወታደራዊ እርዳታ ይጠይቅ ነበር፡፡ ትህነግ የቀኝ እጁን ወደ ኢምፔሪያሊስቷ አሜሪካ ለተራድዖ እየዘረጋ በግራ እጁ ደግሞ የአልባኒያን ኮምኒስታዊ ኀልዮት ያነበንብ የነበረ መርህም አቋምም የለሽ የሆነ ጉደኛ ድርጅት ነበር፡፡
በወቅቱ “ኢምፔሪያሊስት” የሚባሉት ሀገራት ‹ጦርነት ሀገርን ይሠራል፤ ሀገር ጦርነትን ይሰራል› (War made the state, and the state made war) በሚለው የሀገረ-መንግሥት ምስረታ የሚያምኑ፣ በአንፃራዊነት የግለሰብ ነፃነትን የሚፈቅዱ፣ ስለ ሀገር ክብርና ታሪክ የሚጨነቁ ነበር። የእነዚህን ሀገራት ባሕል ከአንተ የሀገረ-መንግሥት ምስረታ ባሕሪ፣ የሀገር ፍቅርና ግለሰባዊ እምነት ጋር አማትቶ ከተፈረጁት ጋር አማራን ፈርጇል። ከዚህ የባሰው ደግሞ አሸባሪው ትህነግ አማራን ቅኝ ገዥ አድርጎ መፈረጁ ነው። ልክ ምዕራባዊያኑ በኃይል አፍሪካና ሌሎች አህጉሮችን ሲገዙ ኢምፔሪያሊስት እንደተባሉት፣ አሸባሪው ትህነግ አማራን ‹‹ቅኝ ገዥ››፣ ‹‹ጨቋኝ›› ፣ ሌሎቹን በኃይል የሚገዛ አድርጎ ሳለው። አሸባሪው ትህነግ ገና እንደተመሰረተ ሰነዱ ላይ “ኢምፔሪሊዝም ጠላታችን ነው” ብሎ ሲያስቀምጥ ከምዕራባዊያን አንፃር ያሰበው ቢያስመስልም፤ ከልቡ አቋም ይዞበት አልነበረም። ዋነኛ ምልከታውም ሆነ አቋሙ ከአማራ አንፃር ነው። ምዕራባዊያኑማ ከምስረታው በኋላ አግዘውታል። ስልጣን ከያዘ በኋላ ደግሞ ዋና የብድር ምንጩ እነሱው ነበሩ። አሁን ተመልሶ ጫካ ሲገባም የሚያግዙት ጥቂቶች ቢሆኑም ድሮ ኢምፔሪያሊስት ተብለው የተፈረጁት ናቸው። እንደ ትርጉሙ ቢሆን አሸባሪው ትህነግ ‹ኢምፔሪያሊዝም ጠላቴ ነው› ብሎ ሊያስቀምጥ አይችልም። ለአንተ ነው። ለአማራ ነው። የጋራ ሀገረ-መንግሥት ምስረታን እስከደገፍክ፣ ተገንጣይነትን እስካላቀነቀንክ ብሔርህ ምንም ይሁን ምን ለአሸባሪው ትህነግ አንተ ‹አማራ› ነህ።
ሁለተኛ፡- ፊውዳሊዝም፤ አማራውን የማጥቂያ መሳሪያ
 
አሸባሪው ትህነግ በማንፌስቶው ጠላቴ ነው ብሎ በሁለተኛ ደረጃ ያስቀመጠው ፊውዳሊዝምን ነው። ፊውዳሊዝም የኢኮኖሚ መሰረቱን መሬት፣ የፖለቲካ ሥርዓቱን ንግሥና ያደረገ ሥርዓት ነው። ይህ አስተሳሰብ ከ1950ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ በተማሪዎች እንቅስቃሴ ተቃውሞ ሲገጥመው፣ ከእንቅስቀሴው አራማጆች ውስጥ በርካታ የአማራ ልጆች የነበሩ ቢሆንም፣ ትህነግ ግን በትግል ‹‹ትንተናው›› ፊውዳሊዝምን የአማራ ዕዳ አድርጎ ነበር ያቀረበው፡፡ እውነታው ግን የትግሬ ነገሥታቶች፣ መሳፍንቶችና ገዥዎች የነበሩ መሆኑ ነው፡፡ በተመሳሳይ የትግሬ መሬት ከበርቴዎች ነበሩ። በሌሎች የኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች ውስጥ ተመሳሳይ  የፊውዳል ሥርዓት ነበር፡፡ በያኔዋ ኢትዮጵያ ፊውዳሊዝም የትም ይገኝ የነበረ እንጅ የአማራ ብቻ አልነበረም። አማራው በዚህ ሥርዓት የተበደለበት ቢሆንም በትህነግ ፍረጃ ግን ለፍቶ አዳሪውም፣ በጭሰኝነት ይሰቃይ የነበረውም ጭምር ፊውዳል ነው። በዚህ የሐሰት ትርክት ጥላቻን አንግቦ ወደሥልጣን የመጣው ትህነግ፣ በግዛት ተስፋፊነቱ በጉልበት ከጠቀለላቸው የወልቃይትና የራያ ግዛት በተጨማሪ፣ መሬት ሲቀማ የአማራን ያህል ያራቆተው የለም። መለስ ዜናዊ “መሬት የግል ይሁን”  ሲባል  “አማራና ጉራጌ ይገዛዋል” ማለቱን የጥላቸው መጠን ፖሊሲዎቹን እንዳያሻሽል አድርጎት እንደኖረ በማሳያነት የሚያቀርቡት አሉ፡፡
ያም ሆኖ ትህነግ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ በፍጥነት ዘመናዊ ፊውዳል ሆነ። ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለቤተሰብ፣ ለዘመድ አዝማድ፣ ለሚቀርበው ሁሉ መሬትን በማንአለብኝነት ስሜት አድሏል። ካድሬዎች የመሬት ባለሀብት ሆነው፣ ገበሬውን ጭሰኛ  አድርገውት ታይቷል። የትህነግ አመራሮችና አባላት በግለሰብ ደረጃ ከገዥ-መደብነት ወደ ቱጃርነት ተሻግረዋል፡፡ ለዚህ ማሳለጫው ከመንግሥታዊ ሌብነቱ እኩል የዝርፊያ መሳሪያ የሆነው ኢፈርት የተባለው የቢዝነስ ኢምፓየሩ ነበር፡፡ ሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፍ በድርጅቶቹ ተቆጣጥሮ የኢትዮጵያን አንጡረ ሀብት በዝባዥና ደም መጣጭ ሆኖ 27 ዓመታትት ገዝቷል።
በአንድ ወቅት የኢፈርት ሥራ አስኪያጅ የነበረው ስብሃት ነጋ ድርጅቱ በሀብት ከአፍሪካ አንደኛ መሆኑን ተናግሯል። የኢፈርት ሀብት የተሰበሰበው አሸባሪው ትህነግ ጫካ እያለም ከኢትዮጵያ በዘረፈው ገንዘብ ጭምር ነው። ‹ፊውዳሊዝም ጠላቴ ነው› እያለ ፊውዳል የሆነበትን ሀብት ያካበተው ጫካ እያለ ነበር። አሸባሪው ትህነግ ራሱ ዘመናዊ ፊውዳል ነው። ፊውዳሊዝምን እጠላዋለሁ የሚለው ከአማራ ጋር ሲያገናኘው ብቻ ነው። ከሚጠላው አማራ ጋር ሲገናኝ፣ ምንም ቢሆን ይጠላዋል። ለራሱ ሲሆን ግን አይጠላውም።
ሦስተኛ፤ አማራን እንደ ቋሚ ጠላት
ሦስተኛው ጠላቱ በግልጽ ያስቀመጠው የአማራን ሕዝብ  ነው። ኢምፔሪያሊዝም ጠላቴ ነው ሲል፣ ኢምፔሪያሊዝም ከቅኝ ግዛት ጋር ስለሚገናኝ አማራም ‹‹ቅኝ ገዥ››፣ ‹‹ጨቋኝ››፣ ‹‹በዝባዥ›› ነው ብሎ ብዙ ሳይዞር ኢምፔሪያሊዝም ጋር አገናኘው። ሁለተኛ ጠላቴ ነው ያለውን ፊውዳሊዝምን ደግሞ ጠቅልሎ ለአማራ ሰጠው። በሦስተኛው ግን ሽፋን ሳያስፈልገው አማራ ጠላቴ ነው ብሎ መጣ።  ቀደም ሲል ባስቀመጣቸው ጠላቶችም ሲገለጥ ጠላት ያለው አማራን  ነው። ይሄ ስላልበቃው ግን የአማራን  ስም ጠርቶ መጣ። አማራ ጠላቴ ነው አለ።
በእርግጥ ኢምፔሪያሊዝምን፣ ፊውዳሊዝምን ከትግሬ ጋር ሲሆን አያገናኛቸውም። ያለ አግባብ ከአማራ ጋር አገናኝቶ ነው የጠላቸው። ባይጠላቸውማ ጫካ እያለም ኢምፔሪያሊስት የተባሉት እንዲያግዙት ደጅ ባልጠና፤ ሲያግዙትም እጁን ዘርግቶ አይቀበልም ነበር። ፊውዳሊዝምን ቢጠላ ኢትዮጵያን ዘርፎ በግልም፣ በድርጅትም ከገዥ-መደብነት አልፎ የናጠጠ ሀብታም አይሆንም ነበር። የጠላው ፊውዳሊዝም ጋር ሲልከሰከስ እንደሚገኘው፣ የጠላውን ፊውዳሊዝም እንደተጨማለቀበት ግን የጠላው አማራ ጋር መልካም ነገር ኖሮት አያውቅም። አስተሳሰቦቹንም ጠላኋቸው ያላቸው ከአማራ ጋር አገናኝቶ ነው። ለአሸባሪው ትህነግ ዓለም አቀፋዊ፣ ርዕዮተ ዓለማዊም፣ አህጉራዊም፣ ሀገራዊም፣ ክልላዊም ችግሮች በሙሉ ከአማራ ጋር የሚያገናኛቸው ናቸው። አማራን ለመጥላት ሰበብም ሌላም ጉዳይ አይፈልግም። ሌላውን ለመጥላት ግን አማራን ሰበብ ያደርገዋል።
ለአሸባሪው ትህነግ “ቋሚ ወዳጅ፣ ቋሚ ጠላት የለም” የሚለው ዓለም አቀፋዊ መርህ አይሰራም። አማራን ቋሚ ጠላቱ አድርጎታል። በማንፌስቶው ላይ ከዘረዘራቸው ሦስቱ ጠላቶቹ በቋሚነት ጠላት አድርጎ የቀጠለው ከአማራ ጋር ነው። በስልጣን ዘመኑ በአማራ ሕዝብ ላይ ያልፈፀመው የበደል አይነት የለም። ትህነግ አቅምና እድል ባገኘበት ጊዜ ሁሉ አማራ ላይ የጥፋት ሰይፉን መዝዞ አጥቅቶታል።
የትህነግ ከፍተኛ አመራሮች “አማራን እንዳይነሳ አድርገን አከርካሪውን ሰብረነዋል” ብለው እስከመለፈፍ የደረሱት በዚሁ የጥፋት ሰይፋቸው ተማምነው ነበር። ይሁንና የማይሰበረው አማራ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ተቀናጅቶ አገዛዙ ላይ ሲያምፅ አሸባሪው ትህነግ ከመንበሩ ተነቅሏል።
በመቀሌ የግዞት ቆይታው ‹አማራን ረፍት መንሳት› በሚለው ድርጅታዊ መርሁ የሽብር ፖለቲካን ሲያራምድ የቆየው ትህነግ፣ ከመጋቢት 2010 እስከ ጥቅምት/2013 ድረስ በኢትዮጵያ 113 ግጭቶችን/ጥቃቶችን አቀነባብሯል፡፡ በዚህም በሺህዎች የሚቆጠሩ ሕይወታቸው አልፏል፤ በመቶ ሺህዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ በሚሊየን የሚቆጠሩ ንጹሐን ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡
በዚህ ሁሉ የቀውስ ጊዜ፣ ከሁለት ዓመት ተኩል ዝግጅት በኋላ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ከጀርባ ወግቶ ሥልጣን ሊቆናጠጥ ሲጥር፣ ቀዳሚ ለሀገር ዘብ ሆኖ ያስቆመው የአማራ የጸጥታ ኃይል እና የአካባቢው ሕዝብ ነው።
ከጥቅምት 24/2013 ጥቃት በኋላ ጫካ ሲገባ እንደድሮው ዙሪያ ጥምጥም ሄዶ አማራን ከሌላ ጠላት ጋር አልደረበውም። በዚህ ወቅት ፊውዳሊዝምም፣ ኢምፔሪያሊዝምም ጠላት ተብለው አልተካተቱም። ዛሬ በአደባባይ የሚለፍፈው ‹አማራ ጠላቴ ነው፤ ሂሳብ አወራርዳለሁ› በሚል ነው። ሌላ ተጨማሪ ጠላት መጥራት አላስፈለገውም፡፡
የቱን ትመርጣለህ…?
አሸባሪው ትህነግና አማራ በዓላማ የሚለያዩ ናቸው። በትህነግ ባሕሪ ምክንያት አማራና ትህነግ የሚጠፋፉ ሆነዋል። ትህነግ በቋሚነት የያዘው አቋም አማራ እንዲኖር አለመፈለግ ነው። ትህነግ የሀገር ክህደት ፈፅሞ መከላከያ ሠራዊት ሲያጠቃ አማራ ደጀን ሆኖ መከላከያ ሠራዊት የሚያተርፍ ሆነ። ትህነግ ፀረ ሀገረ መንግሥት ሲሆን አማራ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ሆኖ ሀገረ መንግሥቱን ለማስቀጠል የሚቆም ነው። በዚህም ምክንያት ትህነግ ለሀገረ መንግሥቱ የሚቆም፣ ለሀገር አንድነት የሚሠራን ሁሉ ብሔሩ ምን ይሁን ምን “አማራ” እያለ  ይጠራዋል። እነ ጌታቸው ረዳ የአማራ ልሂቅ እያሉ ሲረግሙ የሌላ ብሔር ተወላጅ የሆኑ ወታደራዊ አዛዦችን፣ ፖለቲከኞችንም ጭምር ነው።
እንዲህ  የሁሉም ችግር መነሻ አድርገው የሚያስቀምጡትን አማራ ስላልቻሉ እንጅ በምድር ላይ እንዲኖር አይፈልጉም። በሥልጣን ዘመናቸው ያኮላሹት፣ ያደኸዩት፣ በሕዝብ ቆጠራ የቀነሱት፣ ርስቱን ወስደው ባርያ ለማድረግ የጣሩት፣ አፍንው ያጠፉት፣ የጨፈጨፉት በመሬት እንዳይኖር ስለሚመኙት ነው። አሁንም  የሚጨፈጭፉት፣ ሊገድሉት ፈልገው ሲያጡት እንሰሳቱን አርደው በልቶ የቀሩትን በጥይት የሚገድሉበት፣ ሊጥና ድፍድፍም ከቤቱ እንዳይቀር የሚወስዱት፣ የሚበላና የሚለበሰውን ዘርፈውና አበላሽተው፣ ቤቱን አፍርሰው አውላላ ላይ እንዲወድቅ ነው።
ትምህርትና የሕክምና ተቋማቱን የሚዘርፉትና የሚያወድሙት ለነገ ተስፋ እንዳይኖረው ነው። በመሬት እንዳይኖር ከኖረም መሬት ሲኦል እንድትሆንበት፣ የቁም ሞት እንዲሞት ስለሚፈልጉ ነው። ሞት በአካል አይታኝም። ሞት ሰውን በተራ ይወስዳል። እንደ ትህነግ አይጨፈጭፍም። ሞት አይዘርፍም፣ አያወድምም። የክብር፣ የእድሜም ሞት አለ። የአሸባሪው ትህነግ ሞት ግን የከፋ ነው። ሞት በአካል ቢታይ ከትህነግ አይብስም።
እናም ‹አማራ ወይንም ሞት› ከምንል፣ ‹አማራ ወይንም ትህነግ› ብንል ይሻላል። ‹ኢትዮጵያ ወይንም ሞት› ከምንል ‹ኢትዮጵያ ወይንም ትህነግ› ቢባል ይሻላል። ደግነቱ ሞትን አንገድለውም። ትህነግን ግን ማጥፋት ይቻላል። እኛ ሞተን መኖር የሚፈልገውን ትህነግ ግብዓተ መሬቱን ማፋጠን እንችላለን። በዚህ ምድር ትህነግ አቅም እስካገኘ ድረስ የአማራ ሕዝብ የተጋረጠበት የሕልውና አደጋ ተባብሶ ይቀጥላል፤ እንደሕዝብ ተበትኖ የመቅረት አደጋም ሊያጋጥመው ይችላል። ስለሆነም መምረጥ አለብን። ያለን አማራጭ አንድ ብቻ ነው እሱም ማሸነፍ፡፡ እንደአማራ ሕልውናችንን አስከብረን ከሌሎች ወንድም ኢትዮጵያዊያን ጋር በሰላምና በፍቅር ለመኖር መደላድሉ የሃምሳ ዓመት ደመኛ ጠላታችንን ነቅለን መጣል አለብን፡፡
‹አማራ ወይንም ትህነግ› ለሚለው ምርጫ፣ አንዱን መምረጥ ይኖርብናል። አማራ እንዲኖር ከመረጥን የትህነግ ግብዓተ መሬት ለማፋጠን ዛሬውኑ ክተት ማለት አለብን!! የሃምሳ ዓመት ደመኛ ጠላት ሊቀበር ሰዓቱ ነውና አማራ ብለህ ተነስ!!
ሕዝባችን ያሸንፋል!
ሞት ለአሸባሪው ትህነግ!
Filed in: Amharic